A Fiumicino attivi E-gate anche per passeggeri canadesi A Fiumicino attivi E-gate anche per passeggeri canadesi  

አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሰው ልጅ ሕይወት ትኩረትን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።

የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የቱሪዝም አገልግሎት ሃላፊነት ባለው ዘላቂ ልማት ላይ በመመስረት ለዘርፉ እድገት የቆሙ መሆን ያስፈልጋል። የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰዎችን አጠቃላይ ማሕበራዊ ሕይወት ግንዛቤ በማስተባበር፣ ጥበብ በተሞላበት መንገድ ሚዛናዊነትን የጠበቀ መሆን ያስፈልጋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በመጭው መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ. ም. “ቱሪዝምና የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት” በሚል መርህ ቃል የሚከበረው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በቀዳሚነት ለሰው ልጅ ሕይወት ትኩረትን እንዲያደርጉ ያስፈልጋል።   

ምክንያት በማድረግ፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ኮዱዎ ታርክሰን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በቀዳሚነት ለሰው ልጅ ሕይወት ትኩረት እንዲያደርጉ አሳሰቡ። የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የቱሪዝም አገልግሎት ሃላፊነት ባለው ዘላቂ ልማት ላይ በመመስረት ለዘርፉ እድገት የቆሙ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል። ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን በማከልም የቴክኖሎጂ ውጤቶችም የሰዎችን አጠቃላይ ማሕበራዊ ሕይወት ግንዛቤ በማስተባበር ጥበብ በተሞላ መንገድ ሚዛናዊነትን የጠበቀ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘላቂ የቱሪዝም አገልግሎት በርትቶ መሥራት፤

የቱሪዝም ዘርፍ ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ መምጣቱ ሲነገር ያለፈው ዓመት መረጃ እንደሚያመላክተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ 70 በመቶ ማደጉን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ታርክሰን፣ የቱሪዝም አገልግሎት በስፋት በሚቀርብባቸው አገሮች ውስጥ አንዳንድ አሉታዊ ገጽታዎች ቢታዩም በዘርፉ የሚታየው እድገት ዘላቂነት ያለው መሆን አለበት ብለዋል።

የጋራ ሃላፊነት እውቀትን ማሳደግ፤

የመጨረሻዎቹ መረጃዎች እንደሚያስረዱት ከሃገር ጎብኚዎች 50 ከመቶ የሚሆኑ የጉዞ መረጃን የሚያገኙት በኢንተርኔት ላይ ከሚታዩ ምስሎች እና አስተያየቶች እንደሆነ፣ 70 ከመቶ የሚሆኑት ለመጓዝ ከመወሰናቸው በፊት ከኢንተርኔት ላይ ከሚያገኙት ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እና የሌሎች ሰዎች ልምድ እና አስተያየት እንደ መረጃ እንደሚጠቀሙ ታውቋል። በዚህ መልኩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለቱሪዝም አገልግሎት እድገት ሰፊ አስተዋጾን ከማበርከት በተጨማሪ፣ የጋራ መኖሪያ የሆነችውን ምድር ለመጠበቅ፣ ብክነትን ለማስቀረት፣ መልሶ የመጠቀም ባሕልን ለማዳበር የጋራ ሃላፊነት እውቀትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን አሳስበዋል።

የግል መረጃዎች አጠባበቅ፤

ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን አንዳንድ ሰብዓዊ ክብርን የሚጋፉ ለምሳሌ የሌሎችን የግል መረጃ ያለ አግባብ መጠቀም ስህተትን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በዲጂታሉ ዓለም ገብተው የሚሰሩት ግለ ሰቦች የሌሎች ሰዎች የግል መረጃዎችን ወስደው በማባዛት ገንዘብ ነክ፣ ቅስቀሳን በመሳሰሉ ሕገ ወጥ ተግባር እንደሚያዉሏቸው ገልጸዋል። ይህ ተግባር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር ገልጸው እያንዳንዱ ሰው ዲጂታል ቴክኖሎጂን የመጠቀም መብቱ እና ሰብዓዊ ክብሩ የተጠበቀ መሆን እንዳለበት አሳስበው የዚህ ዓለማ መጨረሻ ግቡ የቱሪዝም ዘርፍን ወይም አገልግሎትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ መመስረት ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጅዎችን በአግባቡ መጠቀምን በተለይም በቴክኖሎጂው የሚጠቀሙት ግለ ሰቦችና ሕብረተሰብ ደህንነት ዘላቂ እድገትን ያማከለ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል።

የባሕርይ ልዩነት መፈጠር የለበትም፤

የዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት የሚጠቀመውን የወጣት ማህበረሰብ ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ታርክሰን፣ የወጣቶችን ጉዳይ በስፋት እንደሚመለከት ተስፋ የተጣለበት የመላው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ 15ኛው ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚካሄድ አስታውሰው፣ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር ባላቸውን ግኑኝነት ሃላፊነትን በመውሰድ ወጣቶች ትልቅ ሚናን መጫወት እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በወጣቶች ዘንድ ማንነታቸውን የሚያሳጣና በማሕበራዊ ኑሮ መካከል የባሕርይ ለውጥን የሚያስከትል መሆን እንደሌለበት አሳስበዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጠሩት 15ኛው የመላው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ፣ የወጣቶችን ጉዳዮች አስመልክቶ ግልጽ ውይይት ለማድረግ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

08 August 2018, 16:18