ፈልግ

ካርዲና ፓሮሊን የዓለምን እጣ ፈንታ በእጃቸው የያዙት አካላት አስፈሪ ከሆነ ጦርነት ይጠብቁን አሉ!

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ጥቃት በኋላ የቫቲካን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፍ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ይፋ ባደረጉት መልእክት እንደገለጹት ከሆነ ጦርነቱ ለማስቆም "አሁንም ለበጎ ፈቃድ እና ለድርድር ጊዜ አለ" ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዩክሬን ያለው ቀውስ ወደ ግጭት ባደገበት ዕለት በቫቲካን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዩክሬን ባለው ቀውስ ውስጥ ከታዩት የዛሬ ለውጦች አንፃር፣ ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ያቀረቡት ግልጽ እና ልባዊ ተማጽኖ ወቅታዊ መሆኑን እናያለን። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ "ታላቅ ሀዘን" "ጭንቀት እና ስቃይ" ተናግረዋል። በተጨማሪም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት “በሕዝብ ላይ የከፋ መከራ ከሚያስከትል፣ በአገሮች መካከል ያለውን አብሮ መኖር ከሚያናጋና ዓለም አቀፍ ሕግን ከንቱ ከሚያደርጉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ” አሳስበዋል።

ይህ ጥሪ እና ተምጽኖ በዩክሬን ግዛት ውስጥ የሩሲያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ ነው። ሁሉም የሚፈሩት አሳዛኝ ሁኔታዎች እውን እየሆነ ነው። አሁንም ለበጎ ፈቃድ ጊዜ አለ፣ ለድርድርም ቦታ አለ፣ አሁንም ጥበብን መጠቀሚያ ቦታ አለ፣ የወገንተኝነት ጥቅም የበላይነትን መከላከል፣ የሁሉንም ሰው ህጋዊ ምኞት መጠበቅ፣ ዓለምን ከዚ አሰቃቂ እና ከአስፈሪው ነገር ለመታደግ ጦርነቱን ማቆም የግድ ነው።

አማኞች እንደ ምሆናችን መጠን የዓለምን ሀብት በእጃቸው በያዙ ሰዎች ላይ የህሊና ጭላንጭል ተስፋ አናጣም። እናም በመጪው ረቡዕ ዕለት የዐብይ ጾም በምንጀምረበት ወቅት ለዩክሬን እና ለመላው ዓለም ሰላም መጸለይ እና መጾም እንቀጥላለን።

25 February 2022, 12:38