ብጹዕ ካርዲናል ቤያ፣ የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሕብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ ብጹዕ ካርዲናል ቤያ፣ የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሕብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤  

ለክርስቲያኖች ኅብረት የጋራ ውይይት የተጀመረበት 60ኛ ዓመት መከበሩ ተገለጸ።

በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ ፈሬር፣ የክርስቲያኖች ኅብረት ማሳደግ አስፈላጊነት መሆኑን አስረድተው፣ ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ በ60 ዓመታት ጉዞ ያከናወኗቸውን ተግባራት አብራርተዋል።

የቫቲካን ዜና፤

ዓርብ ግንቦት 28/2012 ዓ. ም. 60ኛ ዓመቱን ያከበረውን የክርቲያኖች ኅብረት የጋራ ውይይት መድረክ የመሠረቱት የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ መሆናችው ይታወሳል። የክርስቲያኖች አንድነት የጋራ ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ፣ ከተቋቋመበት ከሁለት ዓመት በኋላ ከተጀመረው ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው ሲታወቅ በወቅቱም የክርስቲያኖች የጋራ ውይይት ጽሕፈት ቤት ተብሎ ይጠራ እንደነበር ታውቋል።

ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ፣ የክርስቲያኖች አንድነት የጋራ ውይይትን ለማሳደግ ምክር ቤታቸው ከወሰዷቸው ጠቃሚ እርምጃዎች መካከል አንዱ፣ ከመላው ዓለም የተወጣጡ እና ተሃድሶ ያደረጉ አብያተ ክርስቲያናት ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ በታዛቢነት እንዲካፈሉ ማድረግ እንደ ነበር አስታውሰዋል። ከቫቲካን ኒውስ ጋር ቃለ ምልል ያደረጉት ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ እንደገለጹት፣ ጳጳሳዊ ምክር ቤታቸው ከተመሠረተበት ጊዜ ወዲህ ከልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የጋራ ውይይት ማድረግ መጀመሩን እና ከአብያተ ክርስቲያናት በኩልም በጎ ምላሽ የተሰጠው መሆኑን አስታውሰዋል። የክርስቲያኖች ሕብረት የጋራ ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያከናወነው ሁለተኛው ጠቃሚ ተግባር፣ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር በ1993 ዓ. ም. ልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙበትን መዝገብ ማዘጋጀት እንደ ነበር አስታውሰው፣ በዚህም በመታገዝ በመላው ዓለም ለሚገኙ የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች የሚሆን መመሪያዎችን እና ደንቦችን በማዘጋጀት፣ አብያተ ክርስቲያናትን በጋራ ውይይት የሚያሳትፍ የቤተክርስቲያኒቱ የወደ ፊት ራዕይ ለማስተዋወቅ መቻሉን አስረድተዋል።

በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ምስረታ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ወቅት የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይፋ ያደረጉትን “ሁሉም አንድ እንዲሆኑ” የሚለውን ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳንን ያስታወሱት ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ፣ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳኑ ለክርስቲያኖች አንድነት የሚደረግ ጥረት ከቤተክርስቲያኗ አካል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል። ካቶሊካዊት  ቤተክርስቲያን አንዲት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ጸለየው የአንድነት ጎዳና የምትጓዝ ቤተክርስቲያን መሆኗን አስረድተዋል።

የዓለም ክርስቲያኖች ምክር ቤት፣

በቅድስት መንበር የክርስቲያኖች ሕብረት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የዓለም አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አባል ባይሆንም ከእምነት እና ከትእዛዝ መምሪያ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ ገልጸው፣ ጥንቃቄ የተደረገባቸው ግንኙነቶች፣ ባሁኑ ጊዜ መልካም ፍሬን እና ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል። ዋና ጽሕፈት ቤቱ ጀኔቭ የሚገኘው የዓለም ክርስቲያኖች ምክር ቤት የተመሠረትበትን 70ኛ ዓመት ባከበረበት በሰኔ ወር 2018 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መገኘታቸውን ያስታወሱት ክቡር አባ አቬሊኖ ጎንዛሌዝ፣ በውቅቱም የመላው ዓለም ዓብያተ ክርስቲያናት ቅዱስነታቸውን ለክርስቲያኖች አንድነት እንደ ዋና ምሳሌ አድረገው የተመለከቷቸው መሆኑን አስታውሰዋል። አባ ጎንዛሌዝ አክለውም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ባስከተለበት ባሁኑ ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዓለም አብያተ ክርስቲያናትን ለጋራ ጸሎት ማስተባበር መቻላቸውን አስታውሰው፣ ይህም ቅድስት መንበር የክርስቲያኖችን አንድነት በጋራ ውይይት ለማፋጠን ያደረገችው የ60 ዓመታት ጥረት ውጤት ነው ብለዋል። 

የጋራ ውይይት ርዕሶች፣

ለክርስቲያኖች አንድነት የተደረጉ በርካታ የጋራ ውይይቶችን ያስታወሱት ክቡር አባ አቬሊኖ ጎንዛሌዝ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መለያየት ያስከተለው ሕመም እና ቁስል ብዙ መሆናቸውን አስታውሰው ይህን መጥፎ ገጠመኝ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ተቋም በጥልቀት የተመለከተው መሆኑን ገልጸዋል። ወደ አንድ የውይይት መድረክ ቀርበን እርስ በእርስ መደማመጥ ስንጀምር ለቁስላችን ፈውስን ማግኘት እንችላለን ብለው ይህ ፈውስ ወደ እርቅ፣ እርቅም ወደ አንድነት የሚያደርስ ድልድልይ እንደሆነ አስረድተው፣ ቅዱስ ወንጌል የሚያስተምረንም ይህን ነው ብለዋል። ያለፈውን ታሪክ መመልከት ወደ ሥነ መለኮታዊ አስተሳሰብ በማምራት ዛሬ የምንገኝበትን ጊዜ እንድናስታውስ እና በጋራ ውይይት አማካይነት ለሥነ መለኮታዊ ርዕሠ ጉዳዮች መልስ ለማግኘት ያግዛል ብለዋል። 

የአብያተ ክርስቲያናት የአንድነት እንቅስቃሴ ተግዳሮቶች፣

የአብያተ ክርስቲያናት የአንድነት እንቅስቃሴዎችን የተለያዩ ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል ያሉት ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ፣ ከእነዚህም መከከል አንዱ ከአሥርት ዓመታት በፊት በክርስቲያኖች መካከል ሙሉ እና ግልጽ አንድነት ለማምጣት የነበረው አስተሳሰብ ዛሬ ካለው አስተሳሰብ ጋር አንድ አለመሆኑ ነው ብለዋል፣ ቢሆን በክርስቲያኖች መካከል ጥልቅ የሆነ የአንድነት ምኞት መኖሩን አስረድተዋል። ባለፉት 60 ዓመታት መካከል ክርስቲያን ማኅበረሰብ ከአመጽ ወደ ወንድማማችነት መሸጋገሩን ያስታወሱት አባ ጎንዛሌዝ፣ ይህም በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በሉተራን ኅብረት መካከል፣ የፕሮቴስታንት ተሃድሶ 500ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተደረሰው የስምምነት ሰነድ ያረጋግጣል ብለዋል። የአንድነት ጎዞ ዋና መንገድ የሆነው የስምምነት ሰነድ የተፈረመው መልካም የሆኑ የጋራ ውይይት መንገዶችን በመከተል፣ ጠቃሚ መረጃዎችን እና ታሪካችንን ገልጠን ማየት በመቻላችን ነው ብለው፣ አሁንም ቢሆን ይህን ሰነድ ተመልክተው መላው የክርስቲያን ማኅበረሰብ ጥቅም ሊያገኝበት እንደሚችል ክቡር አባ አቨሊኖ ጎንዛሌዝ አስረድተዋል።    

08 June 2020, 16:38