ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ተስፋ በፈተና ጊዜ ያበረታናል ማለታቸው ተገለጸ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለ33ኛው የዓለም የህመምተኞች ቀን ባስተላለፉት መልእክት በሥቃይ ላይ ያሉትን እና ለሚንከባከቧቸው ሰዎች ጥልቅ ጥያቄዎች አቅርበዋል። “ሰውነታችን ለከባድና አቅምን በሚያዳክሙ ህመሞች ሲመታ ልንተገብረው የማንችለው ውድ ህክምና የሚያስፈልገን እንዴት ነው ጠንካራ መሆን የምንችለው? ከራሳችን መከራ በተጨማሪ የሚደግፉንን የምንወዳቸውን ዘመዶቻችንን ስናይ እኛን ለመርዳት አቅመ ቢስ ሆኖ ሲሰማን ጥንካሬን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?” ሲሉ ቅዱስነታቸው ጥያቄ አንስተዋል።
ምንም እንኳን እውነተኛ ተስፋ “አያሳፍርም” እና እንዲያውም “በፈተና ጊዜ ብርታት ይሰጠናል” ቢሆንም ይህ በራስ የመተማመን መንፈስ በእውነተኛ የመከራ ሁኔታዎች ውስጥ ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ከራሳችን የበለጠ ጥንካሬ እንደሚያስፈልገን እናስተውላለን። የእግዚአብሔር እርዳታ፣ ጸጋው፣ መሰጠቱ እና የመንፈሱ ስጦታ የሆነው ብርታት እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን በመቀጠል ምእመናንን እግዚአብሔር እየተሰቃዩ ካሉት ጋር የሚቀራረብባቸውን ሦስት ልዩ መንገዶች እንዲያስቡ ይጋብዛሉ፡- “መገናኘት፣ ስጦታ እና ማካፈል" እንደ ሆነም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
መገናኘት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢየሱስ 72ቱን ደቀ መዛሙርት ወደ ተልእኮ በላካቸው ጊዜ የታመሙትን “የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች” ማለትም “ሕሙማን ድክመታቸውን እንዲመለከቱ ለመርዳት…” በማለት እንዲነግሯቸው ጌታ እንደላካቸው ያስታውሳሉ።
ይህ ገጠመኝ፣ ለውጥ የሚያመጣ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል፣ “በህይወት ማዕበል መካከል የምንጣበቅበት ጠንካራ አለት፣ ይህ ልምድ… ብቻችንን እንዳልሆንን ስለሚያስተምር የበለጠ ጠንካራ እንድንሆን ያደርገናል ብለዋል።
ስጦታ
ይህም በመከራችን የእግዚአብሔርን ቅርበት እንደ ስጦታ እንድንለማመድ ይመራናል፣ በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ከምንም ነገር በላይ መከራ ተስፋ ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ እንድንገነዘብ ያደርገናል። ስለዚህም በመጀመሪያ ደረጃ ‘በእግዚአብሔር ታማኝነት በማመን’ ልንቀበለው እና ልናዳብረው የሚገባ ስጦታ ነው ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “በክርስቶስ ትንሳኤ ውስጥ ብቻ የራሳችን ህይወት እና እጣ ፈንታ በዘላለም አድማስ ውስጥ ቦታውን የሚያገኘው በክርስቶስ ትንሳኤ ውስጥ ብቻ ነው” ሲሉ አብራርተዋል። ከክርስቶስ የሚለየን ምንም ነገር የሌለበት “ታላቅ ተስፋ” “በሕይወት ውስጥ በሚያጋጥሙን ፈተናዎችና እንቅፋቶች ውስጥ መንገዳችንን እንድናይ የሚረዱን የእነዚያ ሁሉ ትናንሽ የብርሃን ጭላንጭሎች ምንጭ ነው” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ ረገድ የቀድሞ መሪ ቤኔዲክቶስ 16ኛን ጠቅሰዋል።
ማጋራት
በመጨረሻም፣ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በመከራ ቦታዎች በሚታየው በማካፈል ወደ እኛ ቅርብ ነው። "በህመምተኞች አልጋ ላይ ምን ያህል ጊዜ ተስፋ ማድረግን እንማራለን!" ያሉት ቅዱስነታቸው “በምን ያህል ጊዜ፣ ከሚሰቃዩ ሰዎች ጋር ባለን ቅርርብ፣ እምነት እንዲኖረን እንማራለን! የተቸገሩትን ስንከባከብ ስንት ጊዜ ፍቅር እናገኛለን!” ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በታካሚዎች፣ በሐኪሞች፣ ተንከባካቢዎች፣ ቤተሰብ እና ጓደኞች መካከል "የእነዚህን ጸጋ-የተሞሉ ግንኙነቶችን ውበት እና አስፈላጊነት እንዴት ማድነቅ እንደሚችሉ መማር" አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል። "እነዚህ ሁሉ ሊከበሩ የሚገባቸው የብርሃን ጨረሮች ናቸው፣ በጨለማው የመከራ ምሽት ውስጥ እንኳን ብርታትን ይሰጡናል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ጥልቅ የህይወት ትርጉምን፣ በፍቅር እና በመቀራረብ ያስተምሩናል ብለዋል።
በኢዮቤልዩ ውስጥ ጠቃሚ ሚና
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢዮቤልዩ "በተለይ ጠቃሚ" ድርሻ እንዳላቸው በማሳሰብ ለታመሙ እና ለሚሰቃዩ በልዩ ቃል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። "የእናንተ ጉዞ ለሁሉም ሰው የተስፋ ምልክት ነው፣ "የክብር መዝሙር፣ የተስፋ መዝሙር" ነው።
እናም ስለምስክርነታቸው፣ በቤተክርስቲያኗ ስም እና በራሳቸው ስም፣ ሁል ጊዜ በጸሎቱ ውስጥ መሆናቸውን እያረጋገጡ፣ እናም ሐዋርያዊ ቡራኬያቸው እንደ ማይለያቸው ገልጸዋል።
የዓለም የሕሙማን ቀን 2025
የአለም የሕሙማን ቀን በየዓመቱ የካቲት 11 ቀን የሚከበረው የሉርድ ቅድስት ድንግል ማርያም የስርዓተ አምልኮ መታሰቢያ ሲሆን በተለይም በየሶስት አመቱ በማርያም ቤተ መቅደስ የሚከበር በዓል ነው።
ሆኖም የኢዮቤልዩ ዓመትን በማስመልከት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም በተለምዶ የሚከበረውን ክብረ በዓል ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ጥሪ አቅርበዋል። የዓለም የሕሙማን ቀን መታሰቢያ እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም በማርያም ቤተ መቅደስ ይከበራል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ውሳኔ ሰኞ ማለዳ ላይ የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማት እና የወንጌል ስርጭትን ለማስተዋወቅ የሚሰራው የቫቲካን ጽኃፈት ቤት በታተመ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል። ለኢዮቤልዩ አመት የአለም የሕሙማን ቀን በሀገረ ስብከቱ ደረጃ እንደተለመደው እ.አ.አ የካቲት 11/2025 ዓ.ም መደበኛ በሆነ መልኩ እንደሚከበርም በመግለጫው ተመልክቷል። በተመሳሳይ ጊዜ ከሚያዝያ 5-6/2025 የተቀመጠውን የሕሙማን እና የጤና አጠባበቅ ሰራተኞች መጪውን ኢዮቤልዩ ሲያከብሩ፣ እና በሚያዝያ 28-29/2025 የአካል ጉዳተኞች ኢዮቤልዩ ሲከበር አብሮ እንደ ሚታሰብ ተገልጿል።