ፈልግ

Visita del cardinal Sandri in Libano Visita del cardinal Sandri in Libano 

በሊባኖስ የቤተ ክርስቲያን እርዳታ አቅርቦት ሥራ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ተከበረ።

በሊባኖስ ካሪታስ የተሰኘ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እርዳታ ሰጭ ድርጅት ዳይረክተር የሆኑት አባ ጳውሎስ ካራም፣ ስደተኛ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ተጠልለው ከሚገኙባቸው ስድስት ማዕከላት መካከል አንዱ ወደ ሆነው ወደ ቡሪ ሃሙድ ጉብኝት ማዘጋጀታቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በመካከለኛው የምስራቅ አገሮች የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእርዳታ አቅርቦት ሥራ የተጀመረበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መንፈሳዊ ንግደት ያለፈው እሁድ በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማዕከል ውስጥ ከችግረኛ ቤተሰብ ክፍሎች ጋር በተደረገው የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት መጀመሩን ከሊባኖስ የደረሰን ዜና አመልክቷል። በእራት ግብዣው ስነ ስርዓት የማዕከሉን የአገልግሎት ሂደት አስመልክተው ወይዘሮ ጆሰፊን ገለጻ ማድረጋቸው ታውቋል። በእራት ግብዣው የአርመን ካቶሊክ ፓትሪያርክ ግረጎሪዮ ጴጥሮስ 20ኛ፣  የሶርያ ካቶሊካዊ ፓትሪያርክ ዩናን እና የኢራቅ ስደተኛ ሕጻናት የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም በመካከለኛው የምስራቅ አገሮች የሚገኙ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእርዳታ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችም መገኘታቸው ታውቋል። በሊባኖስ ውስጥ በርዌሳት ከተማ የሚገኙ የመልካም እረኛ ደናግል በቀን ከ150 በላይ፣ ከእነዚህም በርካታ ቁጥር ያለው የሙስሊም ማሕበረሰብ የሕክምና አገልግሎትን ወደሚያገኙበት ማዕከል ጉብኝት መደረጉ ታውቋል።

በሊባኖስ ካሪታስ የተሰኘ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እርዳታ ሰጭ ድርጅት ዳይረክተር የሆኑት አባ ጳውሎስ ካራም፣ ስደተኛ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ተጠልለው ከሚገኙባቸው ስድስት ማዕከላት መካከል አንዱ ወደ ሆነው ወደ ቡሪ ሃሙድ ጉብኝት ማዘጋጀታቸው ታውቋል። በዚህ ማዕከል ውስጥ ከተለያዩ አገሮች ለቤት ሥራተኛነት ብለው ወደ ሊባኖስ የመጡ ወጣት ሴቶች፣ ከመጡ በኋላም ብዙ ችግሮችን ያሳለፉ መሆናቸውና በሚኖሩበት ማዕከልም የተለያዩ የቋንቋና የሞያ ስልጠናን በመውሰድ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

የአርመን ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሁኔታ በሊባኖስ፣

የአርመን ካቶሊክ ፓትሪያርክ ግረጎሪዮ ጴጥሮስ 20ኛ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚገኙ የአርመንያ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶችም ልዑካን በክብረ በዓሉ ላይ መገኘታቸው ታውቋል።

ከኢራቅ ስደተኞች ጋር የተደረገ ግንኙነት፣

በክብረ በዓሉ ወቅት በሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ የኢራቅ ስደተኛ ሕጻናት ትምህርታቸውን ወደሚከታተሉበት ትምህርት ቤት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በዚህም ወቅት ከሕጻናት ተማሪዎች በኩል ዕርዳታን በማቅረብ ላይ ለሚገኙት ተቋማት በሙሉ ምስጋና ቀርቦላቸዋል። በሊባኖስ የኢራቅ ስደተኛ ሕጻናት ተንከባካቢ የሆኑት የሶርያ ካቶሊካዊ ፓትሪያርክ ዩናን፣ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችን ተቀብለው ተማሪዎቹ የሚስተናገዱበትን ማዕከላት ማስጎብኘታቸው ታውቋል።

ካርዲናል ራይና ሳንድሪ መስዋዕተ ቅድሴን ማድረጋቸው፣

በሊባኖስ የቅድስት መንበር እንደራሴ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ስፒተሪ፣ በሊባኖስ የሃሪሳ ኖተር ዳም ካቴድራል የመስዋዕተ ቅዳሴን ስነ ስርዓት የመሩ ሲሆን በመስዋዕተ ቅዳሴው ስነ ስርዓት ላይ ብጹዕ ካርዲናል ሳንድሪ፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የምስራቅ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያኖች ጉዳይ ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ መገኘታቸው ታውቋል። በስነ ስርዓቱ ብጹዕ ካርዲናል ራይ በሊባኖስ ከሃምሳ ዓመንት በፊት የተቋቋመው የዕርዳት ማቅረብ አገልግሎትን በአካባቢው ለምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሰፊ የአገልግሎት ዘርፍ እንደሆነ ጠቅሰው ቤተክርስቲያንም በመካከለኛው የምስራቅ አገሮች እንድታበረክት በተጠራችበት የአገልግሎት ዘርፍ፣ የእግዚአብሔር ምሳሌ በመሆን፣ በትህትናና በየዋህነት፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በሙሉ ሳታቋርጥ እርዳታን ማቅረብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።                     

14 November 2018, 15:11