ካርዲናል ካንታላሜሳ በቫቲካን የስብከተ ገና አስትንትኖዎችን በማድረግ ላይ ባልበት ወቅት የሚያሳይ ምስል ካርዲናል ካንታላሜሳ በቫቲካን የስብከተ ገና አስትንትኖዎችን በማድረግ ላይ ባልበት ወቅት የሚያሳይ ምስል  

ካርዲናል ካንታላሜሳ “ሞት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያሸጋግረን ድልድይ ነው” አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመና ዘንድ የስብከተ ገና ወቅት በሕዳር 20/2013 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የስብከተ ገና ወቅት ተገቢ የሆነ መንፈሳዊ ዝግጅት ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ በሆኑት እና በቅርቡ የካርዲናለት ማዕረግ የተሰጣቸው ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ ከሕዳር 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን የስብከተ ገና ወቅት አስመልክተው ለእዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዝግጅት ይሆን ዘንድ በየሳምንቱ ዘወትር ዓርብ እለት አስተንትኖ ማደረግ መጀመራቸው ተገልጿል። አሁን ያለንበትን የካሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት ማሕበራዊ ርቅት መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ የተነሳ በእዚህ ዓመት የስብከተ ገና ወቅት በካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ አማካይነት የሚደርገው አስተንትኖ የሚከናወነው በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ እንደ ሆነም ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የስብከተ ገና ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በቫቲካን የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቄሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ በሆኑት እና በቅርቡ የካርዲናለት ማዕረግ የተሰጣቸው ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ አማካይነት የሚሰጠው አስተንትኖ ዘወትር ዓርብ የሚደርግ ሲሆን የመጀመርያ አስተንትኖ በሕዳር 25/2013 ዓ.ም በተከናወነበት ወቅት የአስተንትኖ ትኩረት ከሕይወት በኋላ ስላለው ሞት ትርጉም ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ “ሞት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያሸጋግረን ድልድይ ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ ለእዚህ አመት የስብከተ ገና ወቅት አስተንትኖ የመረጡት መሪ ቃል “ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን” (መዝሙር 90፡12) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደ ነበረም ተገልጿል። ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ አስተንትኖዋቸውን ማደረግ የጀመሩት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጣሊያናዊው ባለቅኔ በተጻፈው ባለ 10 ቃል ግጥም በመጠቀም ሲሆን ይህም ግጥም “እኛ በበልግ  ወቅት በዛፎች ላይ እንዳሉት ቅጠሎች እኛ ነን” የሚለውን ጥቅስ በመጠቀም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያስከተለው ስቃይ የሰው ልጆች ብቻቸውን ለመጋፈጥ ስለሚከብዳቸው የፈጣሪ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ እንዳሉት የዓለም ወቅታዊ ችግር የሰው ልጆች ደካማ በመሆናቸው የተነሳ ብቻቸውን መጋፈጥ እንደማይችሉ ያሳየ ክስተት እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ይህንን ከፍተኛ የሆነ የአለማችንን ተግዳሮት መጋፈጥ የምንችለው በእምነታችን ላይ መሰረቱን ባደረገ መንፈሳዊ ኃይል ጭምር ነው ብለዋል።

ለሕይወት የሚሆን ትምህርት

ሞት በሁለት የተለያዩ መንገዶች ሊነገር ይችላል - በክርስቶስ የሕይወት መዳን እና ትንሣኤ ወይም በጥበብ ብርሃን በማለት በአስተንትኖዋቸው የተናገሩት ካርዲናል ካንታላሜሳ ሁለቱም ለሰው ልጅ የሚያስተምሩት ነገር አላቸው ብለዋል። የመጀመርያው  በእንግሊዘኛ ቋንቋ (kerygma) በግሪክ ቋንቋ ኬሪጋማ (በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም ጮክ ብሎ ማወጅ፣ መስብከ፣ መናገር የማቴዎስ ወንጌል 3፡1-3 የመልከቱ) የተሰኘው እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ሞት የህልውናን መጨረሻ የሚገልጽ ግድግዳ ሳይሆን “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያሸጋግር ድልድይ” መሆኑን ያሳየናል ብለዋል።

ሁለተኛው ደግሞ በቅልጥፍና የተሞላ ወይም በጥበብ ላይ ያተኮረ አመለካከት እንደ ሆነ የገለጹት ካርዲናል ራኔሮ ካንታላሜሳ ከሞት የሰው ልጅ ተሞክሮ በመልካም ሕይወት ለመኖር የሚያስችሉ ትምህርቶችን እንድንወስድ ያስችለናል ብለዋል።

የራሳችንን ሞት ማስታወስ

ካርዲናል ካንታላሜሳ በእዚህ የስብከተ ገና ወቅት የመጀመርያው ስብከታቸው ትኩረት ያደረጉት በሞት ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የትራፒስት ማሕበር መነኮሳት ሁልጊዜ የሚጠቀሙበትን የማሕበራቸውን ዋና መሪ ቃል የሆነውን በላቲን ቋንቋ Memento mori” ወይም በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም “ሟች እንደሆናችሁ አስታውሱ” በሚለው የጥበብ እይታ ላይ አድማሱን ያደረገ አስተትኖ እንደ ነበረ ተገልጿል።

የብሉይ ኪዳን የጥበብ መጻሕፍት እንዲሁም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ በቤተክርስቲያን ባህል በተለይም በበረሃ ውስጥ የሚኖሩ አባቶች በሰጧቸው አስተንትኖዎች ውስጥ መረዳት እንደምንችለው የሰው ልጅ ሞት ጭብጥ ሰፋ ያለ ነፀብራቅ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል ማለት “ጠዋት ላይ እስከ ምሽት ድረስ እንደ ማትቆይ ማሰብ ነው። አንድ ጊዜ ከመሸ በኋላ ደግሞ የሚቀጥለው ቀን ጠዋት አያለሁ ብለህ አትመካ” የሚለው ማሰሰቢያ እንደ ሆነ ካርዲናል ካንታላሜሳ የገለጹ ሲሆን አስከፊ በሆነ መልኩ አሁን ባለንበት ሕይወት ተማርከን ከመኖር ይልቅ ሟች መሆናችንን ማሰላሰላችን ወደ “የዘላለም ሕይወት እምነት” ሊመራን ይችላል ብለዋል።

በወረርሽኝ የተደገፉ ነጸብራቆች

ካርዲናል ካንታላሜሳ አስተንትኖዋቸውን በቀጠሉበት ወቅት አሁን በተከሰተው ወረርሽኝ መካከል አንዳንድ ትምህርቶችን መማር እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን “በእህት ሞት ትምህርት ቤት” ውስጥ እራሳቸውን እዲያስገቡ ታዳሚዎችን ጋብዘዋቸዋል። “አሁን ያለው በኮርኖና ቫይረስ ምክንያት የተከሰተው መከራ‘ እቅድ ማውጣትና የወደፊቱን መወሰን ’በተመለከተ በሰው ፈቃድ ላይ የሚመረኮዘው ነገር ምን ያህል እንደሆነ ለማስታወስ ጊዜ እንደ ሚሰጠን” ገልጸዋል። ሞት “በሰው ልጆች መካከል የሚከሰቱ ልዩነቶችን እና የፍትሕ መጓደል ዓይነቶችን ሁሉ” እንደገደለ አስታውሷል።

በተጨማሪም ሞት ከነገሮች ጋር ተጣብቀን እንዳንኖር ወይም ልባችንን “በምድራዊ መኖሪያችን” ላይ ብቻ እንዳናደርግ በመከልከል በጥሩ መንፈስ እንድንኖር ያበረታታናል ብለዋል።

የዘላለምን ሞት መፍራት

ካርዲናል ካንታላሜሳ አክለው እንደ ገለጹት ከብዙ ዘመናት በፊት ሞት በአውሮፓ አህጉር ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስ ትልቅ የሆነ ሚና እንደነበረው እና እንደገና ቅዱስ ወንጌልን በአዲስ መልክ ለመስበክም ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

አንድ ዘመናዊ የሥነ-ልቦና ባለሙያ የሞትን አለመቀበል ወይም መካድ የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ድርጊት መነሻ እንደሆነ እንደ ሚናገር የገለጹት ካርዲናል ካንታላሜሳ “እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው” (ዕብ 2፡15) ኢየሱስ እንደ መጣ አክለው ገልጸዋል። ነገር ግን “አንድ ሰው ከእሱ ለመላቀቅ ያ ፍርሃት ሊያጋጥመው ይገባል። ኢየሱስ የመጣው አካላዊ ሞት ከመፍራት ይልቅ ስለሁኔታ የማያውቁትን ሰዎች የዘላለምን ሞት እንዲፈሩ ሊያስተምር መምጣቱን” ገልጸዋል።

ሕይወታችንን በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ማቅረብ

በአስተንትኖዋቸው ማጠቃለያ ላይ ካርዲናል ካንታላሜሳ እንደ ገለጹት ኢየሱስ ራሱ ከቅዱስ ቁርባን ምስረታ ጋር የራሱን መት አያይዞ መናገሩን የገለጹ ሲሆን በቅዱስ ቁርባን ላይ መሳተፍ “የራሳችንን ሞት ማክበር እና በየቀኑ ለአባታችን ማቅረብ” የምንችልበትን አጋጣሚ ይከፍትልናል ብለዋል። ስለሆነም በቅዱስ ቁርባን መሳተፍ የራሳችንን ሞት ማክበር እና በእየለቱ ለአባታችን ራሳችንን ማቅረብ ማለት ነው ያሉ ሲሆን ለእግዚአብሔር የራሳችንን ሕይወት መስዋዕት አድርጎ ከማቅረብ የተሻለ ምን ስጦታ አለ በማለት ጥያቄ ካነሱ በኋላ የእለቱን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

04 December 2020, 13:07