ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለፍጥረታት እንክብካቤን ማድረግ እንደሚገባ ባሳሰቡበት ወቅት፣   ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለፍጥረታት እንክብካቤን ማድረግ እንደሚገባ ባሳሰቡበት ወቅት፣  

ፍጥረታትን የምንከባከብበት ክርስቲያናዊ የሆኑ ምክንያቶች

“እናታችን የሆነችው ምድራችን” በሚል አርእስት ምድራችንን እየገጠማት ያለውን ተፈታታኝ ሁኔታ በተመለከተ ክርስቲያናዊ የሆነ እይታ” በተመለከተ በቫቲካን ታትሞ ከዛሬ ጀምሮ ማለትም ከጥቅምት 13/2012 ዓ.ም ይፋ የሆነው መጽሐፍ  በአሁኑ ወቅት በአከባቢያችን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ከፍተማ ውድመት በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና እንዲሁም የቁስጢንጢንያው የኦርቶዶክስ የውህደት ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ በአሁኑ ወቅት አከባቢያችንን ወይም ምድራችንን እየገጠማት የሚገኘውን ፈታኝ ሁኔታ አስመልክቶ ክርስቲያኖች ሁኔታውን በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ እንዲጨምር በማሰብ በጋራ እና በትብብር መሥራ እንደ ሚኖርባቸው የሚገልጽ መጽሐፍ ነው።

በማስከተል እምነታችን ይህ ነው በሚል አርእስት ዘወትር ሐሙስ በእዚህ ሰዓት የምናቀርብላችሁን ሳምንታዊ ዝግጅት እናስደምጣችኋለን። በዛሬው እለት እመነታችን ይህ ነው በሚለው ዝግጅታችን ከእዚህ ቀደም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ተንተርሰው ርዐሰ ሊቃነ ጵ በተከታታይ ስይቀርቡ የነበሩትን አስተምህሮ ክፍል 5 እናስደምታጭኋለን።

ፍጥረታትን የምንከባከብበት ክርስቲያናዊ የሆኑ ምክንያቶች

ከባለፈው መስከረም 25- ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም ድረስ “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህ ሲኖዶስ “የዓለማችን ሳንባ” በመባል የሚታወቀውና 7.8 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎሜትር በሚሸፍነው የአማዞን ደን ክልል አዋሳኝ አገሮች ማለትም በብራዚል፣ በቦሊቪያ፣ በፔሩ፣ በኤኳዶር፣ በኮሎንቢያ፣ በቬንዙዌላ፣ በጉያና እና በሱሪናም አከባቢ የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ትኩረት ባደረገ መልኩ እና የቤተክርስቲያኗን ዓለማቀፋዊነት በሚያንጸባርቅ መልኩ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ የካቶሊክ ቤተክርቲያን ብጹዐን ጳጳሳትን ባካተተ መልኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ቀደም ባሉ ዘገባዎቻችን መግለጻችን ይታወሳል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የብጽዐን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዛሬ ጥቅምት 13/2012 ዓ.ም እንደ ሚጠናቀቅ የተገለጸ ሲሆን ይህ ሲኖዶስ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ዝግ በሆነ ሁኔታ በመምከር እና የማጠቃለያ ሰነድ በማዘጋጀት በመጪው ቅዳሜ እለት በሚቀረበው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ድምጽ ተሰጥቶ ከጸደቀ በኋላ በመጪው እሁድ ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሚያደርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ይጠናቀቃል። በእዚህ ሲኖዶስ ማብቂያ ላይ በላቲን ቋንቋ  “Laudato sì’” በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዛሬ አራት አመት ገደማ “የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ለንባብ ካበቁት ሐዋርያዊ መልእክት በመቀጠል “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የብጽዐን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሲኖዶሱ ወቅት ካደረጉዋቸው ንግግሮች እና በወቅቱ ከተደረጉት ውይይቶች እና ንግግሮችን አጠቃሎ የያዘ አንድ አዲስ መጽሐፍ ይፋ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የእዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ እና ግብ “ፍጥረትን የምንከባከብበት ክርስቲያናዊ የሆኑ ምክንያቶች” በስፋት የሚተነትን መጽሐፍ እንደ ሆነ ተገልጹዋል።

“እናታችን የሆነችው ምድራችን። ምድራችንን እየገጠማት ያለውን ተግዳሮት በተመለከተ ክርስቲያናዊ የሆነ እይታ” በተመለከተ በቫቲካን ከዛሬ ጀምሮ ማለትም ከጥቅምት 13/2012 ዓ.ም ይፋ የሆነው መጽሐፍ  በአሁኑ ወቅት በአከባቢያችን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ከፍተኛ ውድመት በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና እንዲሁም የቁስጢንጢንያው የኦርቶዶክስ የውህደት ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ በአሁኑ ወቅት አከባቢያችንን ወይም ምድራችን እየገጠማት የሚገኘውን ፈታኝ ሁኔታ አስመልክቶ ክርስቲያኖች ሁኔታውን በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ እንዲጨምር በማሰብ በጋራ እና በትብብር መሥራት እንደ ሚኖርባቸው የሚገልጽ መጽሐፍ ነው። በተለይም ደግሞ የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምድራችንን በተመለከተ “አሳሳቢ የሆኑውን የወደፊቱ የምድራችን እና በምድራችን ላይ የሚኖሩ ፍጥረታት ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን” በተመለከተ ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ ለመፍታት እና መፍትሄ ለማበጀት በጋር ተቀራርበው የሚሰሩበት እና ለምድራችን አስፈላጊ የሆነ እንክብካቤ ማደረግ እንደ ሚገባ የሚያሳስብ መጸሐፍ መሆኑም ተገልጹዋል።

የሰው ልጅ አንድነት

“ዘላቂ እና የተዋሃደ ልማት ለማምጣት ይችላ ዘንድ መላውን የሰው ልጅ አንድነት ባካተተ መልኩ እና በእዚህ  አማካኝነት የጋራ ቤታችንን የመጠበቅን አስፈላጊነት” የሚያጎሉ ሐሳቦች የተካተቱበትና የመጀመርያው ምዕራፍ “የተቀናጀ ራእይ” የሚል አርእስት ተሰጥቶታል። ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የብክለት ፣ የአለም ሙቀት መጨመር ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሀ ሕይወት መጥፋት ባለበት በአሁኑ የአካባቢ ቀውስ ሁኔታ ላይ የተደረጉ አንዳንድ ስነ-ምዕዳርን የተመለከቱ ትንታኔዎችን በማጥናት “ዓለማቀፋዊ ከሆኑ ተግዳሮቶች አንስቶ ዓለም አቀፍዊ እስከሆኑ ዕድሎች ድረስ” ያለውን በመጥቀስ ማብራሪያ የሚሰጥ ምዕራፍ ነው። በአጭሩ ይህ አሁን ዓለማችን እየገጠማት የሚገኘው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ካላገኘ እና የመፍትሄ ሐሳቦች ካልተቀመጡ፣ ይህ ሐሳሳቢ የሆነ ሁኔታ እንዲቀየር የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ካልተቀመጡ ዓለማችን አሳሳቢ ወደ ሆነ ሁኔታ ውስጥ ስለምትገባ ይህን ሐሳሳቢ ሁኔታ እና መፍትሄውን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሁኔታውን አሳሳቢነት፣ በተለይም ወጣቶች ግንዛቤ የሚያገኙበትን መድረክ እና ሁኔታ በመፍጠር ከህሊና የመነጨ እውነተኛ ሥነ-ምህዳራዊ የሆኑ ትምህርቶችን  በማስፋፋት ሁኔታውን መቀየር እንደ ሚገባ የሚገልጽ ሐሳቦች የተካተቱበት ምዕራፍ ነው።

የፍጥረታትን እና የሕይወትን መብት መጠበቅ

ንግግሮችን፣ ከታዳሚዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶችን እና ግንኙነቶችን በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያደረጉዋቸውን በርካታ ስብከቶች በተካተቱበት የመጽሐፉ ክፍል ውስጥ እርሳቸው ስመተ ርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ከተቀበሉበት እለት አንስቶ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ያደረጉዋቸውን ንግግሮች እና የሰጡዋቸውን አስተያየቶች አጠቃሎ በያዘው የመጽሐፉ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለሁሉም ሕያዋን ፍጥረታት የሰጠውን ትልቁን ስጦታ ጠብቆ ለማቆየት ነው፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ “በእግዚአብሔር እስትንፋስ” የተፈጠረው የሰው ልጅ አሁን በዓለማችን ላይ ለተቃጣው አሳሳቢ አደጋ በምድራችን ላይ የተቃጣባትን አደጋ ለመታደግ በሚደርገው ጥረት የሰው ልጅ በግንባር ቀደምትነት ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ምክረ ሐሳብ የሚያቀርብ የመጽሐፉ ክፍል ነው። በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው ፈጣሪ የሆነው እግዚኣብሔር ፍጥረታት እና የሰው ልጅ የማይነጣጠል እና ጠንካራ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው መግለጻቸውን የሚያመለክቱ ሐሳቦች የተጠቀሱበት መጽሐፍ ሲሆን ፍጠርታትን እና የሰው ልጅ ሕይወትን የተመለከቱ ጥያቄዎች መሰረታዊ እና ቀጣይነት ያላቸው ፍትሃዊ የሆኑ ጥያቄዎች በመሆናቸው የተነሳ ለእነዚህ የሕልውናችን ጥያቄዎች በሙሉ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን ከጥፋት መታደግ ይገባል የሚል እንድምታ የያዘ የመጽሐፉ ክፍል ነው። 

ስነ-ምዕዳርን የተመለከተ መንፈሳዊ ንባብ

“እናታችን የሆነችው ምድራችን” የተሰኘውን መጽሐፍ በማጠቃለያው ጽሑፍ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትኩረታቸው አሁን ያለው የምድራችን ሁኔታ ለአካባቢያችን ደህንነት በጣሚ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ መደረሱን ለማመልከት የተጠቀሙበትን ልዩ ልዩ ሐሳቦች አቅፎ በመያዝ ትንታኔ የሚያቀርብ የመጽሐፉ ክፍል ሲሆን ስነ-ምዕዳርን የሚመለከቱ ጉዳዮች ሳያንሳዊ ትንታኔ የሚሰጥባቸው ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ የፈጣሪ ድንቅ ሥራ የሚንጸባረቅበት በመሆኑ የተነሳ ነገረ-መለኮታዊ በሆነ መልኩ ጭምር ትንታኔ በመስጠት ምድራችን ሐሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መገኘቷ በራሱ መንፈሳዊ የሆነ መፍትሄ የሚያስፈልገው ጉዳይ እንደ ሆነ ጨምሮ ይገልጻል።

የእግዚኣብሔር ፍቅር የሁሉም መዐክል ነው

ፍጥረት የእግዚአብሔር ፍቅር ፍሬ ነው፣ እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ ሁሉ እና ከሁሉም በላይ ለፍጥረታቱ ጠባቂ አድርጎ የሰየመው የሰው ልጅ ለምድራችን ተገቢውን ጥበቃ በማደረግ ምድራችን የሰው ልጆች በተስፋ የሚኖሩባት ሥፋራ ትሆን ዘንድ የማደረግ ኃላፊነት በሰው ልጆች ላይ የተጣለ ኃላፊነት መሆኑን የሚያትቱ ጽሑፎች ተካተውበታል። በእዚህም ምክንያት ትርጉም ባለው መልኩ አከባቢያችንን እና በአጠቃላይ ምድራችንን እየደረሰባት ካለው ውድመት ለመከላከል የሰው ልጆች አንድነት በመፍጠር እና በተቀናጀ መልኩ ተግባራቸውን ማከናወን እንደ ሚገባቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተደጋጋሚ ማውሳታቸውን የሚገልጸው ይህ መጽሐፍ በሰው እና በፍጥረት መካከል ያለው በፍቅር ላይ የተገነባው ግንኙነት ከተቋረጠ የሰው ልጅ ከፈጣሪ የተሰጠውን ጸጋ ትርጉም ባለመረዳቱ የተነሳ ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት ይናጋል የሚሉ የቅዱስነታቸው ሐሳቦች የተጠቀሱበት ጹሑፎች ይገኙበታል። የተፈጥሮ ሐብት በጥቂት ሰዎች እጅ ብቻ ለማስገባት በሚደረገው ኃላፊነት የጎደለው ሐብት ለማጋበስ የሚድረገው ሩጫ ብዙዎቹ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የሚከናወኑ በመሆናቸው የተነሳ ዓለማችንንና የሰውን ልጅ ራሱ ሊያጠፉ የሚችሉ ክስተቶች በመሆናቸው የተነሳ ከአሁኑ አስፈላጊ የሆነ እርምጃ እና መፍትሄ እንዲበጅላቸው ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ ያቅረቡትን ሐሳብ በውስጡ የሚገኙበት መጸሕፍ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህ የአከባቢያችን እና በምድራችን ላይ በአሁኑ ወቅት እየተቃጣ የሚገኘው አደጋ አሰቸኳይ የሆነ መፍትሄ የሚያስፈልገው በመሆኑ የተነሳ ሁኔታው የበለጠ ከመስፋፋቱ በፊት ሕይወት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት በእዚህም መሰረት ሕይወትን ለማቆየት የሚያስችሉ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ የሆኑ ሞዴሎችን በመጠቀም የሰው ልጆች ሁሉ እኩል የሆነ መብት እና ክብር ያላቸው መናቸውን በሚገልጽ ሁኔታ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በማርቀቅ አከባቢያችንን ከጥፋት መታደግ ይገባል የሚሉ ሐሳቦች የተካተቱበት መጽሀፍ ነው።

 

24 October 2019, 16:03