“ባምቢኖ ጀሱ” የሕጻናት ሆስፒታል ያልተለመዱ በሽታዎች ግኝት ዓለም አቀፍ ቀን “ባምቢኖ ጀሱ” የሕጻናት ሆስፒታል ያልተለመዱ በሽታዎች ግኝት ዓለም አቀፍ ቀን 

“ባምቢኖ ጄሱ” የሕጻናት ሆስፒታል፣ አራት አዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች ማግኘቱን አስታወቀ

በቅድስት መንበር የሚተዳደር እና “ባምቢኖ ጄሱ” በመባል የሚታወቅ ታዋቂው የሕጻናት ሆስፒታል ከቅርብ ጊዜት ወዲህ ባካሄደው ምርምር አዳዲስ በሽታን ሊያስከትሉ የሚችሉ አሥራ ሶስት ሕዋሳትን ለይቶ ማግኘቱን አስታውቋል። የምርምሩ ዓላማ ከዚህ በፊት ታይተው በማይታውቁ የበሽታ ዓይነቶች የሚሰቃይ የቤተሰብ ቁጥር ለመቀንስ እና የምርምር ውጤቶችን ለማሳደግ መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እሑድ የካቲት 21/2013 ዓ. ም. በሮም ከተማ በሚገኝ “ባምቢኖ ጀሱ” የሕጻናት ሆስፒታል ያልተለመዱ በሽታዎች ግኝት ዓለም አቀፍ ቀንን በድምቀት የሚያከብር መሆኑ ታውቋል። የሕጻናት ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በስፋት በተዛመተበት በዚህ ወቅት በርካታ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱ ታውቋል። ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከዚህ በፊት በምርምር ያልተገኙ አራት የተለያዩ የበሽታ ዓይነቶችን ለይቶ ማግኘቱ ታውቋል። እነዚህ አዲስ ተገኙ የተባሉት በሽታዎች የሕጻናትን የጀርባ አጥንት ዕድገት የሚጎዱ እና ሌሎች ከኔርቭ እድገት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሦስት የሕመም ዓይነቶችን የሚያስከትሉ መሆናቸው ታውቋል። በእነዚህ ምርምሮች የተገኙት ውጤቶች እ.አ.አ. በ2020 ዓ. ም. የተገኙትን ጠቅላላ የምርምር ውጤቶችን ቁጥር ወደ አሥራ ሶስት ማድረሱ ታውቋል።

ለአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች የሚውል የምርምር ዕቅድ

በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኝ “ባምቢኖ ጄሱ” የሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ የተደረጉት ምርምሮች እስካሁን ባልታወቁ የበሽታ ዓይነት በሚሰቃዩ ሕሙማን ላይ መካሄዳቸው ታውቋል። ምርምሮቹን ለማካሄድ የተለያዩ ድርጅቶች ዕርዳታ ማድረጋቸው ሲታወቅ፣ የጣሊያን መንግሥት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም በእርዳታው መርሃ ግብር ከተሳተፉት መካከል አንዱ መሆኑ ታውቋል።

ለቤተሰቦች በቂ ምክር መስጠት

“በባምቢኖ ጄሱ” የሕጻናት ሆስፒታል የዘረ-መል እና የአዳዲስ በሽታዎች ምርምር አስተባባሪ የሆኑት አቶ ማርኮ ታርታሊያ እንዳስረዱት፣ ለእያንዳንዱ ታካሚ የሚደረግ ምርመራ የሚጀምረው ለተወሰኑ ሕመሞች ሊሰጥ የታለሙ ሕክምናዎችን ለመጀመር የሚያስችን ሁኔታ ሲመቻች ብቻ መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህም በተጨማሪ በሕመሙ ለሚሰቃዩ ቤተሰቦች በቂ የምክር አገልግሎት መስጠት የመርምሩ አካል መሆኑን አስረድተዋል። በአዲስ የበሽታ ዓይነት ለሚሰቃይ ሕጻን ምርመራን የማድረግ ዕቅድ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ ያለተለመደ መሆኑን ያስረዱት አቶ ማርኮ፣ ይህ እቅድ ለወላጅ ቤተሰብም ጭምር ትልቅ ዕድል መሆኑን አስረድተዋል። አቶ ማርኮ በማከልም፣ በምርምሩ ሂደት ላይ በሕዋሳቱ ላይ አዲስ ለውጥ መታየቱን ለይቶ ማወቅ፣ ውጤታማ የሆኑ ምርምሮችን ለማካሄድ እና ወደ ታቀደው ግብ በመድረስ ትክክለኛውን መድኃኒት ለማግኘት ያግዛል ብለዋል።

የምርምር ውጤቶችን ማሳደግ ያስፈልጋል

በአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች ላይ ምርምሮችን በማካሄድ መልካም ውጤቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማስመዝገብ የታማሚ ሕጻናት እና ቤተሰብ ቁጥርን ለመቀነስ መሆኑን የገለጹት አቶ ማርኮ፣ በምርምሩ ላይ የሚሳተፉት የተለያዩ የሕጻናት ሕክምና መስጫ ተቋማት በወር ሁለት ጊዜ ተገናኝተው በመወያየት፣ ጠቃሚ ግኝቶችን የሚለዋወጡ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ የውይይት መንገድ 58 ከመቶ የሚሆኑ ሕሙማን በመርሃ ግብሩ እንዲጠቀሙ ማደረጉን አስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት 40 ሺህ መርመራዎች ተካሂደዋል

ባለፉት ሰባት ዓመታት የ “ባምቢኖ ጄሱ” የሕጻናት ሆስፒታል፣ በአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች ላይ ባደረገው ምርመራ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ አዳዲስ የዘረ-መል በሽታ ዓይነቶች መገኘታቸው ታውቋል። “ባምቢኖ ጄሱ” የሕጻናት ሕክምና መስጫ ሆስፒታል በአገር ደረጃ በአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች ላይ ሰፊ ምርምሮችን የሚያካሂድ መሆኑ ሲታወቅ፣ ባሁኑ ጊዜ በቁጥር ከ15 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የሕክምና አገልግሎት በማድረግ ላይ መሆኑ ታውቋል። ሆስፒታሉ ከዚህም በተጨማሪ በአውሮፓ ውስጥ በአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች ጥናት በማድረግ የምርምር ውጤቶቻቸውን ከሚጋሩት 15 ከፍተኛ የሕክምና ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑ ታውቋል። እ.አ.አ. ከ2016 ዓ. ም. ጀምሮ በአዳዲስ የበሽታ ዓይነቶች የሚሰቃዩ ሕሙማንን ተቀብሎ የሕክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥበት ልዩ ማዕከል በማደራጀት 40 ሺህ ምርምሮችን ያካሄደ መሆኑ ታውቋል።

25 February 2021, 13:25