ፈልግ

ካርዲናል ፓሮሊን ካርዲናል ፓሮሊን 

ካርዲናል ፓሮሊን፡ “ምድራችን ከመውደሟ በፊት የሚመለከታቸው አካላት በሕብረት መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል”

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በአሁኑ ወቅት በሮም በመካሄድ ላይ ባለው ዓለቀፍ ጉባሄ ተሳታፊዎች እንደ ገለጹት “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እና የወደፊቱ የምድር ላይ ሕይወት” በተመለከተ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሥነ ምሕዳርን በተመለከተ ተያያዥነት ባለው መልኩ የሚያቀርቡት ሐስባ ሊመስገን የሚግባ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን፡ “ምድራችን ከመውደሟ በፊት የሚመለከታቸው አካላት በሕብረት መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል”።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በአሁኑ ወቅት በሮም በመካሄድ ላይ ባለው ዓለቀፍ ጉባሄ ተሳታፊዎች እንደ ገለጹት “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እና የወደፊቱ የምድር ላይ ሕይወት” በተመለከተ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሥነ ምሕዳርን በተመለከተ ተያያዥነት ባለው መልኩ የሚያቀርቡት ሐስባ ሊመስገን የሚግባ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ይህንን የተናገሩት ከሰኔ 26/2010 ዓ.ም ጀምሮ በሮም “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እና የወደ ፊቱን የምድር ላይ ሕይወት” እንከባከብ በሚል አርእስት በመካሄድ ላይ ባለው ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ ዓለማቀፍ ጉባሄ እየታካሄደ የሚገኘው  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “Laudato si”  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁትን ሐዋሪያው መልእክት ሦስተኛ ዓመት የተዘከረበትን አጋጣሚ ተጠቅመው በቅድስት መንበር ሥር በሚተዳደረው የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ባዘጋጀው ጉባሄ ላይ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” የሚለው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሐዋሪያዊ መልእክት የጋራ መኖሪያ የሆነችውን ምድራችንን ከብክለት እንከላከል የሚል ሐሳብ ያነገበ ሐዋሪያዊ መላክት እንደ ሆነ ይታወሳል።

በእዚሁ ውዳሴ ላንተ ይሁን የሚለው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ ይፋ ባደረጉት ሐዋሪያዊ መልእክት ላይ ተመርኩዘው በወቅቱ በጉባሄው ላይ ንግግር ያደርጉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን እንደ ገለጹት ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋሪያዊ መልእክት በመላው ዓለም በመሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ስይንሲስቶችን ባካተተ መልኩ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጸው ይህ የሆነበት ምክንያት ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት ሁሉም ነገሮች ተያያዥነት እንዳላቸው አድርጎ በማቅረቡ የተነሳ እንደ ሆነ ካርዲናል ፔትሮ ጳሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ቫቲካን ስነ-ምዕዳርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ጉባሄ አስናዳች

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተቀናጀ ስነ-ምዕዳርን፣ የጋራ መኖሪያችንን መንከባከብ ቀዳሚ የሆነ ስፍራ ሊሰጠው ይገባል፣ የሰው ልጆች እና ስነ-ምዕዳር ከፍተኛ የሆነ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ የተነሳ “ለሰብአዊው ቤተሰብ የማይነጣጠሉ ጉዳዮች መሆናቸውን”  በመግለጽ “ስለ ዓለም ተፈጥሮ ጥልቅ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖር በማድረግ ስለ ፍጥረት 'ወንጌል' በመናገራቸው የተነሳ ከፍተኛ አድናቆት እንዳልቸው ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ተያያዥነት ያለው የስነ-ምህዳር አቀራረብ

የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በንግግራቸው ጨምረው እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ውስጥ ተያያዥነት ያለው የስነ-ምህዳር አቀራረብ እንዳለ ለዓለም በግልጽ ማሳየታቸውን ገለጸው “ከእግዚኣብሔር እና ከባልንጀሮቻችን ጋር ያለን ግንኙነት በተመሳሳይ መልኩ እናት ከሆነች ምድራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሊያካትት እንደ ሚገባው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቁልጭ አድርገው ማሳየታቸውን ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚለው ሐዋሪያዊ መልእክታቸው በኀጢአት ምክንያት በሰው ልብ ውስጥ የሚፈጸመው አመፅ በተፈጥሮ ላይ በሚያስከትላቸው ችግሮች ላይ ተንጸባርቋል በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አመላክተው እንደ ነበረ የገለጹት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በአሁኑ ወቅት ባለው ዓለማችን በከፍተኛ መልኩ እየተንጸባረቀ ባለው ተጠቅመህ ጣል “use and throwway” በሚለው ባሕል የተነሳ “በተፈጥሮ ላይ ከፍተኝ ጉዳት ማደርሱ ምድራችንን ለከፍተኛ አደጋ መዳረጉዋን” በመገለጽ አጣዳፊ በሆነ መልኩ “የሰው ልጆችን የእድገት ሂደት አመጣጥን፣ ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ሁኔታዎችን የምናስተዳድርበት ሁኔታ እና የአኗኗር ዘይቤአችንን መለወጥ እንደ ሚገባን የሚያሳስቡ መሆናቸውን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አሳስበዋል።

የካቶሊክ ዶክትሪን (አስተምህሮ)

ስነ-ፍጥረትን በተመለከተ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያለው ግንዛቤ ዓለም እግዚአብሔር "ለፍጡራን ሁሉ የሰጠው ውድ ስጦታ እንደ ሆነ” አድጎ የሚያቀርብ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ካርዲናል ፓሮሊን “አጽናፈ ሰማይ "እግዚአብሔር ሆን ብሎ የፈጥረው ነው ነገር ሲሆን የሰው ልጅ ከእዚያ ቀጥሎ የተሳሰበ ነገር ሳይሆን ነገር ግን የሰው ልጅ “የአጽናፈ ሰማያት መሠረታዊ ክፍል” በመሆኑ የተነሳ በእግዚኣብሔር አምሳያ በመፈጠራችን የሰው ልጅ ዋነኛው ጥሪ እግዚኣብሔር የፈጠረውን ፍጥረት መንከባከብ ነው እንጂ በተፈጥሮ ላይ የበላይነትን ማንጸባቅ እና ምድርን ማውደም አይደለም ብለዋል።

እኛ ሁላችን ተጠያቂዎች ነን

በንግግራቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቅድስት መነበር ዋነ ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርእስት የዛሬ ሦስት ዓመት ይፋ ያደርጉትን ሐዋሪያዊ መልእክት በተመለከተ እንደ ተናገሩት ከእግዚኣብሔር፣ ከባልንጀራዎቻችን እና ከምድራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናክር እንደ ሚገባ ጠቅሰው ጥሪያችን እግዚኣብሔር የፈጠረውን መንከባከብ ነው፣ ኃላፊነታችን ደግሞ እግዚኣብሔር የሰጠንን ሥራ ማስፈጸም ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

05 July 2018, 13:22