ሴቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከሚያደርጉት ጥረቶች መካከል ሴቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከሚያደርጉት ጥረቶች መካከል 

ሴቶች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚችሉ ብርቱ ተዋናይ መሆናቸው ተገለጸ

“ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚለውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳንን መሠረት ያደረገ እና ሴቶች ሁሉ አቀፍ ዕድገትን፣ ባሕልን እና እንክብካቤን በማሳደግ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው የሚወያይ የመጀመሪያው የአውታረ መረብ ላይ አውደ ጥናት መካሄዱን በቫቲካን የአካባቢ ጥበቃ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ቢሮ አስተባባሪ የሆኑት የወ/ሮ ኪያራ ማርቲኔሊ አስታወቁ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሴቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የተቀበሉትን የመሪነት ሚናን በመጠቀምሁለገብ ዕድገትን ለማምጣት  የሚችሉ መሆናቸው ተገለጸ። “ምግብ ለሕይወት” በሚል ርዕስ ሁለገብ ዕድገትን ለማምጣት ሴቶች በሚጫወቱት ሚና ላይ የሚወያይ የአውታረ መረብ ላይ ውይይት ከግንቦት 8 - 16/2013 ዓ. ም ድረስ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል። ውይይቱ እ. አ. አ በ2021 ዓ. ም ለሚካሄድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ገንቢ ሃሳቦችን ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ታውቋል። በውይይቱ ላይ የሚሳተፉት ከቅድስት መንበር ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት፣ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት፣ በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ እና በዓለም ምግብ ፕሮግራም የቅድስት መንበር ቋሚ መልዕክተኛ፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ተውካይ እና በቫቲካን የአካባቢ ጥበቃ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ቢሮ ተወካዮች የሚሳተፉ መሆናቸው ታውቋል።

ሁሉ አቀፍ አመለካከት ሊኖር ያለው

“ምግብ ለሕይወት” በሚል ርዕስ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” ሳምንት በሚከበርበት ማለትም ከግንቦት 8 - 16/2013 ዓ. ም ድረስ የሚካሄደው ውይይት ዋና ዓላማ የአካባቢ ጥበቃን በማሳደግ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ለዓለም ሕዝብ በቂ የዕለት ምግብን ለማቅረብ የሚያግዙ ሃሳቦችን ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ታውቋል። ይህን ዓላማ መሠረት በማድረግ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች ተዋናዮችም የሚችሉትን አስተዋጽኦን እንዲያበረክቱ፣ የጋራ መኖሪያ ምድራችንን ከጥፋት ለመታደግ፣ የጋራ ጥቅምን እና ሰብዓዊ ክብርን በጠበቀ መልኩ በማኅበረሰቡ መካከል የሚታይ መገለልን በማስወገድ የሰው ልጅን በሙሉ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ታውቋል።

በቫቲካን የአካባቢ ጥበቃ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ቢሮ አስተባባሪ የሆኑት የወ/ሮ ኪያራ ማርቲኔሊ እንደገለጹት፣ ቅድስት መንበር እና በርካታ ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን ተዋናዮች በቂ የዕለት ምግብን ለማቅረብ የሚያግዙ ሃሳቦችን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ለማቅረብ ፍላጎታ ያላቻአው መሆኑን አስረድተዋል። በቫቲካን የአካባቢ ጥበቃ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ቢሮ አባላት እንደመሆናችን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳንን መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሴቶች ለዚህ የመወያያ መድረክ በርካታ ገንቢ ሃሳቦችን ማካፈል እንደሚችሉ የገለጹት ወ/ሮ ኪያራ ማርቲኔሊ በቂ የምግብ ዋስትና እጦት በሴቶች ላይ ከፍተኛ ችግር ማስከተሉን ጠቅሰው፣ ችግሩ በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በተቀረው የማኅበረሰብ ክፍልም ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ የውይይቱ ዓላማ ፍትሃዊ የሆነ በቂ የምግብ ዋስናን ለማረጋገጥ እና ሴቶች የአካባቢ ጥበቃን በማሳደግ በቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። ሴቶች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጠረት ፍሬያማ ለማድረግ በውይይቱ ላይ የሚሳተፉ እና በዓለማችን በእርሻው ምርት ዘርፍ ከተሳተፉ ድርጅቶች የሚነገሩ ልምዶችን ማድመጥ አስፈላጊ መሆኑን   ወ/ሮ ኪያራ ማርቲኔሊ ገልጸዋል።               

18 May 2021, 16:15