ቫቲካን የረመዳን ፆም ሲጀመር ለሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፋለች።
በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት መላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በቅርቡ የጀመሩትን የረመዳን ፆም ወር ምክንያት በማደረግ አጋርነት እና ወዳጅነትን ለመግለጽ ለሁሉም ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ማስተላለፉ ተገለጸ።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
“ለሁሉም ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች” ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ይፋ ባደርገው መልእክት ይህ የረመዳን ፆም ወቅት “በመለኮታዊ በረከቶች እና በመንፈሳዊ እድገት የበለፀበ ወር ይሆን ዘንድ ወንድማዊ የሆነ መልካም ምኞቶችን” በማስተላለፍ ይጀምራል። መልዕክቱ “ከጾም ፣ ከጸሎት ፣ ከምጽዋት እና ከሌሎች ጥሩ ልምዶች ጋር ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ አብረን የምንኖርባቸው እና የምንሰራባቸው ሰዎች ሁሉ እንድንቀርብ የሚያደርገን ከመሆኑም በላይ በወንድማማችነት ጎዳና ላይ አብረን እንድንጓዝ ይረዳናል” ብሏል።
የሚያጽናኑ ምልክቶች
ባለፉት ጥቂት ወራቶች “በመከራ ፣ በጭንቀት እና በሐዘን” በተለይም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በቤት ውስጥ ተቆልፈን በቆየንባቸው አስቸጋሪ ጊዜያት “መለኮታዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገን ተገንዝበናል ፣ በተጨማሪም ለወንድማማችነት አብሮነት መገለጫዎች እና ምልክቶች” ማሳየት እንደ ሚገባንም ተገንዝበናል በማለት በመልእክቱ ገልጿል። በጣም ብዙ ትናንሽ ምልክቶች አሉ በማለት በመልእክቱ የገለጸው በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት መልዕክቱን ሲቀጥል -የስልክ ጥሪ ፣ የድጋፍ እና የመጽናናት መልእክት ፣ ጸሎት ፣ መድኃኒቶችን ወይም ምግብን በመግዛት እገዛ ማድረግ፣ ምክር በመስጠት፣ አንድ ሰው ሁል ጊዜ ለእኛ ቅርብ እንደ ሆነ ሰዎች እንዲያውቁ ማደረግ” በራሱ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ተግባር ነው ብሏል።
ይህ የምንመኘው እና የምንፈልገው መለኮታዊ እርዳታ “ብዙ ነው” በማለት በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የእግዚአብሔር ምህረት ፣ ይቅርታ ፣ አቅርቦት እና ሌሎች መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ስጦታዎች እንደ ሚያካትት የገለጸ ሲሆን "ሆኖም በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በጣም የምንፈልገው ነገር ተስፋ ነው" ብሏል።
ተስፋ
መልእክቱ ከዚያ በኋላ ትኩረቱን ወደ “ተስፋ” አስፈላጊነት ያዞራል። “እንደምናውቀው እርግጠኛ መሆን ብሩህ ተስፋን ይጨምራል” ተስፋ ከእዚያ ባሻገር የሚጓዝ ነገር ነው በማለት በመልእክቱ የገለጸው በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት መልእክቱን ሲያብራራ "ብሩህ አመለካከት የሰዎች አመለካከት ቢሆንም ተስፋ ግን በሃይማኖታዊ ነገር ውስጥ መሠረት አለው-እግዚአብሔር ይወደናል ስለዚህ እርሱ በአስተማማኝነቱ ይንከባከበናል" ብሏል።
ምንም እንኳን ለእነሱ ምክንያቱን መረዳቱ ወይም ከእነሱ የምንወጣበት መንገድ መፈለግ ለእኛ አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ሊሆን ቢችልም ቅሉ ተስፋ የሚነሳው ሁሉም ችግሮቻችን እና ፈተናዎቻችን ትርጉም ፣ እሴት እና ዓላማ እንዳላቸው ካመንን ብቻ ነው በማለት በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በመልእክቱ አክሎ ገልጿል።
"ተስፋም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ባለው መልካምነት ላይ እምነትንም ያገኛል። ብዙ ጊዜ በችግር እና በተስፋ መቁረጥ ሁኔታዎች ውስጥ፣ እርዳታ እና የሚያመጣው ተስፋ እኛ ካልጠበቅናቸው ሰዎች ሊመጣ ይችላል" በማለት በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ገልጿል።
ወንድማማችነት ፣ የተስፋ ምንጭ ነው
መልእክቱ በመቀጠልም “የሰው ልጅ ወንድማማችነት በብዙ መገለጫዎቹ ውስጥ በመሆኑ ለሁሉም ፣ በተለይም በማንኛውም ዓይነት ፍላጎት ውስጥ ላሉ ሁሉ የተስፋ ምንጭ ይሆናል በማለት በመልእክቱ የገለጸው በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በችግር ጊዜ እጅግ በጣም ብቸኛ ለሆኑት ሰዎች አጋርነታቸውን እየገለጹ ላሉ ሰዎች ሁሉ ምስጋና እናቀርባልን” ብሏል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች እና የእነሱ መልካምነት የወንድማማችነት መንፈስ ዓለም አቀፋዊ መሆኑን እና ሁሉንም ድንበሮች የሚያልፍ መሆኑን አማኞችን ያስታውሳል በማለት በመልእክቱ የገለጸው በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት “ይህንን መንፈስ በመቀበል በፈጠራቸው የሰው ልጆች ፣ በሁሉም ፍጥረታት እና በመላው አጽናፈ ሰማይ ላይ በቸርነት የሚመለከተውን እግዚአብሔርን እንመስላለን” የሚለውን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተስፋ መልእክት በመጥቀስ በመልእክቱ አካቶ አቅርቧል።
የተስፋ ጠላቶችን መዋጋት
በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የረመዳን የፆም ወቅትን አስመልክቶ ለመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች ባስተላለፈው መልዕክት “እኛም ተስፋ ጠላቶች እንዳሉት እናውቃለን” በማለት የገለጸ ሲሆን "በእግዚአብሔር ፍቅር እና እንክብካቤ ላይ እምነት ማጣት ፣ በወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እምነት ማጣት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና ተቃርኖዎች፣ መሠረተ ቢስ ግምት ፣ በራስ አሉታዊ ልምዶች ላይ በመመርኮዝ ኢ-ፍትሃዊ አጠቃላይ መግለጫዎች እና የመሳሰሉት" ሁሉም የእምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል። በእግዚአብሔር ላይ ተስፋን ለማጠናከር እና በሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እምነት ለመጣል እነዚህን ጎጂ አስተሳሰቦች ፣ አመለካከቶች እና ምላሾች በብቃት ማስወገድ ይኖርብናል በማለት አክሎ ገልጿል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ተስፋችንን እንድናድስ ያቀረቡት ግብዣ
በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት መልእክቱን ያጠቃለለው በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጣሊያነኛ ቋንቋ “ፍራቴሊ ቱትቲ” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) በሚል አርዕስት ያፋ ያደረጉትን ጳጳሳዊ መልእክት በማጣቀሻነት በመጠቀም ሲሆን “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስለ ተስፋ ደጋግመው ይናገራሉ” ብሏል። በእዚህ ጳጳሳዊ መልእክት ውስጥ “እያንዳንዱ ሰው ያለውን ተስፋ እንዲያድስ እጋብዛለሁ’ ተስፋ ከሁኔታዎቻችን እና ከታሪካዊ ሁኔታችን ገለልተኛ በሆነ መልኩ በሁሉም የሰው ልብ ውስጥ ስር የሰደደ ነገር ይነግረናልና። ተስፋ ስለ ጥማት ፣ ስለ ምኞት ፣ ስለ ፍፃሜ ሕይወት ናፍቆት ፣ ታላላቅ ነገሮችን ለማሳካት መሻትን ፣ ልባችንን የሚሞሉ እና መንፈሳችንን ከፍ ወዳለ እውነታዎች ፣ እንደ እውነት ፣ ጥሩነት እና ውበት ፣ ፍትህ እና ርኅራኄ… እና ህይወትን የበለጠ ቆንጆ እና ዋጋ ያለው ለማድረግ እንችል ዘንድ ተስፋ ታላላቅ ሀሳቦች ሊከፍትልን ይችላል'። በተስፋ ጎዳናዎች ላይ ወደፊት መራመዳችንን እንቀጥል” ማለታቸውን መልእክቱ አስታውሷል።
በመጨረሻም መልዕክቱ “እኛ ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች የተስፋ ተሸካሚዎች እንድንሆን ፣ ለአሁኑ ህይወት እና ለሚመጣው ህይወት ፣ እንዲሁም ምስክሮች ፣ የዚህ ተስፋ ተስፋ ሰጪ እና ገንቢዎች እንድንሆን የተጠራን ሲሆን በተለይም ችግር ላለባቸው እና ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች ተስፋቸውን መልሰው እንዲጎናጸፉ ማደረግ ይኖርብናል” በማለት በመልእክቱ ማጠቃለያ ላይ የገለጸው በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እናም በመንፈሳዊ አንድነት ምልክት ላይ ተመርኩዘን የምናደርገውን “ፀሎታችንን እናረጋግጥልዎታለን ፣ እናም ሰላማዊ እና ፍሬያማ የሆነው የረመዳን ወቅት እንዲሆንላችሁ እንዲሁም በደስታ የታጀበ ‘የኢድ አልፈጥር ’በዓል ታከብሩ ዘንድ መልካም ምኞቶቻችንን እንገልጽላችኋለን” በማለት በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማ መካከል የሚደርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት መልእክቱን አጠናቋል።