ካርዲናል ካንታላሜሳ በቫቲካን የስብከተ ገና አስትንትኖዎችን ለማድረግ ተዘጋጁ ካርዲናል ካንታላሜሳ በቫቲካን የስብከተ ገና አስትንትኖዎችን ለማድረግ ተዘጋጁ  

ካርዲናል ካንታላሜሳ በቫቲካን የስብከተ ገና አስትንትኖዎችን ለማድረግ ተዘጋጁ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመና ዘንድ አሁን የምንገኝበት ወቅት የስብከተ ገና ወቅት እንደ ሆነ ይታወቃል።በዚህ በሕዳር 20/2013 ዓ.ም በተጀመረው የስብከተ ገና ወቅት ተገቢ የሆነ መንፈሳዊ ዝግጅት ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ በሆኑት እና በቅርቡ የካርዲናለት ማዕረግ የተሰጣቸው ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ ከሕዳር 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን የስብከተ ገና ወቅት አስመልክተው ተከታታይ ስብከቶችን ማደረግ እንደ ሚጀምሩ ተገልጿል። አሁን ያለንበትን የካሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት ማሕበራዊ ርቅት መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ የተነሳ ስብከቶቹ የሚደረጉት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ እንደ ሆነም ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ከወጣው መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው የእዚህ አመት ለስብከተ ገና ወቅት የሚጀምረው በሕዳር 25/2013 ዓ.ም እንደ ሆነ ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የስብከተ ገና ወቅት አስመልክቶ በሚደርገው መንፈሳዊ ዝግጅት ላይ ተሳታፊ እንደ ሚሆኑ ተገልጿል፣ በዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት ላይ አስተንትኖ የሚያቀርቡት ደግሞ በቅርቡ የካርዲናልነት ማዕረግ የተሰጣቸው እና የካፑቺን ማሕበር አባል የሆኑት በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ የሆኑት ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ መሆናቸው ተገልጿል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የካፑችን ማሕበር አባል ይሆኑ ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ እ.አ.አ ከ1980 ዓ.ም ጀምረው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ  ለእዚህ አመት የስብከተ ገና ወቅት የመረጡት መሪ ቃል “ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን” (መዝሙር 90፡12) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ እንደ ሚሆን ተገልጿል።

ካርዲናል ካንታላሜሳ አሁን ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ለሦስት የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት ሰባኪ ሆነው አገልግለዋል። ካርዲናል ሪኔሮ ካንታላሜሳ ሰሞኑን ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደ ገለጹት በእነዚህ አርባ አመታት ውስጥ ባጋጠማቸው ተሞክሮ እና ልምድ ላይ የበኩላቸውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን “እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፣ ወይም ቤኔዲክቶስ 16ኛ እና  እንድሁም እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለእኔ ደካማ እና ምስኪን የካፑቺን ማሕበር አባል የሆንኩኝ እኔን ተራ ካህን ለማዳመጥ ጊዜ ያገኛሉ ብለዬ ማሰብ ለእኔ ከባድ ነበር፣ መልካም ምሳሌ ስጥተውኛል፣ ለአምላክ ቃል ያላቸው አክብሮት ምሳሌ ለመላው ቤተ ክርስቲያን ሰጥተዋል። በተወሰነ መልኩ የምሰብከው እኔ ሳልሆን እነሱ ነበሩ እኔን የሚሰብኩኝ” ማለታቸው ይታወሳል።

በዚህ የስብከተ ገናን ወቅት በማስመልከት በሚደርገው መንፈሳዊ ዝግጅት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት የሚኖሩ ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የተጋበዙ ሲሆን የህንን የስብከተ ገና ወቅት አስመልክቶ ሦስት ዝግጅቶች እንደ ሚከናወኑ ተገልጿል።

02 December 2020, 13:31