ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው የኮንራድ ሂልተን ድርጅት (ፋውንዴሽን) ቦርድ ባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው የኮንራድ ሂልተን ድርጅት (ፋውንዴሽን) ቦርድ ባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ‘ቤተ ክርስቲያን ድሆችን ለማገልገል ገዳማዊያት ያስፈልጋታል’ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው የኮንራድ ሂልተን ድርጅት (ፋውንዴሽን) ቦርድ ባላትን ባነጋገሩበት ወቅት ለድሆች የሚያደርጉትን ያላሰለሰ ጥረት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ድርጅቱ ሴት ገዳማዊያን ለማብቃት እና ለመደገፍ የምያደርገውን ጥረት አወድሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ዕለት ጥር 14/2017 ዓ.ም የሂልተን ፋውንዴሽን ድሆችን እና የተቸገሩትን በማገልገል ላይ ስላለው ተግባር እና ሴት ገዳማዊያንን በማብቃት እና ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚታየውን ሴቶችን የማያሳትፍ አስተሳሰብ እንዲያሸንፍ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አመስግነዋል።

የተቸገሩ ሰዎችን ሕይወት ማሻሻል

እ.ኤ.አ. በ1944 በታዋቂው የሆቴል ባለቤት ኮንራድ ሒልተን የተመሰረተው ፋውንዴሽኑ በዓለም ዙሪያ በእርዳታ፣ በአጋርነት እና በጥብቅና በመደገፍ የተቸገሩ እና አቅመ ደካሞችን ህይወት ማሻሻል ላይ ያተኩራል።

ፋውንዴሽኑ እንደ ቤት እጦት፣ ሱስ፣ ትምህርት፣ በልጅነት ወቅት የሚከሰቱ የእድገት ችግሮችን፣ ስደት እና የአለም ጤና ያሉ ጉዳዮችን የሚፈታ ሲሆን በተፈጥሮ አደጋዎች እና ሌሎች ቀውሶች ለተጎዱ ማህበረሰቦች ድጋፍ ይሰጣል።

በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ሴት ደናግላንን ማብቃት፣ የሴቶችን ሃይማኖታዊ ተፅእኖ በትምህርት እና በሌሎች ተነሳሽነት በማጠናከር ይደግፋል። ከነዚህም መካከል ከቫቲካን የኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር የተስፋፋው የእህትማማች ፕሮጀክት ተነሳሽነት ይገኝበታል።

"ርህራሄ" ወደ ሌሎች ስቃይ መቅረብ ማለት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባላት በጥር 14/2017 ዓ.ም ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በኋላ ለአባላቱ ሰላምታ አያቀረቡ ሲሆን ድህነት እና መገለል በሚቀጥልበት ዓለም ውስጥ በጣም የተቸገሩትን ሰዎች ሰብአዊ ክብር ለማስተዋወቅ ያላቸውን “ስሜታዊ እና ርህሩህ” ቁርጠኝነት አወድሰዋል።

ሥራቸውን ከደጉ ሳምራዊ ምሳሌ ጋር በማነፃፀር አንድን ሰው ለመናቅ ተቀባይነት ያለው ብቸኛው ምክንያት እንዲነሱ መርዳት እንደሆነ በማሳሰብ ይህንን መርህ በተልዕኳቸው ላይ እንዲያደርጉ አሳስቧቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም የፋውንዴሽኑ አባላት "የርኅራኄን" ምንነት እንዳትዘነጉ ሲሉ አበረታቷቸዋል፣ - "ርኅራኄ" ሲሉ "አይን ውስጥ ሳያዩ ሳንቲም ወደ ሌላው እጅ  ላይ መጣል ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር መቀራረብ እና መከራ መጋራት ማለት ነው" ብለዋል።

ሴት ገዳማዊያንን በመረጃ ማብቃት

የንግግሩ ጉልህ ክፍል ፋውንዴሽኑ ለሴት ገዳማዊያን ተከታዮች፣ ወጣት እህቶችን በመረጃ ማብቃት እና አረጋውያን መነኮሳትን በመንከባከብ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ያተኮረ ነበር። በኮንራድ ሒልተን በጣም የተከበረ ምክንያት ነው። ፋውንዴሽኑ ከቫቲካን ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር የመነኮሳትን ሙያዊ ብቃትና ተደራሽነት በማስታወስ፣ ቤተ ክርስቲያን መነኮሳትን በማስተማርና በማሠልጠን ወሳኝ ተልእኮአቸውን እንዲጎለብት አስቸኳይ ፍላጐት እንዳላቸው አመልክተዋል።

ሴት ገዳማዊያን የተጠሩት ድሆችን እንዲያገለግሉ እንጂ እነርሱን ሊገለገሉባቸው አይደለም።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ሴት ገዳማዊያን እና መነኮሳት “ሁለተኛ ደረጃ” ዜጋ ናቸው በሚል የተሳሳተ አመለካከት ላይ በመመሥረት ቤተክርስቲያን ከቀሳውስት ጋር ሲወዳደር ለእህቶች የሕነጻ አገልግሎት የምትመድበው ሀብት እጅግ ያነሰ እንደነበር ጠቁመዋል። “አሁንም እህቶች ቀጣይነት ያለው ትምህርት እና ስልጠና ማግኘት እንዲቀጥሉ አስፈላጊ ነው” ምክንያቱም “በድንበር አካባቢ እና በድሆች መካከል የሚሰሩት ስራ ስልጠና እና ብቃትን የሚጠይቅ ነው” ሲሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን ቤተክርስቲያኗን ወደ ውጭ በመውጣት እንድታገለግል  ላደረገው ድጋፍ ፋውንዴሽኑን አመስግነዋል።

“የእህቶች ተልእኮ ከመካከላችን ትንሹን ማገልገል ነው። የማንም አገልጋይ መሆን የለባቸውም። ይህ መቆም አለበት፣ እና እናንተ እንደ ፋውንዴሽን ቤተክርስቲያንን ከዚህ አስተሳሰብ ለማውጣት እየረዳችሁ ነው" ብለዋል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የካህናት የበላይነት አስተሳሰብ መለወጥ

ሆኖም በተመሳሳይ ጊዜ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ውስጥ ጨምሮ በርካታ ሴቶች በአመራርነት ሚና የተሾሙ ሴቶችን በውሳኔ ሰጭነት ቦታዎች ውስጥ በማካተት ረገድ እድገት አሳይተዋል። በቅርቡ የገዳማዊያንን/ገዳማዊያትን እና የሐዋርያዊ ሕይወት የሚመለከተው ጽሕፈት ቤት የበላይ ጠባቂ ሆነው መሾማቸውን እና በቅርቡም ሌላ መነኩሲት የቫቲካን ከተማ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን አስታውሰዋል።

"እግዚአብሔር ይመስገን መነኮሳት ወደፊት በመሄድ ላይ ናቸው እና ከሰው በተሻለ እንዴት እንደሚሠሩ ያውቃሉ። እንደዚያ ነው… ምክንያቱም ነገሮችን፣ ሴቶችን እና መነኮሳትን የማድረግ ችሎታ ስላላቸው ነው" ብለዋል።

ርህራሄ ፣ ቅርበት እና ሞቅ ያለ አቀራረብ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጠቃለያው የሒልተን ፋውንዴሽን ላደረገው “ያላሰለሰ አገልግሎት” አመስግነው “የተጣሉ፣ የተገለሉት በኅብረተሰቡ ውስጥ በጣም የሚያስፈልጋቸው የለውጥ ወኪሎች ሊሆኑ የሚችሉበት ዓለም የመኖር ሕልማቸውን ገልጸዋል፣ ርኅራኄ፣ መቀራረብና አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል። ርኅራሄ፣ ቅርበት እና ሞቅ ያለ አቀራረብ እነዚህ ሦስቱ የእግዚአብሔር ባሕርያት ናቸው ብለዋል።

23 Jan 2025, 14:59