ታዳጊ ሕጻናትን ከጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚቻል የሚወያይ ስብሰባ ተጀመረ  ታዳጊ ሕጻናትን ከጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚቻል የሚወያይ ስብሰባ ተጀመረ  

ታዳጊ ሕጻናትን ከጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚቻል የሚወያይ ስብሰባ ተጀመረ

ከየካቲት 14-17/2011 ዓ.ም ለአራት ቀናት ያህል የሚቆይ ታዳጊ ሕጻናትን ከጥቃት እዴት መከላከል  እንደ ሚቻል የሚወያይ ስብሰባ በቫቲካን መጀመሩ ታውቁዋል። በዚህ ስብሰባ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ጨምሮ በርካታ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ብጹዕን ጳጳሳት ይህንን ስብሰባ ለመታደም በቫቲካን መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ስብሰባ ለተሰብሳቢዎቹ አዳዲስ ዕድሎችን ያቀርባል፣ ከዚህ ቀደም ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች የደረሰባቸውን በደል ያዳምጣል፣ ኃላፊነት፣ ተጠያቂነት እና ግልጽነት የተላበሰ አስራር ይከተሉ ዘንድ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚረዳ ስብሰባ መሆኑን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ-መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ለታዳጊ ሕጻናት ጥበቃ ማድረግ” የሚለው ደግሞ የዚህ ስብሰባ ዋነኛው የመወያያ አርዕስት ነው። ይህ ስብሰባ በሕጻናት እና በታዳጊዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን “እንዴት መከላከል ይቻላል? መገለጫዎቹስ ምንድናቸው?”  በሚሉት ጭብጦች ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባሻገር በአደባባይ እና በተዘዋዋሪ በድብቅ የሚፈጸሙ በጭካኔ የተሞሉ ጥቃቶችን እና ድርጊቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መዋጋት እንደ ምትችል፣ ይህ ጥቃት የሚያስከትለው ከፍተኛ መዘዝ በግልጽ የሚዳሰስበት እና በመጨረሻም ይህንን ድርጊት መከላከል የሚቻልበት የአቋም መግለጫ የሚወጣበት ስብሰባ እንደ ሆነ ይጠበቃል።

የእዚህ አሰቃቂ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ምስኪን ልጆች እና ወጣቶች ድምጻቸው በፍጹም ሳይሰማ አይቀርም። ለረዥም ጊዜ የዘለቀው የስቃይ ለቅሶ ዝምታው ተሰብሮ ለጉዳዩ አፋጥኝ የሆነ መፍትሄ እንዲፈለገ መንገዱን ከፍቱዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት የዚህ በተለይም የተለያዩ ጥቃቶች ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ጋር  በተደጋጋሚ ተገናኝተው ሐዘናቸውን ማዳመጣቸው እና አብረዋቸው ጸሎት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን የዚህ አሁን የተጀመረው ስብሰባ ዋነኛው ዓላማ በተለይም ደግሞ ቀሳውስት እና የሃይማኖት አባቶች በዚህ ዓይነት አጸያፊ ድርጊቶች ውስጥ ተሳታፊ እንዳይሆኑ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባሻገር ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ ግለሰቡ እና ግለሰቡ ብቻ ተጠያቂ እንደ ሚሆን፣ ይህም በሕግ አግባብ እርምጃ የሚያስወስድ ድርጊት መሆኑን አጽኖት በመስጠት የሚያሳስብ ስብሰባ ነው። የጥቃቱ ሰለባ ሰዎች ምስክርነት መስማት በራሱ በቂ አይደለም፣ ነገር ግን በተፈጸመባቸው ጥቃት የተነሳ የደረሰባቸውን መከራ እና ሐዘን መካፈልን ያካትታል፣ በእነርሱ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ተግባር በሚገባ በመረዳት ሐዘናቸውን በተገቢው ሁኔታ በመረዳት የዚህ ዓይነቱ ድርጊት በድጋሚ እንዳይፈጠር፣ የዚህ ዓይነት ድርጊት ተፈጽሞ በሚገኝበት ወቅት ድርጊቱን ከመደበቅ ይልቅ ይፋ በማድረግ ለሕግ ማቅረብ እንደ ሚገባ ግንዛቤን ማስጨበጥ የሚያስችል አእምሮን ይከፍታል ተብሎ የሚታሰብ ስብሰባ ነው።

በዚህ ስብሰባ ላይ በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በተመለከተ ጉዳዩ በተለያዩ ልምዶች እና ባህሎች መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ በማሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረገ ስብሰባ ነው። ይህ ስብሰባ በመጀመሪያው ቀን ሐዋርያዊ፣ መንፈሳዊ እና ሕጋዊ ኃላፊነትን በተመለከተ ለብጹዕን ጳጳሳት ማብራሪያ በመስጠት ብጹዕን ጳጳሳት የተሰጣቸውን “ኃላፊነት” እንዴት መወጣት እንደ ሚኖርባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች ይካሄዳሉ። በሁለተኛው ቀን ስብሰባ ደግሞ  "ተጠያቂነትን" በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች እንደ ሚካሄዱ የተገለጸ ሲሆን ጥቃቶች በሚፈጸሙበት ወቅት ጥቃቱን በፈጸመው ግለሰብ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያላደርጉ ሰዎች ላይ እንዝላልነትን በማሳየታቸው የተነሳ ሊወሰድ ስለሚገባው ቅጣት በተመለከተ ሕገ ቀኖናን በማጣቀሻነት በመጠቀም ውይይቶች ይደረጋሉ። ይህ አሁን በቫቲካን እየተካሄደ የሚገኘው ስብሰባ በሦስተኛው ቀን ውሎ ደግሞ “ግልጽነትን” በተመለከተ በሰፊው የሚወያይ እንደ ሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ማነኛቸው ዓይነት በሕጻናት እና በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ አካላዊ ጥቃቶች ይህንን ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ የቤተ ክርስቲያንን ውስጣዊ ሕገ ደንብ በጠበቀ መልኩ የሲቪክ ማኅበረሰቡ በሚተዳደርበት ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆን ዘንድ አሳልፎ የመስጠት ግዳታን በተመለከተ ጥልቅ ውይይቶች ይደረጋል። ይህ ስብሰባ የተለያዩ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በሚቀጥለው እሁድ እንደ ሚደመደም ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

21 February 2019, 14:18