ፈልግ

 ፓራጉዋይ-ወንድማማችነት ፓራጉዋይ-ወንድማማችነት  

ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ፣ የቅዱስነታቸው የወንድማማችነት ሰነድ ተመራጭ መሆኑን አስታወቁ

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ጊዜያዊ ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ፣ መጋቢት 21/2014 ዓ. ም. ሮም በሚገኝ ኡርባኒያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚለው የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ላይ በማስተንተን ማብራሪያ ሰጥተዋል። ብጹዕነታቸው በማብራሪያቸው “የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን፣ ከማኅበራዊ ሕይወት ወደ ኋላ የቀሩትን ዘንግተው ለግል ደኅንነት ብቻ የሚደረጉ ያለፉት አስተሳሰቦችን በመተካት ተስፋን ሊሰጥ የሚችል ታላቅ ሀሳብ ነው” በማለት አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በአንድ ዘመን ከቶማስ ሞር እስከ ቅዱስ ስምዖን ድረስ ያሉ እና ሌሎች በምቾት ሕይወት ውስጥ የሚገኝ ማኅበረሰብ ባለራዕይ ደራሲዎች በራሳቸው መንገድ የሰው ልጅ ፍትሃዊ በሆነ እና ብልጽግና ባለበት ዓለም ውስጥ እንዲኖር ይመኙ ነበር።  እነዚያ የዕውቀት ማማዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ከሁሉም በላይ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ፈራርሰው በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሊደርሱባቸው በማይችሉት እና ተስማሚ በሆኑ ዓለም አቀፍ ዕቅዶች በመተካት ምልክት ጥለው አልፈዋል።

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ጊዜያዊ ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ መጋቢት 21/2014 ዓ. ም. በኡርባኒያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ በተግባር ተተርጉሞ በተጨባጭ የማይታየውን ታሪክን በአዲስ መልክ በማቅረብ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” ከሚለው ከር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ተመልክተዋል።

የፍትሃዊው ዓለም ዋጋ

በተግባር የማይተረጎም ምኞት በነባሩ ማኅበረተሰብ ሞዴል ውስጥ የገንቢ ትችት አካል መሆኑን የጠቆሙት ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ፣ ሃሳባቸውን ከር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሀሳብ ጋር በማዛመድ፣ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚል ርዕሥ የቀረበው የር. ሊ. ጳ . ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን  መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ እና ጭብጥ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።  ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን የሰው ልጅ በወንድማማችነት እና በማኅበራዊ ወዳጅነት ጎዳና ላይ እንዲጓዝ ትክክለኛ አማራጭ መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ አስረድተዋል። ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳኑ ከዚህም በተጨማሪ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አልፎ አልፎ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በአሁኑ ዓለም ውስጥ ሊታይ የሚችለውን የንቀት ባሕልን፣ ዘረፋን እና ብዝበዛን የሚያስከት ግለኝነትን እና የመገለልን ባሕልን የሚያመነጭ የጋራ ጉዳት ያገናዘበ መሆኑን አስረድተዋል።

ዓለምን ማዳን የሚችል እሴት

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በማለት ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ወንድማማችነትን እና የማኅበራዊ ወዳጅነት ህልምን እውን በማድረግ "በግል ደህንነት እና በሰው ልጆች ደስታ መካከል ያለውን ልዩነት" በማሸነፍ ዓለምን ከልዩ ልዩ ችግሮች ሊያድን የሚችል እሴት መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ አስረድተዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ አክለውም፣ እርስ በእርስ የመገናኘት ባሕልም፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ወጣቶች ወላጅ አልባ ሆነዋል የሚለውን የታላላቅ እሳቤዎች ባዶነት የሚሞላ እና ለሥነ-ምህዳር ጥያቄ ለመመለስ የሚያነሳሳ መሆኑንም ገልጸው፣ ወንድማማችነት፣ “ሰው አንድነትን ሊመሠርት አይችልም” የሚለውን የሊበራል አስተሳሰብን፣ እንደዚሁም የሰውን ልጅ ነጻነት ከሚገድብ ማርክሳዊ የአንድነት አስተሳሰብ ሊታደግ የሚችል አድማስ መሆኑን አስረድተዋል። ወንድማማችነት፣ በሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል ባለው ኅብረት ውስጥ የወንጌል መመስረትን የሚያመለክት "የመዳን መንገድ ነው” ብለው፣ የታሪክን እና የባሕል ሞዴሎችን ትርጉም እንደገና መግለጽ የሚችል፣ የሰብዓዊ ክብር ዋጋ የሚተረጎምበት የሕይወት ዘይቤ መሆኑን፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ጊዜያዊ ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ አስረድተዋል። 

31 March 2022, 16:03