ፈልግ

የቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን  

ካርዲናል ፓሮሊን ከሩሲያው ላቭሮቭ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ውጊያው እንዲቆም ጠየቁ!

የቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ትናንት ማክሰኞ የካቲት 29/2014 ዓ.ም በስልክ መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን የሰላም ጥሪ በድጋሚ በማንሳት ለማንኛውም የሽምግልና ዓይነት የቅድስት መንበር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አክለው ገለጸዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ ካርዲናል ፓሮሊን ከሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ያደረጉትን የስልክ ውይይት አረጋግጠዋል።

"ካርዲናሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዩክሬን እየተካሄደ ላለው ጦርነት ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው በማሳየታቸው ጳጳሱ ባለፈው እሁድ በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ የተናገሩትን በድጋሚ አረጋግጠዋል።በተለይም በትጥቅ የተደገፉ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ የሰብአዊነት ኮሪደሮች ለሰላማዊ ሰዎች እና ለሰላማዊ ስደተኞች እንዲከፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ከትጥቅ ትግል ይልቅ ድርድር ያስፈልጋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የስልክ ጥሪውን ሲያጠናቅቁ የቅድስት መንበር ፈቃደኝነት በመግለጽ “እራሷን ለዚህ ሰላም አገልግሎት ለማቅረብ የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ” ፈቃደኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በመካሄድ ላይ ያሉ ድርድሮች

የሩሲያ ፌዴሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የንግግሮቹ ዜና በኢንተርፋክስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

"ፓርቲዎቹ በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ቀጣዩ ዙር ውይይት በቅርቡ እንደሚካሄድ እና በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ እንደሚደርስ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል" ሲሉ የሩሲያ ምንጮች ገልፀዋል ።

የሚኒስትር ላቭሮቭ ቃል አቃባዮች ሚኒስቴሩ ለካዲናል ፓሮሊን "በዩክሬን የተካሄደውን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መንስኤ እና ዓላማን በተመለከተ ስለ ሩሲያ ተነሳሽነት" እንዳሳወቁ ገልፀዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ እለት በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ወቅት በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ግጭት ወታደራዊ ዘመቻ ሳይሆን ጦርነት እንደሆነ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን "ከግጭቱ ጋር በተያያዙ ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እርምጃዎች እንዲወሰዱ፣  የሰብአዊ ኮሪደሮች አደረጃጀት እና አተገባበር እንዲከፈት እና ለስደተኞች እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

09 March 2022, 13:47