ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ከሆስፒታል ለህዝቡ የመጀመርያውን ሰላምታ እና ቡራኬ አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከየካቲት 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሮም ከተማ በሚገኘው ጂሜሊ ተብሎ በሚታወቀው ሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ወር ከሁለት ሣማንት በላይ ቆይታ ማረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም በጂሜል ሆስፒታል በረንዳ ላይ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ታይተዋል። በቦታው ለተገኙ ሰዎች ሰላምታ ያቀረቡት ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ቡራኬያቸውን ሰጥዋል፣ ከታች ባለው አደባባይ ለተሰበሰቡት ወደ ሶስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሰላም ካሉ በኋላ ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ጂሜሊ ሆስፒታል መግቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ለተሰበሰቡ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ምእመናን “ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ!” በማለት ሰላምታ አቅርበው ነበር።

"ለሁሉም ሰው አመሰግናለሁ!" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በደከመ ድምፅ ተናግረዋል። በድምጽ ብቻ የታጀበ ሰላምታ እንዲያደርጉ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ሊቃነ ጳጳሳቱ ቃል ለመስማት ብቻ ሳይሆን መታየት ፈለጉ።

ከእዚያም ቅዱስነታቸው በሮም ከተማ በሚገኘው "ማሪያ ማጆሬ" በመባል በሚታወቀው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተሰየመው ባዚሊካ ተገኝተው ጸሎት ካደረጉ በኋላ በቫቲካን ወደ ሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ማቅናታቸው ተገልጿል።

 

23 Mar 2025, 16:14