ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አቶ አንድሪ ኒሪና ራጆኤሊና ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አቶ አንድሪ ኒሪና ራጆኤሊና ጋር በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አቶ አንድሪ ኒሪና ራጆኤሊና ጋር መገናኘታቸው የገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም በማዳጋስካር አድርገው የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዟቸውን አስታውሰዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሐሙስ ዕለት ነሐሴ 11/2015 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማዳጋስካር ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አቶ አንድሪ ኒሪና ራጆኤሊና ጋር ተገናኝተው ነበር። ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመራው የቅድስት መንበር መሥርያ ቤት ዋና ጸሐፊ ጋር ፕሬዝዳንቱ መገናኘታቸውም የተገለጸ ሲሆን በቅድስት መንበር እና ማዳጋስካር ያላቸውን መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ የማዳጋስካር ማህበረሰብ ክፍሎች የምታበረክተውን አስተዋፅዖ ጠቁመዋል።

ዓለም አቀፍ ጉዳዮች

የቅድስት መንበር ኅትመት ጽ/ቤት መግለጫ እንዳስታወቀው ውይይታቸው የተለያዩ አገራዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን ያቀፈ ነበር።

እነዚህም በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና ዓለም አቀፋዊ ውጤቶቹ እና በአፍሪካ አህጉር ላይ የተከሰቱ በርካታ ቀውሶች ይገኙበታል።

ከዚህም በላይ ሁለቱም ወገኖች “የሁለትዮሽ ስምምነትን በማዘጋጀት መቀጠል፣ የአክብሮት ትብብርን እንደ ተጨማሪ ምልክት” ያለውን አቅም መርምረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ማዳጋስካር ያደረጉት ጉብኝት ትውስታዎች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለ30 ደቂቃ በፈጀው ከፕሬዚዳንቱ ጋር ያደረጉት ቆይታ ሲያበቃ ጳጳሱ እ.አ.አ ከመስከረም 6-9/2019 ዓ.ም በማዳጋስካር አድርገውት ስለንበረው ሐዋርያዊ ጉዞ አንስተው ትውስታቸውን ተነጋግረዋል።  

18 Aug 2023, 10:41