ፈልግ

Arcivescovo Bernadito Auza, Osservatore Permanente della Santa Sede presso le Nazioni Unite a New York, ad un evento a ONU il 4 giugno 2018 Arcivescovo Bernadito Auza, Osservatore Permanente della Santa Sede presso le Nazioni Unite a New York, ad un evento a ONU il 4 giugno 2018 

ቅድስት መንበር ሰላምንና በውስጥዋ ያሉትን ሁሉ መንከባከብ እንደሚያስፈለግ ኣስታወቀች።

የቫቲካኑ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኣውዛ በዓለም ኣቀፍ በተለያዩ ደረጃዎች ስለ ተፈጥሮ ከሚሠራው ቡድን ጋር የተወያዩ ሲሆን በቀጣይም ቀናትም በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ከክልል ውጭ ባሉ የባሕር ግዛቶች መብት ላይ በዚሁ በኒውዮርክ በሚገኘው መስታወታማው ሕንፃ ተወያይተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

በተናንትናው ዕለት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ተጠሪ ሞንሲግኖር በርናዲቶ ኣውዛ በኒውዮርክ በመስታወቱ ሕንፃ ውስጥ በሁለት በተለያዩ ቃለ ምልልሶች ኣንዳስረዱት ሰላምና ሥነ-ተፈጥሮኣዊ እንዲሁም የኣካባቢ እንክብካቤ ለምንኖርባት ምድር መበልፀግ ከፍተኛ የሆነ እገዛ እንዳላቸው የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ሮበርታ ጂሶቲን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ሞንሲግኖር በርናዲቶ ኣውዛ የሰላምን ባሕል መጠበቅ ሰላምን በሁሉ ቦታ ለማስፈን ከሚደረገው ርብርብ ጎን ለጎን ሰለ ሰው ልጅ ክብርና ሰለ ሰው ልጆች መብት ኣጠባበቅ መታገል የተባበሩት መንግሥታት ዋነኛና ተቀዳሚ ዓላማዎች እንደሆኑ ኣስረድተዋል። በተባበሩት መንግሥታት በከፍተኛ ደረጃ በተዘጋጀው የሰላም መድረክ ላይ ተወካዩ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በዚህ ረገድ ያላቸውን ተነሳሽነት በማመስገን የእርሳቸውን ቃል እንዲህ በማለት ኣሰምተዋል።

በዓለም ላይ በሚደረጉ የተለያዩ የመንግሥታት ግጭቶች እንዲሁም የዓለም ጦርነቶች በዚሁም ጦርነት ወቅት የምንጠቀማቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተለያዩ የፀረ-ሽብርተኝነት እርምጃዎች የአምባገነን ስርዓቶች የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችና ሕገ ወጥ እርምጃዎች በሙሉ የሰውን ልጅ ስላምና የምድርን የተፈጥሮ ሁኔታ ከማዛባትና ከማዉደሙም በላይ በዚሁ ሳቢያ ብዙ ሲዎች በተለይም ሕፃናትና በእድሜ የገፉ ሰዎች ያለ ጧሪ ቀባሪ እንደሚቀሩና ኣብዛኞቹም የትውልድ ሃገራቸውን በመተው ለስደትና ለተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች እንደሚጋለጡ ኣስረድተዋል።

የዚሁ የቫቲካኑ ተወካይ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኣውዛ በዓለም ኣቀፍ በተለያዩ ደረጃዎች ስለ ተፈጥሮ ከሚሠራው ቡድን ጋር የተወያዩ ሲሆን በቀጣይም ቀናትም በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ከክልል ውጭ ባሉ የባሕር ግዛቶች መብት ላይ በዚሁ በኒውዮርክ በሚገኘው መስታወታማው ሕንፃ ተወያይተዋል። ሊቀ ጳጳስ ኣውዛ እ.ኣ.ኣ. በመጋቢት 24 2015 የወጣዉን ላዉዳቶ ሲ ወይ ክብር ላንተ ይሁን ተብሎ የተተረጎምርዉን የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስን ሰነድ በመጥቀስ ይህ ዓለምንና የተፈጥሮን የመብት ሁኔታ ከመጠብቅ ኣኳያ የሚታየዉን ክፍተት በማስወገድ እንደውም ዓለምንና የተፈጥሮን ሁኔታ ይበልጥ ለማሻሻል ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

እኚሁ የዚሁ የቫቲካኑ ተወካይ እንደገለጹት የኑሮኣችን ዓይነት የምናመርታቸውና የምንጠቀማቸው ነገሮች በሙሉ በምንኖርበት ምድር እንዲሁም በዙሪኣችን በሚገኙ የተለያዩ ኣገሮች ላይ ኣዎንታዊም ይሁን ኣሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ ስለሆነም ይህ መሠረታዊ ጉዳይ ነውና በነገሩ ላይ ጠለቅ ያለ ጥናትና ጊዜ ተሰቶት ይበልጥ ሊሰራበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ ኣውዛ በመቀጠልም በዚህ ከተፈጥሮ እንክብካቤ በተጓዳኝ ከባሕር ክልል ውጭ ያለን የተፈጥሮ ዉኃን በመጠቀም ረገድ የዓለም ኣቀፍ ሕግና ስምምነቶችን በተከተለ መልኩ እንዲሆንና ይህ ከተላያዩ

ፋብሪካዎች በሚወጡ ተረፈ ምርቶች የሚከሰተው የባሕር ብክነትም ተገቢውን ክትትል በተገቢው ባለሥልጣን መደረጉ በምድራችን ላይ ለምናመጣው ተፈጥሮኣዊ ለውጥ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

07 September 2018, 17:50