የቫቲካን ማዕከላዊ ባንክ የቫቲካን ማዕከላዊ ባንክ  (© Vatican Media)

ቫቲካን ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ባደረገችው ጥረት ተመሰገነች

ባለፈው የአውሮፓዊያኑ 2020 ዓ. ም ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራትን ለመከላከል የተደረጉት ጥረቶች መልካም ውጤት ማሳየታቸውን “Moneyval” የተባለ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት መርማሪ መሥሪያ ቤት አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ በተጨማሪም ወንጀሎቹ እንዳይፈጸሙ የሚያግዱ ደንቦችን፣ ተግባራዊ የሚሆኑ የቁጥጥር መንገዶችን እና ወንጀሎችን ለመከላከል ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ ባለሥልጣናት ጋር የነበሩ ትብብሮችን በዝርዝር መመልከቱን አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅድስት መንበር ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ እጅግ በጎ ውጤቶችን ካሳዩት አገራት መካከል የምትመደብ መሆኗን የቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን በ2020 ዓ. ም. ሪፖርቱ አረጋግጧል። ሪፖርቱ አክሎም ቅድስት መንበር ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራትን ለመከላከል ከአገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ ባለ ሥልጣናት ጋር መተባበሯን አስታውቋል። በአውሮፓዊያኑ 2020 ማረጋገጫዎችን ለማግኘት ጥረት የተደረጉባቸው 89 የተግባር ዘርፎች መኖራቸውን እና 16 ሪፖርቶች ወደ ፍትህ ጽ / ቤት መላካቸውን የቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን አክሎ አስታውቋል። ለቫቲካን ባለሥልጣን 49 የመረጃ ጥያቄዎች መቅረባቸውን፣ በ124 ግለሰቦች ላይ ፍተሻ መደረጉ ካለፈው ዓመት ጋር ሲታይ እድገት መታየቱ ወንጀልን ለመከላከል በቅድስት መንበር እና በቫቲካን ተቋማት መካከል ትብብር መኖሩን ያመለክታል ሲል የቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን አስታውቋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቀመጡ ውሎች መሠረት በቫቲካን ጽ/ቤቶች በተደረጉ ፍተሻዎች መልካም ትብብር መታየቱን ገልጾ፣ ከቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን በኩል ለቀረቡለት 58 የመረጃ ጥያቄዎች ቫቲካን  ከ196 ግለ ሰቦች ያሰባሰበችውን ምላሽ የሰጠች ሲሆን በ104 ግለሰቦች ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች 19 ፈጣን ምላሽ የሰጠች መሆኗን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ከፍተኛ እንቅስቃሴ የተደረገበት ዓመት

ያለፈው የአውሮፓዊያኑ 2020 ዓመት ከፍተኛ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የታየበት ቢሆንም የመረጃ ማሰባሰቡ ሥራ እንዲገታ ከተደረገበት እ. አ. አ ከኅዳር ወር 2019 ዓ. ም. በኋላ በጥር ወር 2020 ዓ. ም. ወደ ሥራ ተመልሶ የተገባበት መሆኑን የቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን አስታውቋል። ተጨማሪ የሰው ኃይል ተመድቦለት አዲሱ አስተዳደር ሲቋቋም በሚያዝያ ወር 2020 ዓ. ም ሥራውን የጀመረው የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት፣ የቁጥጥርና የሕግ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በማቋቋም የአወቃቀሩንና የአደረጃጀት ገጽታ አስተካክሎ በር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቋል። “Moneyval” በመባል የሚታወቅ እና ከአውሮፓ አገራት የተወጣጡ ከ30 በላይ አባላት ያሉበት ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራት መርማሪ ምክር ቤት፣ በቁጥጥር እና የገንዘብ መረጃ ባለስልጣን በኩል በቫቲካን ላይ ያደረገው የቁጥጥር ሚና ጥቃሚ መሆኑን የገምጋሚ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ካርሜሎ ባርባጋሎ አስታውቀዋል።

የ “Moneyval” ፍርድ አሰጣጥ

ባለፈው የአውሮፓዊያኑ 2020 ዓ. ም ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራትን ለመከላከል የተደረጉት ጥረቶች መልካም ውጤት ማሳየታቸውን “Moneyval” የተባለ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የሽብር ተግባራት መርማሪ መሥሪያ ቤት አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ በሪፖርቱ እንደገለጸው፣ ቅድስት መንበር እና የቫቲካን አስተዳደር ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና የሽብር ተግባራትን ለመከላከል በጋራ የሄዱበት አካሄድ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጾ፣ ቫቲካን ባደረገችው ጥረት ፍርድ እንዲሰጥበት በቀረቡለት አሥራ አንድ መስፈርቶች ውስጥ በ5ቱ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን እና 6ቱ አመርቂ የሚባሉ መልካም ውጤቶችን ማስገኘታቸውን የባለሞያዎች ኮሚቴ አረጋግጧል።

የጋራ ጥረቶች

የሽብር ተግባራት መርማሪ መሥሪያ ቤቱ ወንጀሎቹ እንዳይፈጸሙ የሚያግዱ ደንቦችን፣ ተግባራዊ የሚሆኑ የቁጥጥር መንገዶችን እና ወንጀሎችን ለመከላከል በቫቲካን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማት በጋራ ያደረጉት ጥረት ግልጽነት ያለው የትብብር ሥራ ውጤት መሆኑን ሪፖርቱ አስታውቋል። የፋይናንስ መረጃ ክፍሉ እንደገለጸው፣ ለፍትህ ቢሮ የተላከው ሪፖርት ካለፈው ዓመት ጋር ሲወዳደር ዕድገት ማሳየቱን ገልጾ፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በ 92 ኛው የፍትህ ዓመት መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ አርአያነት ያላቸው መልካም ልምዶች ፍጹም ግልፅነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ማሳሰባቸውን እና ይህም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዘንድ ባሉ እውነታዎች በኩል የሚገለጽ መሆኑን የፋይናንስ መረጃ ሪፖርት አመልክቷል።

15 July 2021, 16:02