“የተስፋ ኃይል” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ፣ “የተስፋ ኃይል” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ፣  

በተስፋ የኮሮና ቫይረስ ውረርሽኝን ማሸነፍ የሚቻል መሆኑ ተገለጸ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረግ የሕክምና አገልግሎት ላይ በማስተንተን ሃሳባቸውን በዲጂታል መጽሐፍ ላይ የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ፣ የዓለም ነፍሳትን ለመዋጀት የተባበሩ እጆች ሊኖሩ ያስፈልጋል ማለታቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የዓለም ነፍሳትን የሚዋጁ እጆች፣

ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ ይህን ዲጅታል መጽሐፍ የጻፉት በሮማ የሚገኘው ጀሜሊ ፖሊኒክ ክሊኒክ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተጀመረውን የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረት ለማገዝ መሆኑ ታውቋል። ካርዲናል በዚህ መጽሐፋቸው የኮሮርና ቫይረስ በማስከተል ላይ ያለው ቀውስ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካስከተለው ቀውስ የበለጠ መሆኑን በመጽሐፋቸው ባቀረቡት አስተንትኖ በኩል ገልጸው፣ ከዚህ ቀውስ መውጣት የሚቻለው የሐይማኖት ተቋማት እና ሕዝባዊ ድርጅቶች የድጋፍ እጆቻቸውን በማስተባበር መሆኑን አስረድተው፣ ዓለም ከወደቀበት ቀውስ መውጣት የሚችለው በተስፋ ሃይል እንደሆነ፣ ይህም በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በሚደረግ ዓለም አቀፍ የጸሎት ሕብረት መሆኑን አስረድተዋል።

ተነጥሎ መቀመጥ ወረርሽኙን ይቀንሳል፣

የተስፋ ኃይል ከሞት እና ከጥፋት ልንተርፍ የምንችልበትን የኑሮ ልማድ መልሶ በማጤን መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ አስረድተዋል። የኮሮርና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቀነስ ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል አንዱ ከሰዎች በመነጥል ወይም በመለየት ሲሆን ይህ ዘዴ ያልተለመደ ቢሆንም አሁን በምንገኝበት አስጨናቂ ሰዓት ላይ ተግባራዊ ማድረግ ያለብን ስጦታ ነው ብለዋል። ከሰዎች ተነጥለን በምንቀመጥበት ጊዜ የማኅበራዊ ኑሮ ትክክለኛ ትርጉምን ማወቅ እንችል ይሆናል ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ፣ ከዚህም ብዙ ነገር መማር እንችላለን ብለው ሙሉ ጤና፣ የእርስ በእርስ ማሕበራዊ ግንኙነት፣ እጅ በመጨባበጥ የሚደረግ የሰላምታ ልውውጥ ትርጉም ምን እንደሆነ መረዳት እንችላለን ብለዋል። አሁን ግን እጅ ለእጅ ሳንጨባበጥ፣ ሳንተቃቀፍ፣ በእንግድነት በመቀባበል እና አንዱ ለሌላው አለኝታ መሆን እንችላለን ብለው እርስ በእርስ ባንተዋወቅም አንዳችን ለሌላው ማሳየት ያለብንን ፍቅር ለመግለጽ እንገደዳለን በማለት ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ አስረድተዋል።  

ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት መልሶ ማግኘት፣

“በተስፋ ፍርሃትን ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው?” በማለት ጥያቄ ያቀረቡት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የመዝገብ ቤት ተጠሪ፣ ገጣሚና የሥነ-መለኮት ትምህርት አዋቂ፣ ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ፣ አንድ መንገድ እንዳለ ሲያስረዱ፥ አሁን የምንገኝበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት እና እምነት መልሰን የምናገኝበት ጊዜ ነው ብለዋል። የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ እንደጻፈው፣ ለሕይወታችን እና ለስጋችን የምናደርገውን ዕለታዊ ልፋት በድንገት በማቋረጥ ለሕይወታችን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በእውነት ማግኘት ወደ ምንችልበት አዲስ የሕይወት ዘይቤ መድረስ የሚቻል መሆኑን ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ አስረድተዋል።

አርቆ መመልከት ያስፈልጋል፣

“አርቆ መመልከት ያሻል” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ፣ ብዙን ጊዜ የእኛ አርቆ ማየት ብዙ ሳይርቅ በአጭር ተወስኖ ይቀራል ብለው ማሰብ ያለብን ራሳችን ማከናወን ወይም መፈጸም በምንችለው ነገር ብቻ ሳይሆን የሕይወት አድማሳችን ከዚያ ያለፈ እና በምስጢራዊ መንገድ ስፋት ካለው የሕይወት አቅጣጫ ጋር መወያየት ያስፈልጋል ብለዋል። ውይይታችንም አቅማችን ማድረግ ከሚችለው እና ከእግዚአብሔር በስጦታ ከተቀበልነው ችሎታ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጤን መሆን አለበት ብለዋል።

ምን አስተዋጽዖ ማድረግ ይቻላል፣

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረግ የሕክምና አገልግሎት ላይ በማስተንተን ሃሳባቸውን በመጽሐፍ የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ፣ ነፍሳትን ለመዋጀት የተባበሩ እጆች በተስፋ ሃይላችንን ማስተባበር እንደሚያስፈልግ  ሃሳብ የሚሰጥ መጽሐፋቸውን “ከሳክሮ ኩዎሬ ዩኒቨርሲቲ” ማተሚያ ቤት  ድረ ገጽ ላይ በነጻ በመቀበል በሮም ከተማ የሚገኝ “ጀሜሊ ፖሊ ክሊኒክ” የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት በገንዘብ ማገዝ የሚቻል መሆኑ ብጹዕ ካርዲናል ሆሴ ቶሌንቲኖ መንዶካ አስታውቀዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
24 March 2020, 17:40