በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑ ካርዲና ፔትሮ ፓሮሊን በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑ ካርዲና ፔትሮ ፓሮሊን  

ካ. ፓሮሊን “የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በሽታን መፈወስ እና ሕይወትን የመጠበቅ ኃላፊነት አላቸው!” አሉ

በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑ ካርዲና ፔትሮ ፓሮሊን ባለፈው ሐምሌ 17/2011 ዓ.ም በሮም ከተማ የሚገኘውን እና በቫቲካን ጥላ ሥር የሚተዳደረው ባንቢኖ ጄዙ (ሕጻኑ ኢየሱስ) በመባል የሚታወቀው የሕጻናት ሆስፒታል አስተዳዳሪዎች እና ከሐኪሞች ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመከሩበት ወቅት እንደ ገለጹት “የጤና እንክብካቤ መስጫ ተቋማት በሽተኛው ከሕመሙ የሚፈወስበት ቦታ ብቻ ሳይሆን ለሕይወት ጥበቃ የሚደረግበት ሥፍራ ጭምር ነው” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም “የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በሽታን መፈወስ እና ሕይወትን የመጠበቅ ኃላፊነት አላቸው!” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአሁኑ ወቅት “ብዙ ዓይነት በሕክምና መዳን የሚችሉ በሽታዎች አሉ፣ በሕክምና የማይድኑ በሽታዎች ቢኖሩም እንኳን ለበሽተኛው እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ እንክብካቤ ማድረግ እና ሕይወቱን መንከባከብ እንደ ሚገባ” በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉ በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የሰው ልጆች ከውልደታቸው እስከ ተፈጥሮአዊ ህልፈታቸው ድረስ ለሕይወታቸው እንክብካቤ ማደረግ እንደ ሚገባ አክለው የገለጹ ሲሆን የሰው ልጅ የገዛ ራሱ ነፍስ ባለቤት ስላልሆነ የነፍሱ ባለቤት የሆነው ፈጣሪ በፈለገው ጊዜ እና ሰዓት ነፍሱን እስኪወስዳት ድረስ ለሕይወት እንክብካቤ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ባንቢኖ ጄዙ (ሕጻኑ ኢየሱስ) በመባል የሚታወቀው የሕጻናት ሆስፒታል 150 ዓመት እድሜ ያለው የሕጻናት ሆስፒታል ሲሆን በሥሩ አራት ቅርንጫፍ የሕጻናት ሆስፒታሎች እንደ ሚገኙ፣ ከጣሊያን እና ከጣሊያን ውጪ ከሚገኙ የተለያዩ አገራት የተውጣጡ ሕጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት በቫቲካን ጥላ ሥር የሚተዳደር ሆስፒታል ነው።

በወቅቱ ንግግር ያደረጉት በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የተቋሙ ግብ የተሳካ እንዲሆነ በርትተው የሰሩትን የተቋሙን ሰራተኞች በሙሉ ማመስገናቸው የተገለጸ ሲሆን በተቋም የሚሰጡ የጤና ክብካቤ ሂደት ሳይናሳዊ እና ማኅበራዊ በሆነ መልኩ በተቀናጀ ሁኔታ መሰጠታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው በተጨማሪም በተለያዩ አገርት የሚገኙ ሕጻናት የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ዘንድ የሚደረገውን ሰብዓዊ ድጋፍ ከቤተክርስቲያኗ ማኅበራዊ አስተምህሮ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
24 July 2019, 15:30