2018.10.26 Festa dei Giovani Sinodali 2018.10.26 Festa dei Giovani Sinodali 

ወጣቶች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በዓል ማክበራቸው ተገለጸ።

በማንኛውም የችግር ወቅት፣ ከእርስዎና ከቤተክርስቲያናችን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር ነን በማለት 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስን አጥቃላይ መደበኛ ጉቤን የተካፈሉ ወጣቶች፣ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድጋፋቸውን ሰጥተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል። ወጣቶቹ በተጨማሪም በጳጳሳት ጉባኤ ወቅት በቫቲካን ባደረጉት ቆይታ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የጠብቀ ወዳጅነት መፍጠራቸውን ገልጸው እንደዚሁም ከብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አባቶች ጋር በቅርብ ሆነው ሲመክሩና ሲወያዩ በመቆየታቸው አጭር ታሪክ ሰርተናል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

15ኛውን የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የተካፈሉ ወጣቶች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በዓል ማክበራቸው ተገለጸ።

ከመስከረም 23 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ በደበኛ ጉባኤ ከመጠቃለሉ አንድ ቀን አስቀድሞ ማለትም ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ. ም. ሲኖዶሱ የምክር ቤት አባቶችን መምረጡ ታውቋል። ምርጫውን ካርዲናሎችን ጨምሮ 249 ብጹዓን ጳጳሳት የተካፈሉ መሆናቸው ታውቋል። ወጣቶችም በዚህ የተሰማቸውን ደስታ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ሆነው የገለጹበት ደማቅ በዓል መከበሩ ታውቋል።

ዛሬ 20ኛና የመጨረሻ ዙር ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከጉባኤው ቀጥሎ በተዘጋጀው በቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ ስርዓት ላይ “ቅዱሱ አባታችን፣ እናመሰግናለን” በማለት  ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። መላው የሲኖዶሱ ተካፋዮች፣ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ጋር በጋራ በመሆን ባቀረቡት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ በተለዩዩ ቋንቋዎች ዝማሬዎችን በማቅረብ ከወትሮ በተለየ መልኩ ብጹዓን አባቶች ደስታቸውን ገልጸዋል። የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ሎረንሶ ባልዲሰሪ በመስዋዕተ ቅዳሴው ወቅት የቀረቡትን መዝሙሮች በፕያኖ የሙዚቃ መሣሪያ ማጀባቸው ታውቋል።

አጭር ታሪክ ተሠራ፣

በምንኛውም የችግር ወቅት፣ ከእርስዎና ከቤተክርስቲያናችን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር ነን በማለት 15ኛ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስን አጥቃላይ መደበኛ ጉቤን የተካፈሉ ወጣቶች፣ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድጋፋቸውን ሰጥተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል። ወጣቶቹ በተጨማሪም በጳጳሳት ጉባኤ ወቅት በቫቲካን ባደረጉት ቆይታ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የጠብቀ ወዳጅነት መፍጠራቸውን ገልጸ እንደዚሁም ከብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አባቶች ጋር በቅርብ ሆነው ሲመክሩና ሲወያዩ በመቆየታቸው አጭር ታሪክ ሰርተናል ብለዋል። የጉባኤው ተሳታፊ ወጣቶች ፊርማቸውን ባሰፈሩበት መልዕክታቸው ላይ እንደገለጹት አዳዲስ ሃሳቦች መቅረብ አለባቸው፣ ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸውን መድረክ ወይም ስፍራን አዘጋጅተውልናል በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በደስታ አምስገነዋቸዋል። ወጣቶቹ በመልዕክታቸው፣ የዛሬው ዓለም ገና ያልተነኩ በርካታ ችግሮች ስላሉት፣ አዳዲስ የማቃለያ መንገዶችን፣ አዲስ የፍቅር ጉልበትን ይጠይቃል። የትሻለ ዓለምን ለመገንባት ከመቀበል ይልቅ በስጠትን የሚገኘውን ደስታ የማግኘት ተስፋ እንዲኖረው ያስፈልጋል። በምሆኑም እርስዎ የጀመሩትን ጉዞ ይቀጥሉበት፣ በጸሎታችን እናግዝዎታለን፣ ሃሳብዎትንና ህልምዎትን እንጋራዎታለን፣ ሁሉን የምታቅፍ፣ የሁሉ የሆነች በተለይም ደግሞ ለተናቁት ለተጠሉትና ለተቸገሩት የቆመች ቤተክርስቲያንን እንፈልጋለን በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ወጣቶች ከና ከጅምሩ በቤተክርስቲያናቸው ሆነው የተሻለ ሕብረተሰብ ለመገንባት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው ሁሉ የደሄዩትን፣ የታመሙትንና የተጨቆኑትን በማገልገል፣ የሰላምና የአንድነት ባሕልን ለመገንባት ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸዋል። 

15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ፣ ነገ እሑድ ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ. ም. ጠዋት መላው የሲኖዶሱ ብጹዓን አባቶች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ሆነው በሚያሳርጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።  

27 October 2018, 17:34