ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሲኖዶስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቅ. ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሲኖዶስ መስዋዕተ ቅዳሴ በቅ. ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደበት ወቅት  

አቡን ሬኖ ፊዚኬላ “ጴጥሮስ እስከ መጨረሻው ድረስ ለኢየሱስ ጥሪ ታማኝ በመሆን ሕይወቱን ሰቱዋል”

ከባለፈው መስከረም 23/2011 ዓ.ም እስከ ሚቀጥለው እሁድ ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም “ወጣቶች፣ እምነት እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል 15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን የዚህ ሲኖዶስ ተካፋይ የሆኑ ብጽዕን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ወጣቶች እና ተጋባዥ እንግዶችን ያካተተ ስድት ኪሎሜትር የሚሆን መንገድ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 15/2011 ዓ.ም በመጓዝ መንፈሳዊ ንግደት በማድረግ በቫቲካን ወደ ሚገኘው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የሲኖዶሱ ተከፋዮች በእግር ማቅናታቸውን ለመራዳት የተቻለ ሲሆን በሮም የሰዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ መካፈላቸው እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ መደረጉን ከስፍራው ከደርሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።  

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ በመስዋዕተ ቅዳሴ ላይ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ዛሬ የጀመርነውን መንፈሳዊ ጉዞ እዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ መካነ መቃብር በሚገኝበት ስፍራ ተገኝተን፣ የእግዚኣብሔርን ቃል ካዳመጥን በኋላ ማጠናቀቃችን ለሕይወታችን ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጠው ክስተ ነው” ብለዋል።

አሁን በመካሄድ ላይ በሚገኘው እና ለወጣቱ ትውልድ ትኩረት በሰጠው ሲኖዶስ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ በመንፈስ ከእኛ ጋር እየተካፈለ ይገኛል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ፣ በጸሎተ ሐይማኖት ጸሎት እንደ ምንደግመው በሕይወታችን ውስጥ የቅዱስ ጴጥሮስን ሕይወት እና መንፈሳዊ ጥሪ የተላበሰ ትርጉም ያለው ሕይወት ልንኖር ይገባናል ብለዋል።

እዚህ አሁን በምንገኝበት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት እንደ ሚገልጹ ያወሱት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ በዚህም መልኩ ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን እንዴት መኖር እንደ ሚገባን ያሳየናል ብለዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ “ጴጥሮስ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ሥፋራ ትሄድ ነበር” (ዮሐ. 21፡18) በማለት ኢየሱስ ለጴጥሮስ መናገሩን አስታውሰው ይህ ጉዳይ እኛ አሁን ባለንበት ዘመን እንዲከሰት የምንመኘው ጉዳይ መሆኑን ጨምረው ገለጸው “ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ሰው ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ሥፋራ ይወስድሃል” ብሎ እንደ ተናገረው አስታውሰዋል።

ነገር ግን እነዚህን ኢየሱስ ለጴጥሮስ የተናግራቸውን ቃላት በሚገባ ለመረዳት ከጥቂት ዓመታት በፊት የተከሰተውን ነገር በቅድሚያ መመልከት ይኖርብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት ውስጥ የተቀሰውን ሰለ ጴጥሮስ የመጀመሪያ ጥሪ የሚያወሳውን ታሪክ መመልከት ይኖርብናል ብለዋል። በወቅቱ ጴጥሮስ ምሽቱን በሙሉ ዓሳ ሲያጠምድ ነበር፣ ነገር ግን አንዲት ዓሳ እንኳን መያዝ እንዳልቻለ በስብከታቸው የጠቀሱት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ ኢየሱስ ወደ እርሱ ቀርቦ “በጀልባህ ላይ ተስፈር፣ መረብህንም ወደ ባሕሩ ጣል” ብሎ ኢየሱስ እንደ ነገረው አስታውሰው ምንም እንኳን ጴጥሮስ ከዚህ ቀደም ኢየሱስን በዓይኑ አይቶት ባያውቅም ነገር ግን ከዚያች የመጀመርያ ግንኙነት በኋላ ኢየሱስን ወዶት እንድ ነበረ ጨምረው ገለጸዋል።

በወቅቱ ወጣት የነበረው ኢየሱስ በሙያው ዓሳ አጥማጅ የነበረውን እና ሌሊቱን በሙሉ ዓሳ ስያጠምድ ያነጋውን ጴጥሮስን  በድጋሚ መረብህን በዚህ በኩል ጣል ብሎ በነገረው ወቅት ጴጥሮስ “አንተ አናጺ ነህ፣ እኔ ግን ዓሳ አጥማጅ ነኝ ብሎ” እንዳልመለሰለት በስብከታቸው የገለጹት አቡነ ሬኖ ፍዚኬላ “ጴጥሮስ አንተ ስላልከኝ መረቤን ወደ ባሕሩ ወረውራለው” በማለት የኢየሱስን ቃል በእመንት እንደ ተቀበል ገለጸዋል።

ምንም እንኳን ጴጥሮስ ከዚህ ቀደም ኢየሱስን አይቶት ባያውቅም ቅሉ በዚህ ተግባሩ ከኢየሱስ የመጀመሪያውን የእመነት ትምህርት ቀስሞ እንደ ነበረ ገልጸው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በ15ኛው ምዕራፉ ላይ “ያለኔ ምንም ነገር ማከናወን አትችሉም። በእኔ የሚኖር እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል” የሚለውን የኢየሱስን ቃል አስታውሰው በዚህም መስረት ቅዱስ ጴጥሮስ ቀስ በቀስ ይህንን ጉዳይ በመረዳት ማመን እንደ ሚገባው በመረዳት፣ በተለይም ደግሞ የእግዚኣብሔ ጸጋ እንደ ሚያስፈልገው በገልጽ መረዳቱን ገለጸዋል።

እኛም ያለ እርሱ እርዳታ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፣ ብዙን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ ይወርድ ዘንድ በምናቀርበው የመማጸኛ ጸሎት ላይ “ያለ አንተ፣ ያለ አንተ ብርሃን ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” በማለት የመማጸኛ ጸሎት እንደ ምናቀርብ ሁሉ ጴጥሮስም በኢየሱስ ማመን ፍሬያማ እንደ ሚያደርግ አስቀድሞ በመረዳት ኢየሱስ ባዘዘው መልኩ መረቡን በመጣል ፍሬያማ ሊሆን እንደ ቻለ አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ በስብከታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ከሚገባው እና ካሰበው በላይ በጣም ብዙ ዓሳ መያዙን የተረዳው ጴጥሮስ “እባክህን ከእኔ ራቅ፣ እኔ ከአንተ ጋር ለመሆን የተገባው ሰው አይደለሁኝም” ብሎ ጴጥሮስ በተናግረበት ወቅት ኢየሱስም በበኩሉ “ጴጥሮስ ሆይ አትፍራ! እኔ ሰዎችን እንድታጠምድ አደርግሃለሁ፣ በእኔ መተማመንህን ቀጥል፣ ከእኔ ጎን መጓዝህን ቀጥል፣ ከእኔ እንዳትለይ” ብሎ ተናግሮት እንደ ነበረ አስታውሰዋል።

ይህ ታሪክ እኛ ወጣቶች በነበርንበት ወቅት የነበረንን መልካምነት፣ ፍጥነት፣ ኅብረት፣ ሰው በተቸገረበት ሥፍራ ሁሉ ተገኝተን ለመርዳት . . . ወዘተ የነበረንን የወጣትነት ፍላጎት እንደ ሚያስታውስ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ ጴጥሮስ ሁሉንም ነገር ወደ ኋላ በመተው ኢየሱስን መከተል መጀመሩን ጨምረው ገለጸዋል።

በዚህ መልኩ ለሚቀጥሉት ሦስት አመታት ያህል ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር በነበረው ቆይታ በተለያየ መልኩ ለኢየሱስ የነበረውን ታማኝነት ገልጾ እንደ ነበረ ያስታወሱት አቡን ሬኖ ፊዚኬላ በጌተ ሰማኒ በአትክልቱ ቦታ ወታደሮች ኢየሱስን ለመያዝ በመጡበት ወቅት ጴጥሮስ ጎራዴውን አውጥቶ የአንድ ወታደር ጆሮ በቆረጠበት ወቅት ኢየሱስ ይህ አመጽ ተገቢ እንድዳልሆነ ለጴጥሮስ ነገሮት እንደ ነበረ አስታወሰው ጴጥሮስ ቀስ በቀስ አዳኝ እርሱ ስይሆን ነገር ግን ኢየሱስ እና እግዚኣብሔር ብቻ አዳኝ መሆናቸውን ተረድቶ እንደ ነበረ ገለጸዋል።

ነገር ግን በስተመጨረሻ አከባቢ ኢየሱስ ሞት በተፈረደበት ወቅት ጴጥሮስ ኢየሱስን ክዶት እንደ ነበረ በመገለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ ኢየሱስ ከሙታን በተነሳበት ወቅት ዮሐንስ እና ጴጥሮስ ወደ መቃብሩ እየሮጡ በሄዱበት ወቅት ኢየሱስ ጴጥሮስን “ለምንድነው እርሱ የካድከኝ?” ብሎ እንዳልጠየቀው ገለጸዋል። ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ጴጥሮስን በጠራበት ወቅት “ጴጥሮስ ሆይ ትወደኛለህን? ብሎ እንደ ጠየቀው አስታውሰው ጴጥሮስም አዎን ጌታ ሆይ እንደ ምወድህ አንተ ራስህ ታውቃልህ ብሎ ሦስት ጊዜ እንደ መለሰለት እና ይህም ጥሪ የፍቅር ጥሪ እንደ ነበረ አስታውሰዋል።

ጴጥሮስ ለዚህ ለኢየሱስ ፍቅር እና ጥሪ እስከ መጨረሻ ቀን ድረስ ራሱን አሳልፎ እስከ መስጥት ድረስ ታማኝ ሆኖ መቆየቱን በስብከታቸው ያወሱት አቡነ ሬኖ ፊዚኬላ አሁን እኛ የምንኖርበት ዘመን ሐዋርያዊ ጴጥሮስ ከነበረበት ዘመን ጋር ተመሳሳይ ባይሆንም ነገር ግን እኛም ለኢየሱስ ጥሪ በታማኝነት ተመሳሳይ ምላሽ መስጠት እንችል ዘንድ ልያግዘን ወደ እኛ እንደ ሚመጣ ገልጸው ይህንን የቅዱስ ጴጥሮስ አብነት በመከተል እኛም ሕይወታችን ለጌታ መስጠት እንችል ዘንድ አማላጅነቱን ልንማጸን እንደ ሚገባ ከገለጹ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
25 October 2018, 15:30