“በችግር ጊዜ ብርቱ መሆን” መጽሐፍ የፊት ገጽ “በችግር ጊዜ ብርቱ መሆን” መጽሐፍ የፊት ገጽ 

ቫቲካን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከቶች በመጸሐፍ መልክ ይፋ ማደረጓ ተገለጸ!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቤተ ውስጥ የመቀመጥ ግዴታ በነበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተለያዩ የማሕበራዊ የመገናኛ መስመሮችን ተጠቅመው ያሳርጉ በነበረው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሟቸውን ስብከቶች ቫቲካን በመጽሐፍ መልክ ያፋ ማደረጓ ተገለጸ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቫቲካን የሕትመት ውጤቶች ክፍል እንደ ገለጸው በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያሳርጓቸው በነበሩ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእየለቱ ያደረጓቸውን ስብከቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አስገዳጅ በሆነ ምክንያት በቤት ውስጥ ለመቀመጥ ተገደው ለነበሩ ምዕመናን መጽናኛ ይሆን ዘንድ ያደረጓቸው ስብከቶች በመጽሐፍ መልክ መቅረቡን የቫቲካን የሕትመት ወጤቶች ቢሮ ይፋ ማደርጉ ተገልጿል።

በኮርና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለታመሙ፣ በገለልተኛ ስፍራ ብቻቸውን እንዲቀመጡ ለተገደዱ ሰዎች፣ ወይም በማንኛውም ምክንያት ከቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገው ለነበሩ ሰዎች ያላቸውን ቅርበት ለመግለጽ በማሰብ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አደጋ እስኪቀንስ ድረስ በእየለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ሕዝቡን ለማጽናናት የሚያግዙ አስተንትኖዎችን ያደርጉ እንደ ነበረ ይታወሳል።

እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 9 እስከ ግንቦት 18/2020 ዓ.ም ድረስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየቀኑ ጠዋት በማለዳ በማሕበራዊ የመገናኛ አውታሮች አማካይነት በዓለም ዙሪያ ይሰራጭ የነበረ መስዋዕተ ቅዳሴ ማደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፣ ምንም ዓይነት የሃይማኖት ልዩነት ቢኖራቸውም ፣ የተለያዩ የቫቲካን ሚዲያ ጣቢያዎችን እና ሌሎች የሬዲዮ እና ቴሌቪዥኖች ጣቢያዎችን ወይም ዲጂታል መድረኮችን በመጠቀም መከታተል እና ማዳመጥ ችለው እንደ ነበረ ይታወሳል።

የርዕሰ ሊቃና ጳጳሳቱ ስብከት እና ዲጂታል እትመት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያሳረጓቸው መስዋዕተ ቅዳሴዎች እና ስብከቶቻቸው በቫቲካን ዜና እና በዩቱብ ጣቢያ እና በድረ ገጾች በኩል ለዓለም ተደራሽ ሆነዋል። የአማርኛ እና የትግረኛ ቋንቋዎችን ጨምሮ ስብከቶቻቸው በ39 የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ነበር።

በመከራ ጊዜ ጠንካራ ሆኖ መገኘት: - ኅብረት በቤተክርስቲያን ውስጥ - በችግር ወቅት የተረጋገጠ ድጋፍ የሚል አስዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ነው።

24 July 2020, 11:29