ፈልግ

የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ ተጠሪ፣ ብጹዕ ካርዲናል ጁሰፔ ቬርሳልዲ፤ የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ ተጠሪ፣ ብጹዕ ካርዲናል ጁሰፔ ቬርሳልዲ፤  

የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ዓላማ ነፃ እና ሁሉ አቀፍ ዜጋን ማዘጋጀት መሆኑ ተገለጸ።

በጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ ተጠሪ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጁሰፔ ቬርሳልዲ፣ መጋቢት 20/2014 ዓ. ም. ይፋ በሆነው በካቶሊክ ትምህርት ቤት “ማንነት” መመሪያ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የካቶሊክ ትምህርት ቤት ዓላማ፣ ለሰው ልጆች ትኩረትን የሚሰጥ እና አቅመ ደካሞችን የሚያከብር ማኅበረሰብን መፍጠር ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አክለውም ግጭቶችን እና አለመግባባቶችን ለማስወገድ የሚያግዙ መርህዎችን እንደገና ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

"ማንነትን ማወቅ ራስን መከላከያ ሀሳብ ሳይሆን የተለያዩ ምርጫዎች የሚቀርቡበት መድረክ እንደሆነ የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣ የካቶሊክ ትምህርት ቤት በማንም ላይ ጫናን ሳያደርግ የሚያቀርባቸው አንዳንድ እሴቶች አሉ ብለው፣ በትምህርት ቤቶቹ ገብተው ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚወስኑት ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው እንጂ ትምህርት ቤቱ አለመሆኑን አስረድተዋል። ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቱ “የካቶሊክ ትምህርት ቤት የማንነት ውይይት” በሚል ርዕስ መጋቢት 20/2014 ዓ. ም. ይፋ ያደረገውን መመምሪያ ትርጉም ለቫቲካን የዜና አገልግሎት ያብራሩት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣ የጋራ ውይይት የካቶሊክ ማንነት መሠረታዊ አካል እንደሆነ አስረድተው፣ ከሁሉ አስቀድመው የሚመለከቱት፣ በጎዳናዎች እየተዘዋወረ ወደ ሁሉ ሰው ዘንድ በመሄድ፣ ሌላው ቀርቶ የተለየ ሀሳብ ያላቸውንም ጭምር ሲስያስተምር የነበረ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሆነ አስረድተዋል።

ታላቁ አስተማሪ ቅዱስ ጆን ቦስኮ፥ “ማስተማር የልብ ጉዳይ ነው” ያለውን የጠቀሱት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣

በጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ ይፋ ያደረገው ሰነድ ዓላማ፣ በተለይ ለአቅመ ደካሞች ክብርን በመስጠት፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋነኛ ባህሪ የሆነውን የፍቅር ምስክርነት ለሌሎች የሚያሰራጭ ማኅበረሰብን ማዘጋጀት እንደሆነ አስረድተዋል። በማብራሪያቸው ቁምነገረኛነትን፣ ሥነ-ምግባርን፣ ጥናትና ምርምርን እንዲሁም ሙያዊነትን ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ቤርሳልዲ፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ በጎ አድራጊነት እና እርስ በእርስ የመከባበር ስሜት ከሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ጋር መያያዝ አለበት ብለዋል። አንድ ወጣት እንደ ዜጋ እና እንደ ክርስቲያን ሌሎችን በሚያከብሩ፣ ልዩ ልዩ ሀሳቦችን በሚያቀርቡ፣ በሚገስጹ እና ነጻ የሆነ ስብዕና ባላቸው ሰዎች የሚታገዝ እንጂ በሚያስጨንቅ ወይም እጅግ ውስብስብ በሆነ ሳይንሳዊነት መጠመድ እንደሌለበት አስረድተዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቀውስ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን አዳክሞት የነበረ ቢሆንም በሌላ ወገን ማኅበራዊነት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን የበለጠ ግልጽ አድርጎታል ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣ በኅብረት ማጥናት፣ መወያየት፣ መጫወት፣ አንዱ ሌላውን እያከበረ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ማኅበራዊ ሐሳብን ለማሳካት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ይህን ምሳሌ በመከተል የውይይት፣ የወንድማማችነት፣ የዴሞክራሲ ሞዴሎች በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲያድጉ መሸጋገሪያ መሆን አለባቸው ብለው፣ በትምህርት ቤት ያልቀሰሙትን ወይም ያልተማሩትን በኅብረተሰቡ መካከል ማሳየት ይከብዳል ብለዋል።

መዋደድ ፆታዊ ብስለትን እንደሚጨምር የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣ ፆታዊ ግንኙነት የእግዚአብሔር ዕቅድ እና ፍላጎት መሆኑን ተናግረው፣ የፍቅር ግንኙነት በካቶሊክ ትምህርት ቤት ተቀባይነት ያለው ጭብጥ እንጂ እንደ ምርጫ የቀረበ መሆን የለበትም ብለዋል። ከሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በተጨማሪ ለሰው ልጅ ሊሰጥ የሚገባውን ክብር እና ፍቅር ማስተማር፣ እንዲሁም ከራስ ወዳድነት ይልቅ ለፍቅር ሲሉ እራስን ለሌሎች ለማዘጋጀት የሚያስችል ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። መልካም ትብብር በወላጆች እና በትምህርት ቤት መካከል ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያናት፣ በሕዝባዊ ማኅበራት እና በመንግሥት ተቋማት መካከልም ሊኖር እንደሚገባ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም አቀፉ የትምህርት ስምምነት ላይ መጋበዛቸውን አስታውሰዋል። በማከልም የሰው ልጅን በሚያካትት በክርስትና እምነት ጥናት መሠረታዊ ነጥቦች ላይ ግልጽ እና ታማኝ ውይይት በማድረግ ወደ ስምምነት የሚደረስ ከሆነ ዕድገትን ማምጣት የሚቻል መሆኑን ተናግረዋል። ይህ ተግባራዊ ከሆነ ትምህርት ቤትን እና ቤተሰብን ያካተተ አጠቃላይ የትምህርት ማኅበረሰብን እውን ማድረግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ምንም እንኳን በጊዜ ሂደት አንዳንድ አሉታዊ ውጤቶችን የሚያስከትል ቢሆንም ወላጆች ልጆቻቸው ሊቀስሙ የሚገባውን የትምህርት ዓይነት መምረጥ መልካም እንደሆነ ተናግረዋል።

መምህራንን በማዘጋጀት ሂደት ላይ መተባበር እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ብጹዕ ካርዲናል ቬርሳልዲ፣ በካቶሊክ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያስተምሩት መምህራን ሀሳብን ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን መልካም ማኅበረሰብ መፍጠርን ሊሰለጥኑ እንደሚገባ አስረድተው፣ በመሆኑም ከቤተሰብ፣ ከቁምስናዎች እና በአካባቢው ካሉ ሌሎች የትምህርት ተቋማት ጋር ለመነጋገር እና ለመወያየት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።

በጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ የበላይነትን በማንጸባረቅ ሳይሆን እንደ ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤትነቱ ለቤተ ክርስቲያናቱ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማበርከት በነጻ መንፈስ ለመወያየት እና ለማሰላሰል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። ጳጳሳዊ ጽህፈት ቤቱ ለቤተ ክርስቲያናቱ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ፣ በርካታ ብጹዓን ጳጳሳት በካቶሊክ ትምህርት ቤቶች እና በጳጳሳት መካከል ያለውን ግንኙነት በማብራራት መረጃ እንድንሰጥ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንደሆነ ገልጸው፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ አለመግባባቶችን ለማስወገድ፣ ከትምህርት ጋር፣ ደረጃውን የጠበቀ እና የተመጣጠነ መርህን እንደገና ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ፣ ይህም ውዝግቦች እና ግጭቶች አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ እንደሆነ፣ በጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የካቶሊክ ትምህርት ማስፋፊያ ጉባኤ ተጠሪ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጁሰፔ ቬርሳልዲ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት አስረድተዋል።

30 March 2022, 15:01