በቫቲካን የብርታኒያ አባሳደር ሆነው የተሾሙት ሳሊ ጂን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እ.አ.አ በሰኔ 21/2021 ባቅረቡበት ወቅት በቫቲካን የብርታኒያ አባሳደር ሆነው የተሾሙት ሳሊ ጂን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እ.አ.አ በሰኔ 21/2021 ባቅረቡበት ወቅት  

አገሮቻቸውን በመወከል በቫቲካን የሚመደቡ የሴት አምባሳደሮች ቁጥር እያደገ መምጣቱ ተገለጸ!

በአሁኑ ወቅት አገሮቻቸውን በመወከል በቫቲካን በቅድስት መንበር የሚመደቡ ሴት አምባሳደሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየበዙ እንደ መጡ የተገለጸ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2020 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቤት ውስጥ የመቆየት አሰግዳጅ ሕግ በነበረበት ወቅት አገሮቻቸውን በመወከል በቫቲካን የቅድት መንበር ሴት አባሳደሮች በተለይም በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሴት ዲፕሎማቶች በበይነ መረብ አማካይነት ባለሙያዎችን በመመደብ የተለያዩ ውይይቶች እና ዝግጅቶች እንዲከናወኑ ማደረጋቸው ተገልጿል። ከአምባሳደሮች መካከል ሦስቱ በዚህ ክረምት ሮም ውስጥ የተሰጣቸውን ተልእኮ ሲያጠናቅቁ አውታረ መረቡ ግን መስፋፋቱን ቀጥሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሁሉም ነገር የተጀመረው WhatsApp ቡድን በመመሥረት የነበረ ሲሆን እ.አ.አ 2020 ዓ.ም በፀደይ ወቅት የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመግታት የጣሊያን መንግስት ባወጣው ጥብቅ በቤት ውስጥ የመቀመጥ ሕግ በተላለፈበት ወቅት በቅድስት መንበር የብሪታንያ አምባሳደር ሳሊ አክስየብልድ እና የካናዳዋ ባልደረባዋ ኢዛቤል ሳቫርድ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሌሎች 20 ሴት አባሳደሮች ጋር ሀሳቦችን መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ በማሰብ የጀመሩት ውይይት ሲሆን እነዚህ ሴት አባሳደሮች ደግሞ አገሮቻቸውን በመወከል በቫቲካን የተመደቡ አባሳደሮች ናቸው።

ብዙም ሳይቆይ በበይነ መረብ አማካይነት በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ብቃት ያላቸው እንግዶች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚሰሩ ባለሙያዎችን ለመጋበዝ ሀሳቡን አቀረቡ። ከተመረጡት ርዕሶች መካከል የአምባሳደሮቹን ቀልብ የገዛው የቅድስት መንበር ምላሽ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚለው አርእስት ሲሆን በተጨማሪም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ ምእመናን ሚና እና በቫቲካን ውስጥ የሴቶች ሃላፊነቶች እና አመለካከቶች በተመለከቱ አርዕስቶች ላይ ፍላጎት ነበራቸው።

የፖለቲካ ዓላማዎች አልተካተቱም

የሴት አምባሳደሮቹ አውታረ መረብ ግልጽ መደበኛ ያልሆነ ፣ ሕጎችን እና ደንቦችን የማይከተል፣ የምዝገባ ዝርዝርም ሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ ያላነገበ ውይይት እንደ ሆነ እየተገለጸ ሲሆን የፖለቲካ ስምምነቶችን ማድረግ ከዓላማዎቹ አንዱ አይደለም። ነገር ግን ሴት ዲፕሎማቶች ከእኩዮቻቸው ጋር የሚያደርጉትን የሐሳብ ልውውጥ የሚያበለጽግ ሆኖ ያገኙታል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ አንድ አምባሳደር እንዳሉት "ብዙ ነገሮች የሚመጡት ጥሩ መሆናቸውን ስለምታይ እና የበለጠ ስለሚዳብሩ ነው" ብለዋል። ነፃ በሆነ መልኩ በተሰነዘሩ ሐሳቦች ላይ ውይይት የሚያደርግ ቡድን ነው ብለዋል። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከባለሙያዎቹ ጋር የተደረጉ ስብሰባዎች እና ውይይቶች ጊዜ ተስጥቶዋቸው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን  ዲፕሎማቶቹ ራሳቸው ለክስተቶቹ የሚረዱ ሀሳቦችን አቅርበዋል - ብዙውን ጊዜ ውይይቶቹ ይደረጉ የነበሩት በሴት ባለሙያዎች ነበር። ስለሆነም ከቀናት በፊት በሮም ለአምባሳደሮች በተደረገ አቀባበል መስተንግዶ ላይ ከተገኙት ከ30 በላይ አባሳደሮች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እንደ ነበሩ የተገለጸ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሦስቱ ብቻ ወንዶች ነበሩ-ብዙውን ጊዜ በቅድስት መንበር አቀባበል ላይ የሚስተዋለው የሴቶች ዲፕሎማት በቁጥር ማነስ በአሁኑ ወቅት አስገራሚ ለውጥ እያስገኝ መምጣቱ ተገልጿል!

በቫቲካን የሴቶች አምባሳደሮች አጭር ታሪክ

የተለያዩ አገራትን በመወከል በቫቲካን የሚመደቡ የዲፕሎማሲ ቡድን ውስጥ ሴቶች ለረጅም ጊዜ ተወክለዋል። በቫቲካን የቅድስት መነበር ጽሕፈት ቤት የፕሮቶኮል ክፍል ለቫቲካን ዜና እንዳረጋገጠው በቅድስት መንበር የመጀመሪያዋ ሴት አምባሳደር ተደርገው የተመደቡት አንዲት ሴት አፍሪካዊት እንደ ነበረሩ የተገለጸ ሲሆን እ.ኤ.አ. ጥር 23/1975 ዓ.ም የቅድስት መንበር አምባሳደር ሆነው የተመደቡት የኡጋንዳዋ ወ / ሮ በርናዴቴ ኦሎዎ እንደ ነበሩ ተገልጿል። በመቀጠልም በመጀመሪያ ጥቂቶች ከዚያ በኋላ ደግሞ ብዙ ሀገሮች ሴት ዲፕሎማቶችን ወደ ቫቲካን መላክ ጀመሩ፣ የአፍሪካ ሴት ዲምሎማቶች ባለማቋረጥ አግሮቻቸውን ወክለው በቫቲካን እንደ ሚገኙ ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ 1980 ዓ.ም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መዛግብት እንደ ሚያመለክተው በቅድስት መንበር እውቅና ያገኘች አንዲት ሴት አምባሳደር የዛምቢያ አገር ተወላጅ ነበሩ።  እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓ.ም አምስት (ኮስታሪካ ፣ ጋና ፣ ጃማይካ ፣ ኒውዚላንድ እና ኡጋንዳ) ሴት ዲፕሎማቶች አገሮቻቸውን ወክለው በቫቲካን የቅድስት መንበር አባሳደሮች ሆኔው ተሹመው ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም በቫቲካን የሴቶች አምባሳደሮች ቁጥር ወደ ስምንት ማደጉ የተገለጸ ሲሆን እነዚህም ከፊሊፒንስ ፣ ሌሶቶ ፣ ኒካራጓ ፣ ፓናማ ፣ ፓራጓይ ፣ አሜሪካ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ዩክሬን የመጡ እንደ ነበረ ተገልጿል። እ.ኤ.አ በ 2010 ዓ.ም ቦስኒያ-ሄርዞጎቪና ፣ ቡሩንዲ ፣ ፊሊፒንስ ፣ ጋምቢያ ፣ ጆርጂያ ፣ ዮርዳኖስ ፣ ህንድ ፣ አይስላንድ ፣ ኔዘርላንድ ፣ ፓኪስታን ፣ ፓናማ ፣ ፖላንድ ፣ ሱሪናሜ ፣ ስዊድን ፣ ቱኒዚያ ፣ ዩክሬን የመጡ አስራ ስድስት ሴት አባሳደሮች ነበሩ። በመጨረሻም እ.ኤ.አ. በ 2021 ዓ.ም 26 ሴት አምባሳደሮች በቅድስት መንበር እውቅና ያገኙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አስራ ስድስት ቋም ሲሆኑ ሁለት ተጨማሪ ሴት ዲፕሎማቶች የዓለም አቀፍ ተቋማት ልዑካን ሆነው መሾማቸውም ተገልጿል። የቫቲካን የቅድስት መንበር ጽህፈት ቤት መረጃ መሠረት በአጠቃላይ አንድ መቶ ሰላሳ አምሳደሮች በቅድስት መንበር ዕውቅና የተሰጣቸው ናቸው።

የአውሮፓ አገሮች ሴት አምባሳደሮችን ወደ ቅድስት መንበር በመላክ ረገድ ተጠምደዋል- ኦስትሪያ ፣ ፈረንሳይ ፣ ታላቋ ብሪታንያ ፣ ኔዘርላንድስ ፣ እስፔን ፣ ስዊድን ፣ ኢስቶኒያ ፣ ላቲቪያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት በአሁኑ ወቅት ሴት ዲፕሎማቶች በቅድስት መንበር እያገለገሉ ይገኛሉ።

ከኪያራ ፖሮ በመቀጠል አውስትራሊያ ሁለተኛዋን ሴት አባሳደሯን ወደ ቫቲካን ልካለች። በተመሳሳይ መልኩም ፊሊፒንስ እና ግሪክ በመከተል ሴት አባሳደሮቻቸውን ወደ ቫቲካን ልከዋል። እንዲሁም አሜሪካ በተከታታይ ሴት አባሳደሮቿ አገሪቷን ወክለው በቫቲክን የቅድስት መነበር ዲፕሎማቶች እንዲሆኑ ልካለች።

ሮም ውስጥ ከሚገኙ ሴት ዲፕሎማቶች መካከል ሦስቱ በዚህ ክረምት የወቅቱን ሥራቸውን እና ተልዕኮዎቻቸውን አጠቃለው ወደ አገሮቻቸው ይመለሳሉ፣ እነዚህም ኢዛቤል ሳቫርድ ከካናዳ ፣ ሳሊ አክስብላንድ ከእንግሊዝ እና ማሪያ ኤላቪራ ቬላስኬዝ ሪቫስ-ፕላታ ከፔሩ ናቸው። ሆኖም መደበኛ ያልሆነ የሴት አምባሳደሮች አውታረ መረብ መስራቱን እና ማደጉን ይቀጥላል። አግሮቻቸውን ወክለው በቫቲካን የቅድስት መንበር ሴት አባሳደሮች በአሁኑ ወቅት በበይነ መረብ አማካይነት የሚያደርጉት ስብሰባ የድህረ-ወረርሽኙ ሁኔታዎች የሚፈቅዱ ከሆነ በበይነ መረቦች ከሚከናወነው ከምናባዊ ስብሰባዎች ይልቅ ፊት ለፊት ተገናኝቶ ስብሰባዎችን እና ዝግጅቶችን ማደረግ እጅግ በጣም ተመራጭ በመሆን በቅርቡ ወደ እዚያው እንደ ሚሻገር ይጠበቃል።

07 July 2021, 15:38