ፈልግ

የመቁጠሪያ ጸሎት ማቅረብ የመቁጠሪያ ጸሎት ማቅረብ 

የተሰፋ ምልክቶች

የእምነት መጎልበት እና ተአምራዊው ፈተና፣ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ እና መንፈሳዊ ንባባት በሚሉ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ በማስተንተን ክቡር አቶ አንድሬያ ሞንዳ “ሎዜርቫቶሬ ሮማኖ” በተባለ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ኤዲቶሪያል አምድ ላይ አስተንትኗቸውን አስፍረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ኢየሱስም ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለበላችሁ እና ስለጠገባችሁ እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም (ዮሐ. 6፡26) ተብሎ የተጻፈውን ጥቅስ ያስታወሱት አቶ ሞንዳ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ዕብራዊያን በጻፈው መልዕክቱ በምዕ. 4፡12 ላይ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው እና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ስይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስን እና መንፈስን ጅማትን እና ቅልትምን እስኪለይ ድረስ የሚቆራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም አሳብ እና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።” የሚለውንም በመጥቀስ፣ በዚህ መልዕክቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሚያስቀምጠን ፣ በአንድ በኩል ምልክቶችን ፣ በሌላኛው በኩል ዳቦን ፣ በአንድ በኩል ለምልክቶች ያለንን ዕውርነት በሌላ በኩል ደግሞ ለቁሳዊ ነገሮች መራባችንን ይናገራል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐምሌ 25/2013 ዓ. ም. በየእሁዱ በሚያቀርቡት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ወቅት፣ በዕለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ንባብ ላይ በማስተንተን ባቀረቡት አስተምህሮአቸው፣ በምንባቡ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች የዳቦ መብዛቱ ተአምር ቢያዩም የምልክት ትርጉሙ ያልገባቸው መሆኑን ገልጸው፣ የምልክቱን ውጫዊ ገጽታ እና ቁሳዊ ዳቦነቱን ብቻ የተረዱ መሆናቸውን መግለጻቸውን አስታውሰዋል። ይህ ከሆነ እምነታቸው ከአንገት በላይ ብቻ መሆኑን እና ለ“ጣዖት አምልኮ ፈተና” ተገዥነታቸውን ያሳዩበት ነው በማለት ገልጸው፣ እግዚአብሔር የዕለት እንጀራን እንዲሰጠን የምንጠይቀው ረሃባችንን እንዲያስታግስልን፣ ከዚያም ስንጠግብ እርሱን እንረሳለን በማለት ያስተላለፉትን መልዕክት አቶ ሞንዳ አስታውሰው፣ ይህን በመሰለ ገና ባልዳበረ እምነት ውስጥ የሰዎች ፍላጎት እና ምኞት እንጂ እግዚአብሔር የሌለበት መሆኑን መናገራቸውን አስታውሰዋል።

በዚህ የእምነት አለመዳበር ውስጥ ከመጀመሪያው ጀምሮ ፈታኙ ሰይጣን አዳምን እና ሔዋንን፣ በአትክልቱ ውስጥ የሚገኙ ፍሬዎችን በሙሉ ቶሎ እንዲመገቡ፣ የፈጣሪው የቸርነት ምልክት መሆኑን እንዲረሱ፣ በኋላም ኢየሱስ ራሱ ድንጋዮችን ወደ እንጀራ እንዲለውጥ ሲሞግተው እንደነበር አስታውሰዋል። እንደምናውቀው የዚህ ፈተና ውጤት ነፃነትን ማጣት ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የመተማመን ስሜት በማጣት ለስብዕናችን የሚሰጠውን ክብር ማጣት መሆኑን አስረድተዋል። ዶስቶቭስኪ የተባለ ታላቁ የ15ኛው ክፍለ ዘመን ተመራማሪ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃያልነት በማስመልከት በገለጸው ሃሳቡ፣ የሰውን ነፃነት ለመውሰድ የሚችሉ ሦስት ኃይሎች መኖራቸውን ገልጾ እነርሱም ተአምር ፣ ምስጢር እና ስልጣን መሆናቸውን አስረድቷል።

“ሰዎች በተአምር ላይ ያላቸው እምነት አሻሚነት አስፈሪ ነው” ያሉት አቶ አንድሬያ ሞናዳ፣ በዮሐንስ ወንጌል ላይ “ተዓምራት” ብሎ ሚጠቅሰው በአጋጣሚ ሳይሆን “ምልክቶች” ከሚል ወሳኝ ቃል ቃል ጋር መቅረቡን ተናግረዋል። ዓለም በተለያዩ ምልክቶች የተሞላች መሆኗን ገልጸው፣ ዋናው ጉዳይ ምልክቶችን የማየት እና የመረዳት ችሎታ እንዲያድግ እና እንዲጎለብት የማድረግ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የፖላንዱ ባለቅኔ ቼስሎ ሚሎሽ ይህን ሁሉ በማስመልከት በግጥሙ ውስጥ ስለ ስሜት ሲናገር፣ “የዓለም ሽፋን” በሚል ትርጉም ገልጾታል። በተጨማሪም “ከወፍ ፣ ከተራራ ፣ ከፀሐይ መጥለቂያ በስተጀርባ” ተደብቆ የሚገኘውን እውነተኛ ትርጉም በማንበብ መፈለግ ያስፈልጋል ብሏል። ስናነበው መታረቅ የማይችል ነገር ይታረቃል፣ ለመረዳትም ያልተቻለው ግንዛቤን ሊያገኝ ይችላል ብሏል። ነገር ግን በሕይወት ዘመናችን አንብበን ትርጉሙን የማናስተውል ከሆነ እና በጥርጣሬ ውስጥ ብቻ የምንኖር ከሆነ አደጋ ተጋርጦብናል ማለት ነው በማለት ባለ ቅኔው አስረድቷል። ባለ ቅኔው በማከልም፣ ዓለም ምንም ሽፋን ከሌለው፣ በቅርንጫፉ ላይ የሚታየው ሽፍታ ምልክት ካልሆነ፣ በቅርንጫፉ ላይ የሚታየው ሽፍታ ምልክት ብቻ ከሆነ ፣ ለአንድ ትርጉም ትኩረት ሳይሰጡ  በምድር ላይ ምንም ነገር እንደሌለ የሚታሰብ ከሆነ ተስፋን በሚያስቆርጥ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚገባ ገጣሚውን ያስጠነቅቃል።

አንዳንዶች ዓይን እንደሚያታልል፣ ምንም ነገር እንደሌለ እና የምናየው መልክ ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ። እንዲህ የሚናገሩት ተስፋ የላቸውም። የሰው ልጅ ጀርባውን ከምርምር ካዞረ መላው ዓለም እንደ ሌለ እና በሌባ እንደተሰረቀ አድረገው ያስባሉ። የእግዚአብሔር ቃል ድክመታችንን አሸንፈን በተስፋ እንድንኖር ለሚያደርገን ይመስላል በማለት ባለ ቅኔው ተናግረው፣ አንድ ሰው ሲያምን ሕልም ሳይሆን ነገር ግን ሕያው አካል፣ ምድር መሆኑን አስረድተዋል። ምድርም ሕልም ሳትሆን ነገር ግን ሕያው አካል ናት ብለው፣ ምድርም የምትታይ፣ የምትጨበጥ፣ የምትሰማ፣ እና ልትዋሽም የማትችል መሆኗን አስረድተዋል።

የሚያውቋቸው ነገሮች ሁሉ እንደ አትክልት በአንድ መሠረት ላይ የቆሙ እንደሆነ ባለ ቅኔው መናገራቸውን አቶ አንድሬያ ሞንዳ “ሎዜርቫቶሬ ሮማኖ” በተባለ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ኤዲቶሪያል አምድ ላይ ባሰፈሩት አስተንትኗቸውን አካፍለዋል።

03 August 2021, 22:00