ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ፓል ጋላጋር፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ፓል ጋላጋር፣ 

ቅድስት መንበር የኑክሌር ኃይልን ሰላማዊ አጠቃቀም ከፍ ስለማድረግ ጥሪ አቀረበች ፡፡

ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ፓውሎስ ጋላጋር በቅድስት መንበር የመንግስታት ግኑኝነት ጽህፈት ቤት ዋና ጸሐፊ እ/ኤ/አ መስከረም 16 ቀን  ለአለም አቀፍ የአቶሚክ ሀይል ተቋም ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር አድርገዋል፡፡

ቅድስት መንበር ለዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቋም  ለ “ኑክሌር ማስፋፊያ እና “የኑክሌር ቴክኖሎጂዎች በታመነና ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ፣ለሰላምና ልማት ተግባር ድጋፍፌን  አጠናክራለሁ አለች፡፡ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ፓውሎስ ጋላጋር እንደተናገሩት “የኑክሌር መስፋፋት ፣ የኑክሌር የጦር መሣሪያ ዝርጋታ እና የኑክሌር ቴክኖሎጂዎችን ሰላማዊ አጠቃቀሞች በዚሁ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቋም ሰላማዊ አጠቃቀም ላይ የተመረኮዘ ነው ብለዋል ፡፡ይህም እሁድ ዕለት፣ በኦስትሪያ ዋና ከተማ በቪየና በ63 ኛ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቋም  ጠቅላላ ጉባኤ  ላይ ነበር የተናገሩት፡፡ይህ አለም አቀፍ ተቋምም እ.ኤ.አ. በ 1957 የተቋቋመ ገለልተኛ  በሆነ የዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆነ አላማውም፣ሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀምን ለማሳደግ እና የኑክሌር መሳሪያዎችን ጨምሮ ለማንኛውም ወታደራዊ ዓላማ መጠቀምን ለመግታት ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

የኑክሌር ቴክኖሎጂ እና የተቀናጀ ልማት ፡፡

ሊቀ ጳጳስ ጋለገር በበኩላቸው በለዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቋም  የቀረቡት የተለያዩ የኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሊረዱ ይችላሉ ብለዋል ፡፡ የእነሱ ትግበራ ሁሉን አቀፍ ልማት ማጎልበት ይችላል ፣ በዚህም የእግዚአብሔር ፍጥረትን በአግባቡ ለማስተዳደር ይረዳል ብለዋል ፡፡

ሊቀ ጳጳስ ጋለገር እንደተናገሩት የድርጅቱ “በጤና ፣ ውሃ እና አከባቢ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በምግብ ዋስትና እና በግብርና መስክ ያሉ የትብብር ፕሮጄክቶቻቸው፣ ለድህነት ቅነሳ እና ሀገራት የልማት ግቦቻቸውን በዘላቂነት ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ ፣ የቅዱስ መንበር ባለሥልጣን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስኮን በመጥቀስ ፣ “የሳይንሱ ማህበረሰብ ግጭቶችን ለመፍታት መነጋገር የፕላኔታችንን ቀውስ ማሳየት እንዲችል  እንዲሁም“ አጠቃላይ ጥበቃን ለማረጋገጥ እና ልዩ መፍትሄዎችን የሚሰጥ መሪ እንዲያቀርብ ተጠርቷል ፡፡ከቴክኖሎጂ-ኢኮኖሚያዊ ሞዴሉ የሚመነጨው አዳዲስ የኃይል ዓይነቶች በአከባቢ ብቻ ሳይሆን በኅብረተሰባችንም ፣ በዲሞክራሲ ፣ በፍትህና በነጻነት ላይ ሊተካከሉ የማይችሉ ጉዳቶችን ያስከትላሉ ብለዋል፡፡

የሰውን ልጅ ማዕከላዊነት።

ሊቀ ጳጳሱ እንዳመለከቱት ማህበራዊ እድገትን ለማምጣት እና የጋራ የሆኑ መልካም ነገሮችን ለማስፋፋት የሚደረገው ማንኛውም ጥረት የእያንዳንዱ ሰው ትብብር ፣ልማትን ለማረጋገጥ ባለው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ብለዋል ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የልማት መብት ላይ የወጣውን መግለጫ በመጥቀስ “የሰው ልጅ የልማት ዋና ማእከል ነው ብለዋል ፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክ አስራ ስድስተኛን ጠቅሰው ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የኑክሌር ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ለማዋል በቅድስት መንበር የሚደረግ ድጋፍ ፣ ለሰው ልጅ የመከባበርን ባህል ለማዳበር ፣ለሰው ልጅ ክብርና ነጻነት መጎልበት፣ ቀጣይነት ያለው ውይይት እና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፡፡ ክብር ፣ ነጻነት ፣ ለወደፊት መልካም ቤተሰብ እና ዘላቂ የፕላኔታችን ዘላቂ ልማት "

ለምንኖርባት ምድርም ዘላቂ የሰላምና የልማት መፍትሄ ያመጣልም በማለት ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የሳይንስ ግስጋሴያችን እና እድገታችን ሁል ጊዜ“ ሀላፊነት የተሞላበት የሰው ልጅ እድገት ፣ እሴቶቻችንን በመጠበቅ የተደገፈ ”  አለመሆኑን ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ ጋላትገር ለዚሁ አለም አቀፍ ተቋም ከኒውክሌር የጦር መሳሪያዎች ነፃ የሆነ ዓለምን ለመፍጠር በተለያዩ ስምምነቶች እና ፕሮቶኮሎች አማካይነት እየሰራ ላለው መልካም ስራ እውቅና ሰጥተዋል፡፡በመቀጠልም ቅድስት መንበርም በተለይ ለካንሰር ቴራፒ ሕክምና እየተደረገ ላለው ጥረት ምስጋናቸውን ገልፀዋል ፡፡

18 September 2019, 17:52