ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዓለም አቀፋዊ የጸሎት መረብ: ጸሎትና የምሕረት ሥራ የማይነጣጠሉ ናቸው አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በየወሩ የጳጳሱ የጸሎት ዓላማዎች ይታተማሉ። ለምሳሌ፣ ለጥር ወር 2025 ዓ.ም ይፋ የተደርገው የጸሎት ሐሳብ ዓላማው የትምህርት መብትን የተመለከተ ነው።
እ.ኤ.አ. ጥር 23 ቀን ማለዳ ላይ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፍ የጸሎት መረብ የልዑካን ቡድን - እነዚህን ወርሃዊ ዓላማዎች የማተም ኃላፊነት ያለው ድርጅት - ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቫቲካን ሐዋርያዊ ጽኃፈት ቤት ውስጥ ተገናኝተው መወያየታቸው ተገልጿል።
የሁለት እጥፍ የልብ ጉዞ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለአዲሱ የጸሎት ኔትወርክ ዳይሬክተር እና ለመላው አባላት ሰላምታ በመስጠት በቅርብ ጊዜ ዲሌክሲት ኖስ በቡድኑ በደስታ በመቀበላቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ደብዳቤው የድርጅቱን ሐዋርያት “መንፈሳዊነት ለማጎልበት ጠቃሚ ምግብ” ሊሰጥ እንደሚችል አስረድተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ “የልብ መንገድ” የሚለውን ሐዋርያዊ መልእክት እንዴት እንደሚጠራው በሁለት ዓይነት ትርጉም አንፀባርቀዋል። የመጀመሪያው “በሥጋ የመገለጡ፣ ሕማማቱ፣ ሞትና ትንሳኤው ምስጢር የሆነው የኢየሱስ፣ የቅዱስ ልቡ ጉዞ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ “በኃጢአት የቆሰልን፣ በፍቅር ለመሸነፍ እና ለመለወጥ የሚፈቅደውን” የራሳችን የልባችን ጉዞ ነው ብለዋል።
ማርያም መሪያችን
በሁለቱም ጉዞዎች ላይ ጳጳሱ ማርያም ትመራናለች፣ ምክንያቱም በዚህ የእምነት እና የተስፋ ጉዞ ከፊታችን ሄዳለች። የሉቃስ ወንጌል ማርያም “በልቧ እያሰላሰሰች ያሉትን የኢየሱስን ቃላትና ድርጊቶች ሁሉ ትጠብቃለች” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማርያም እያንዳንዳችን ተመሳሳይ ነገር እንድናደርግ እንዴት እንደምታስተምር ጠቁመዋል።
ኢዮቤልዩ እና ጸሎት
በኢዮቤልዩ አመት እና እ.አ.አ ከጥር 24-26/2025 ዓ.ም ለሚካሄደው ልዩ የኢዮቤልዩ የመግቢያ መሰረት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የአለም አቀፍ የጸሎት ኔትወርክ ትልቅ ሚና እንዳለው አሳስበዋል። የእነርሱ ስራ ሁሉንም ሰው ለመርዳት ነው - ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች - ኢዮቤልዩ "ጸሎት እና ርኅራኄ፣ ጸሎት እና ከመካከላችን ዝቅተኛ ከሆነው ጋር መቀራረብ፣ ጸሎት እና የምሕረት ሥራዎች የማይነጣጠሉ የተጣመሩበት ጉዞ ናቸው" ብለዋል።