የፓክስታን ክርስቲያን ምዕመናን፣ የፓክስታን ክርስቲያን ምዕመናን፣ 

ዓለም አቀፍ የስነ መለኮት ጥናት ምክር ቤት የእምነት ነጻነትን የሚመለከት ሰነድ ይፋ አደረገ።

ዓለም አቀፍ ስነ መለኮቶዊ ጥናት ምክር ቤት በድረ ገጹ ይፋ እንዳስታወቀው፣ የግል እና የጋራ እምነት ነጻነት ለተቀሩትም የሰው ልጆች ነጻነቶችን እና አጠቃላይ ማሕበራዊ እድገት ወሳኝ እንደሆነ አስታውቋል። “የእምነት ነጻነት ለሰው ልጆች በሙሉ የሚያበረክተው ጥቅም እና የዘመናችን የሥነ መለኮት ድርሻ” በሚል ርዕሥ ዙሪያ ሲወያይ የቆየ ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ ሰነድ በማውጣት መጠናቀቁ ታውቋል። 37 ገጾች ያሉት ይህ ሰነድ የእምነት ነጻነትን አስመልክቶ ከዚህ በፊት ማለትም በ1957 ዓ. ም. የወጣውን እና በላቲን ቋንቋ “Dignitatis humanae” ሲተረጎም “ሰብዓዊ ክብር” የተባለውን እና የዘመኑን አስተሳሰብ መሠረት ባማድረግ የወጣውን ሰነድ የሚያጠናክር መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የሃይማኖታዊ አክራሪነት እና አንጻራዊነት፣

ዓለማዊነትን በተላበሰው ዘመናችን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የእምነት ማሕበረሰቦችን ያገናዘበው ይህ ሰነድ በመንግሥት እና በግል የእምነት ተቋማት መካከል የሚታዩ ግንኙነቶችን ለይቶ የተመለከተ መሆኑ ታውቋል። በዚህም መሠረት ዛሬ የምናያቸው የእምነት እንቅስቃሴዎች እንደ ባሕላዊ የሐይማኖት አክራሪነት የሚቆጠሩ ሳይሆን አንጻራዊነትን በመከተል ከእምነት መንገድ ወጣ ባሉ በዘመናዊ የመንግሥት አወቃቀር እና አመስሠራረት ምክንያት  የሚከሰቱ እንደሆነ ሰንዱ አብራርቷል።

የሊብራል መንግሥታት መመስረት ለዘብተኛ አምባገነናዊነትን ይፈጥራል፣

ሊብራል መንግስሥታት ከየትኛውንም የእምነት ተቋማት ወገን ካለመሆናቸው የተነሳ ብዙውን ጊዜ በእምነቶች ላይ ለሚቀርቡ በርካታ ትችቶች በር እንደሚከፍቱ እና የእነት ተቋማትን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ግግሮችን እና እንቅፋቶች ማስወገድ የማይችሉ መሆኑ ታውቋል። በመሆኑም ሊብራል መንግሥታት ለለዘብተኛ አምባ ገነናዊ ሥርዓቶች መፈጠር ምክንያት በመሆን፣ በማሕበራዊ ኑሮ መስክም ስርዓት እንዳይኖር ያደርጋል ተብሏል።

ርዕዮተ ዓለማዊ የገለልተኝነት ባህሪ እምነትን ያገልላል፣

የፖለቲካ ሥርዓት ርዕዮተ ዓለማዊ ገለልተኝነት ማሕበራዊ ፍትሕን ለመገንባት በሚደረግ ሂደት ላይ ተስጽዕኖን በመፍጠር፣ በእምነት ዕሴቶች በኩል ለሚቀርቡት አስታራቂ ሃሳቦች እድል ካለመስጠቱም በላይ የገለልተኛነትን አቋም የሚያንጸባርቅ በመሆኑ እና ይህም በእምነቶች መካከል ለሚፈጠር መገለል ዋና ምክንያት በመሆን ሰዎች ማሕበራዊ ሕይወትን በሙላት እንዳይሳተፉ፣ እምነታቸውንም በነጻነት እንዳይገልጹ ያደርጋል ተብሏል። የሊብራል መንግሥታት ሰዎች በሚያራምዱት እምነት መካከል ልዩነት እንዲፈጠር መንገድ በመፍጠር፣ በእምነቶች መካከል መበላለጥን በመፍጠር መገለልን ያስከትላል ተብሏል። ገለልተኛ ሕዝባዊ ባሕል የሰው ልጅ ሃይማኖታዊ እሴቶች እንዲወገዱ የሚያደርግ ከመሆኑ በተጨማሪ ሰዎች ታሪካቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ባሕላቸውን እና የራሳቸውን ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጡ የሚያደርግ መሆኑን ጉባኤው ገልጿ። ውጤቱም ሰዎች ማሕበረሰብዓዊ ማንነታቸው መሸረሸር እና መወገድ እንደሚሆን ጉባኤው አሳታውቋል። በአንድ ማሕበረሰብ ዘንድ ሰብዓዊ ማንነት ተዳክሞ መጥፋት በተለይ በወጣቶች መካከል የአስተሳሰብ ቀውስን በማስከተል እምነትን እስከ መካድ እንደሚያደርስ ጉባኤው አክሎ አስገንዝቧል። አመጽ እና አምባ ገነንነት የሚንጸባረቅበት የዘመናችን የፖለቲካ ሥርዓት ወይም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበት በቂ ጥናት ሊደረግበት እንደሚያስፈልግ ጉባኤው አሳስቧል።    

ዓለማዊ አስተሳሰብ የሚመስል ንድፈ-ሐሳብ፣

በስነ ሞራል ገለልተኛ የሆነ መንግሥት በምሕበረሰብ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ሰብዓዊ ደንቦችን እና ሕጎችን መቆጣጠር በሚጀምርበት ጊዜ ወደ ዓለማዊው አስተሳሰብ በማዘንበል በእምነቶች መካከልም የራሱን ንድፈ ሃሳቦች መዘርጋት የሚጀምር መሆኑን እንደሚጀምር ያስታወቀው ጉባኤ መንግሥት የእምነቶችን ነጻነት ለማስፋፋት በሚል ሽፋን እና ፖለቲካዊ ስልጣንን በመጠቀም፣ ፈላጭ ቆራጭ አምባ ገነናዊ ስርዓቱን መከታ በማድረግ፣ ሐይማኖታዊ እሴቶችን ወደ ጎን በማድረግ፣ ለዓለማዊ ንድፈ ሃሳቦች ማደግ ዕድል የሚያመቻች መሆኑን ጉባኤው ገልጿል። በማከልም ስነ ሞራላዊ ነጻነትም መንግሥት በሚያራምደው ግልጽ በሆነ የገለልተኝነት አቋም በመታገዝ በሕዝቦች መካከል ልዩነትን ሊያስከትል እንደሚችል ጉባኤው አስታውቋል።

ሐይማኖት በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ፣

ከዚህ በፊት የተደረገው ጥናት የሦስተኛው ክፍለ ዘመን እምነት የዘመኑን ሥልጣኔን ተከትሎ የምጣኔ ሃብት እድገትን የሚያንጸባርቅ ይሆናል የሚለውን የጥናት ውጤት ሰነዱ ውድቅ አድርጎ በተቃራኒው ሕዝቦች የሚያራምዷቸው ልዩልዩ እምነቶች በሕዝባዊ መድረኮች ላይ በስፋት እየታዩ መምጣታቸውታውን ሰነዱ ይፋ አድርጓል።

የቤተክርስቲያን አስተምሕሮች እድገት፣

በአንድ ወቅት ይሰጥ የነበርው የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ገለልተኛ እና ነጻ የሆነውን ዓለማዊ አስተሳሰብ ይቃወም እንደነበር የገለጸው ሰነድ በዘመናት መካከል ሐይማኖት የአንድ መንግሥት መጠሪያ ይሆን እንደነበር አብራርቶ ይህም በምዕራቡ ዓለም በግልጽ ይታይ እንደነበር ሰነዱ አክሎ አስረድቷል። “Dignitatis humanae” ሲተረጎም “ሰብዓዊ ክብር” የተሰኘው ሐዋርያዊ ሰነድም መሠረታዊ በሆነ ክርስቲያናዊ አስተምህሮው በሐይማኖት ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ መደረግ እንደሌለበት፣ ተጽዕኖ የሚደረግ ከሆነ እግዚአብሔር ለፈጠረው ሰብዓዊ ፍጥረት ተገቢ እንዳልሆነ፣ የክርስትና እምነትም አስተምህሮ እንዳልሆነ ሰነዱ አስታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የእምነት ነጻነት ለሌሎች ነጻነቶችም መሠረት ነው፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የእምነት ነጻነትን በማስመልከት ባደረጉት ንግግራቸው የእምነት ነጻነት ለሌሎች ነጻነቶችም ሁሉ መሠረት ነው ያሉትን ያስታወሰው ሰነድ ይህም ከመሠረታዊው ሰብዓዊ ነጻነት የሚለይ እንዳልሆነ አስረድቷል። የእምነት ነጻነት በሕግ መረቀቅ ያለበት ሳይሆን እያንዳንዱ ግለሰብ እና ሕዝብ ለጋራ ጥቅም ሲባል ሊኖረው የሚገባ ነጻነት ዋስትና እንዲኖረው የሚያደርግ እንደሆነ ሰነዱ አብራርቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ፣ የእምነት ነጻነት ለአማኞች ብቻ አይደለም፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛም በበኩላቸው የእምነት ነጻነት ከሰው ልጅ ሰብዓዊ ነጻነት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለ መግለጻቸውን ያስታወሰው ሰነዱ በመሆኑም የእምነት ነጻነት ለአማኞች ብቻ ሳይሆን ለመላው ሰብዓዊ ፍጥረት የሚያገለግል ነው ማለታቸውን አስታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዓለማዊ አስተሳሰብ ከሚያራምዱ መንግሥታ ጋር ሊኖር ስለሚገባ አንድነት አስመልከተው ባቀረቡት ሃሳብ የእምነት ነጻነትን ለማስከበር የሚደረጋ ጥረት የአማኞች እና የመንግሥት የጋራ ጥረት መሆን ያስፈልጋል ማለታቸውን ሰነዱ አስታውሷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የእምነት ነጻነት አምባ ገነናዊ ሥርዓትን ለመዋጋት ያስፈልጋል፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእምነት ነጻነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ መሆኑን ገልጸው፣ ለሌሎችም ሰብዓዊ ነጻነቶች መሠረት በመሆን፣ አምባ ገነናዊ ሥርዓትን ለመዋጋት እና በሰዎች መካከል ወንድማማችነትን ለማሳደግ የሚያግዝ መሣሪያ እንደሆነ መናገራቸውን ያስታወሰው ሰነድ የዘመናችንን ሰማዕታት፣ በእምነታቸው ምክንያት ስቃይንና መከራን የሚቀበሉ በርካታ ሰዎች በዓለማችን ዙሪያ መኖራቸውን፣ እግዚአብሔርን የሚቃወሙ የዘመናችን አስተሳሰቦች ለመቃረን የእምነት ነጻነት መኖሩ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ሰነዱ አስታውሷል።

ለሕሊና የመገዛት መብት፣

ቤተክርስቲያን የእምነት ነጻነት እንዲኖር የበኩሏን ጥረት የምታደርገው ምዕመናኖቿ እምነታቸውን በነጻነት የሚገልጹበትን፣ ለሂሊናቸው የመገዛት መብትን በማክበር እና የሌላውንም መብት የማክበር ግዴታን ተግባራዊ እንዲያድረጉ በማሰብ ነው። ማሕበራዊ ሕጎችም ቢሆኑ ሰዎች ለሕሊናቸው የመታዘዝ ወይም የመገዛት መብታቸው ኣንዲከበርላቸው የሚያደርጉ መሆን ይኖርባቸዋል።

የእምነት ነጻነትን ጥሰት፣

በአንዳንድ አገሮች የእምነት ነጻነትን የሚያስጠብቅ ሕግ አለመኖሩን እና የእምነትን በጋራ ሆነው የመለማመድ መብት በጣም የተገደበ በመሆኑ በግል ደረጃ ብቻ የሚከናወን መሆኑን ሰነዱ አስታውሷል። በእነዚህ አገሮች እምነታዊ ሃሳብን በአደባባይ መግለጽ፣ የሞት ቅጣት ፍርድን ጨምሮ ለከፍተኛ ቅጣት እንደሚዳርግ፣ ቅጣቶቹ የሚጸኑት እምነታቸውን በሚቀይሩ ሰዎች ላይ እና እምነታቸውን እንዲቀይሩ በሚያደረጉ ሰዎች ላይ የሚፈጸም መሆኑን ሰነዱ ገልጿል። አምባ ገነናዊ ሥርዓትን በሚያራምዱ አገሮች ዘንድ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በሚያራምዱ አገሮች ዘንድም ቢሆን የክርስቲያን ማሕበረሰብ ግፍ እንደሚፈጸምባቸው፣ በሥራ ገበታቸውም ጭቆና እንደርስባቸው እና ከሥራቸው እንደሚባረሩ፣ ማሕበራዊ አገልግሎትንም እንዳያገኙ የሚደረጉ መሆናቸውን ሰነዱ አብራርቷል። የሕክምና እና የትምህርት አገልግሎትን የሚሰጡ የሐይማኖት ተቋማት ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው እና የሚያበረክቱት አገልግሎትም የሚገደብ መሆኑን ሰነዱ አስታውሷል።

የወንጌል ተልዕኮ እና በሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረግ ውይይት፣

በሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረግ ውይይት ሰላማዊ እና የእምነት ነጻነትን ያገናዘበ በመሆን የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች በሕብረት ሆነው ለጋራ ጥቅም የሚያደርጉት ውይይት ቤተክርስቲያን የወንጌል አገልግሎት ተልዕኮን ስኬታማ ለማድረግ በምታደርገው ጥረት መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል።

ክርስቲያን ሰማዕት ጥላቻብ በፍቅር ያሸንፋል፣

ሰማዕትነት ጥላቻን ያስወገደ የእምነት ምስክርነት መሆኑን የገለጸው ሰነድ ክርስቲያኖች ለእምነታቸው ያላቸውን ጽኑ ታማኝነት የሚገልጹበት መንገድ፣ የጥላቻ፣ የማስፈራሪያ እና የስቃይ ድርጊት የሚፈጸምበት መሆኑን ሰነዱ አስረድቶ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሰማዕትነት የእምነት ነጻነት የሚገለጥበት ፍቅር ጥላቻን የሚያሸንፍበ፣ ሰላም አመጽን የሚያሸንፍበት ምልክት ሆኖ እንደሚገኝ ሰነዱ አስታውቋል። ብዙን ጊዜ ለእምነታቻ ሲሉ ሰማዕትነትን የሚመርጡ ሰዎች ምስክርነት በርካታ ሰዎች ለእምነታቸው ነጻነትን የሚያገኙበት፣ ጥላቻንም በፍቅር የሚያሸንፉበት መልካም ፍሬ እንደሚሆን ሰነዱ አብራርቷል።

ቤተክርስቲያን የግለሰብ እምነት እና የጋራ ጥቅም ታከብራለች፣

ክርስትና የድነት ታሪክ በቤተክርስቲያን ብቻ ተገድቦ እንዲቀር አያደርግም ያለው ሰነዱ ጠቅላላ የሰው ልጅ ታሪክ በእግዚአብሔር የፍቅር ታሪክ ብርሃን እንደሚገለጥ፣ የሰው ልጆች በሙሉ እግዚአብሔር ላዘጋጀው ድነት የተጠሩ መሆናቸውን እና እውነቱንም እንዲያውቁ ተጠርተዋል (1ኛ ጢሞ. 2፤4)። የቤተክርስቲያን የወንጌል ተልዕኮ፣ በእምነት ምስጢር ውስጥ እንደተጠቀሰው በግዴታ የሚገለጽ ሳይሆን  ከእግዚአብሔር የተሰጠ የጸጋ ስጦታ፣ የነጻነት በረከት መሆኑን ሰንዱ ያስረዳል። ቤተክርስቲያን ወንጌልን ለማብሠር የምትከተልበት መንገድ የግለሰብን እምነት፣ የጋራ ጥቅምን የሚያከብር እነደሆነ እና እምነትን በመመስከር የምታስተምረው የድነት መንገድ ግልጽ እና ራሱን በስጣን ከፍ ከሚያድረግ መንፈስ የራቀ መሆኑን ሰነዱ አስረድቷል።

ወንጌልን የመቀበል ነጻነት፣

ሰንዱ በማጠቃለያው የእግዚአብሔር መንግሥት በዘመናት ታሪክ ሁሉ ሥራውን በማከናወን ላይ እንዳለ እና በመጨረሻው ዘመንም  ለእኛ  እንደሚገለጽ ገልጾ መንፈስ ቅዱስም “ና” (ዮሐ. ራዕይ 22.17) “እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን” (ሮሜ 8፤22)። “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” (ዮሐ. ራዕይ 21፤5)፣ ወደ ዓለም በሙሉ የእምነት ጽናትን (ሮሜ 8፤1-27) “በሰው ልጆች ሁሉ ላይ እንዲሆን አድርግ” (1ኛ ጴጥ. 3፤5) “የእምነት ነጻነትም ለሁላችን እንዲሆን እንድንሰማው እና እንድንከተለው አድርገን”።      

27 April 2019, 18:22