ካርዲናል ሆለርክ ሮበርት ሹማን ካርዲናል ሆለርክ ሮበርት ሹማን 

ካርዲናል ሆለርክ የአውሮፓ ህብረት ኮቪዲ 19 ቫይረስ እንዲዋጋ ጥሪ አቀረቡ።

ዛሬ ግንቦት 01/2012 ዓ.ም “የአውሮፓ ቀን” መከበሩ ይታወሳል። እ.ኤ.አ. ግንቦት 9 /1950 ዓ.ም የዛሬ 70 አመት ገደማ ማለት ነው በወቅቱ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሮበርት ሹማን የአውሮፓ አገራት የድንጋይ ከሰል እና የአልሙኒየም እቃዎችን በማምረት ሂደት ውስጥ አንድነትን እንዲፈጥሩ ሐሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል። ዓላማው በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ ያሉ አገራት ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን አንድ ላይ በማምጣት በአውሮፓ አገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አንድነት እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸው ጽንሰ-ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያለበት ወቅት ነበር። በዚህ መንገድ ነበር እንደ ፈረንሣይና ጀርመን ባሉ ታሪካዊ ተቀናቃኝ አገራት በነበሩ መካከል ይደረግ የነበረው ጦርነት የሮበርት ሹማንን ቃላት በመጥቀስ - “እንኳን ለመተግበት ይቅርና ሊታሰብ የማይችል የነበረው ግጭት” ተወግዶ ሰላም እንዲፈጠር ተደረገ።

የሹማን መግለጫ “አደጋ ከሚያስከትሉ አደገኛ ሁኔታዎች አንፃር ሲታይ ከፈጠራ ጥረቶች በስተቀር የዓለም ሰላም ሊጠበቅ አይችልም። የተደራጀ እና ወሳኝ የሆነ አውሮፓ ለሥልጣኔ የምታደርገው አስተዋጾ ለሰላማዊ ግንኙነቶች ቀጣይነት አስፈላጊ ናቸው” በማለት በአውሮፓ አህጉር ሕብረት እንዲፈጠር የራሱን ሚና ተጫውቷል።

ይህ “የአውሮፓ ቀን” በእየአመቱ እንደሚከበር የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቀን ዛሬ ግንቦት 01/2012 ዓ.ም በተከበረበት ወቅት ካርዲናል ዧን ክላውድ ሆለርክ ባስተላለፉት መልዕክት የአውሮፓ መሪዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልክ በከፍተኛ ደረጃ እየተነቃቃ የሚገኘውን እና የአውሮፓን ሕብረት ሊገዳደር  እና አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ብሔራዊ ስሜትን ለማስቆም በሚያደርጉት ትግል አንድነታቸውን እንዲያሳዩ አሳስበዋል።

ከጊዜ በኋላ የአውሮፓ ህብረት እንዲፈጠር ያደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሹማን መግለጫ የተጀመረበት 70 ኛ ዓመት የምስረታ ቀን ዛሬ ግንቦት 01/2012 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል። ይህንን ክብረ በዓል ለመታደም ካርዲናል ዧን ክላውድ በሉስንበርክ በምትገኘው በሸንገን ከተማ መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ ግንቦት 9/1950 ዓ.ም የዛሬ 70 አመት ገደማ ማለት ነው በሸንገን የአውሮፓን ሕብረት ለመመስረት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ የተፈረመበት እለት መታደማቸው ተገልጿል።

በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ሁኒታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት የአውሮፓ አገራት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት የሆኑት ካርዲናል ሹማን የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ችግረኞችን ለመርዳት በአንድነት እንዲሰባሰቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ታላቁ የአውሮፓ በዓል

ካርዲናል ሆለሪክ ከቫቲካን ሬዲዮ የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባ ከሆኑት ከሲስተር በርናዲት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም የተከበረው የአውሮፓ ቀን “ታላቅ የደስታ ቀን” ነው ብለዋል።

“የአውሮፓን ውህደት ሂደት ወደኋላ ተመልሰን የምንመለከት ከሆነ አመስጋኞች ልንሆን እንችላለን” በማለት በቃለ ምልልሱ ወቅት የተናገሩት ካርዲናል ሹማን “ሰላም ፣ የተወሰነ አንድነት ፣ የአውሮፓውያን እሴት አለን ፣ እናም ወላጆቻችን እና አያቶቻችን በዚህ አህጉር ግንባታ ባደረጉት ጥረት እንኮራለን” ብለዋል።

ክርስቲያናዊ ሥር መሰረቶች አደጋ ናቸው

ነገር ግን አሉ ካርዲናል ሆልሪክ የፍራቻ መንፈስ በአውሮፓ ውስጥ በተለይም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋት ምክንያት አህጉሩ ፍርሃት ውስጥ እንደ ገባ የገለጹ ሲሆን “ፍርሃት ሁል ጊዜ መጥፎ ነገር የሚመክር ነው። ፍርሃት ድንበሮችን ዘግቷል። ፍርሃት በእውነቱ ብሔራዊ ፍቅርን የሚያሳዩ አዳዲስ ስሜቶችን አምጥቷል ” ብለዋል።

አውሮፓውያን አህጉሩን ወደ መሰረቱ ወደ መስራቱ አባቶች እና ወደ ክርስቲያናዊ ሥር መሰረታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት ካርዲናል ሹማን እነሱ ማለትም ቀድም ሲል የነበሩ አባቶቻችን “በክርስትና እምነታቸው ተነሳስተው እርቅ ለመፍጠር አንዱ ሌላውን በጠላትነት ላለመመልከት ወስነው እርስ በእርሳቸው የጓደኝነት መንፈስ እንደ መሰረቱ ሁሉ እኛም ይህንን አብነት መከተል ይኖርብናል” ብለዋል።

በአውሮፓ አህጉር የሚገኙትን አገሮች እንዲከፋፈሉ የሚያደርጓቸውን ፍርሃቶች ለማሸነፍ አውሮፓውያን የክርስትና እመነተ ሥር መሰረታቸውን ጠብቀው መጓዝ እንደ ሚኖርባቸው የተናገሩት ሆልሪች በአሁኑ ጊዜ የመተባበር እና የወንድማማችነት ስሜት ያስፈልጋል ብለዋል።

መቻቻል ያስፈልጋል

የሉክሰምበርግ ሊቀጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ሹማን አውሮፓ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያስከተለውን  ቀውስ ለመዋጋት ታላቅ ጥረት ማድረጓን የገለጹ ሲሆን በእዚህ ረገድ የአውሮፓ አገራት ላሳዩት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

“ግን ሰፊ ውይይትና ስምምነትን ማድረግ ያስፈልጋል፣ ሰዎች ሲሰቃዩ ማየት በጣም ያሳዝናል፣ተከታታይ የሆነ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ ይኖርባቸዋል፣ ሁኔታው እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ የተነሳ ቀጣይነት ያላቸው ውይይቶች መደረግ እንደሚገባቸው” ጨምረው ገልጸዋል። በችግር ጊዜ የሚፈጠሩ ዕድሎች

ካርዲናል ሆልሪክ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጨምረው እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በበኩላቸው በእዚህ የወረርሽኝ ወቅት የዓለም መሪዎችን ስሜት ለማንቃት ፈልገው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማደረጋቸውን ያስታወሱ ሲሆን በእዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ይህ አስቸጋሪ ጊዜ የሰጠንን ዕድሎች መጠቀም እንደ ሚገባን መግለጻቸውን አስታውሰዋል።  “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሀሳቦቻቸውን እና ስለ አውሮፓ አህጉር ስለ ሚናገሯቸው ነገሮች ሁሉ እርሳቸውን የሚያመስኑኋቸው ብዙ ፖለቲከኞች ገጥመውኛል” ብለዋል። ካርዲናል ሹማን ጨምረው እንደ ገለጹት እያንዳንዱ ቀን “የበጎ አድራጎት፣ የተስፋ እና አብረን እንድንኖር” እግዚአብሔር የሰጠን እድል ነው ብለዋል።

ድንበሮች በድጋሚ እንከፈቱ

ካርዲናል ሆለሪክ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ በተጨማሪም አውሮፓ አህጉር በአካባቢያዊ እና በአውሮፓ ህብረት ደረጃ የድንበር ችግር እንዳለበት የገለጹ ሲሆን በአውሮፓ ድንበር ውስጥ የሚገኙ ድንበሮችን መዘጋት በሰዎች ላይ ትልቅ ችግር እንደ ሚያስከትል ገልፀዋል። “ሰዎች የተዘጉ ድንበሮችን ይመለከታሉ ፣ ነገር ግን ከአውሮፓ ህብረት የሚመጣውን እርዳታ ገና አላዩም።፡ ለዚህ ይመስለኛል በብዙ ሀገሮች በተለይም በድንበር ክልሎች አከባቢ የሚገኙት ሰዎች አሉታዊ ስሜት እየተሰማቸው የሚገኘው ብለዋል።

ወደ አውሮፓ አህጉር ለመግባት የሚሞክሩ ሰዎች ስለአህጉሩ ያላቸው አስተሳሰብ “ሰላም የሰፈነበት እና አንድነት የሚታይበት” አህጉር ነው ብለው ስለሚያስቡ ወደ አውሮፓ ለመግባት ሙከራ በሚያደርጉበት እወቅት ብዙዎቹ ለሞት መዳረጋቸውን” የገለጹት ካርዲናል ሹማን በእዚህ ረገድ በሰዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም ብለዋል ፡፡

09 May 2020, 17:15