ፈልግ

The Wider Image: Black mothers in the US speak of challenges and resilience

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያልተወለደውን በሳይንስ ድምፅ እንስማ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያንኛ ቋንቋ “የሕይወት ተአምር” በሚል አርዕስት በአርኖልዶ ሞስካ ሞንዳዶሪ፣ ከሳይንቲስት ጋብሪኤሌ ሴምፕሬቦን እና ከደራሲ ሉካ ክሪፓ ጋር በጋራ በመሆን በቅርቡ ይፋ ለሆነው መጽሐፍ የመግቢያ መቅድም መጻፋቸው ተገለጸ። የጣሊያን ኮሪየሬ ዴላ ሴራ የተሰኘው ጋዜጣ በህትመቱ ቅድመ እይታ ላይ እንደፃፈው መፅሐፉ ምንም አይነት የርዕዮተ ዓለም እንቅፋት ሳይኖር በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን  

የመጽሐፉ መግቢያ መቅድም ሙሉ ይዘቱ የሚከተለው ነው።

ይህ መጽሐፍ የእያንዳንዱ ሰው ወደ ዓለም መምጣት ያለውን አስደናቂነት እና ደስታ ለአንባቢው ለማስታወስ ያለመ ነው። ገና ያልተወለደ ህይወት የሁሉም ሰው የሆነው የነባሩ መብት ባለቤት አድርጎ የመመልከት ውበት ያሳያል። ውበት አዎ፣ ምክንያቱም የተፈጥሮ ትዕይንት ሂደት ሲወሰድ አስደናቂ ነገርን ስለሚያሰርጽ እንክብካቤ፣ ጥበቃ እና አቀባበል ይጠይቃል።

የዚህን መጽሐፍ ርዕሰ ጉዳይ በማንሳት ከሁሉም በላይ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሁሉም ሰዎች የፅንስ ማቋረጥን እውነታ ከአንድ ወይም ከሌላ እምነት ወይም የአስተሳሰብ ወግ ብቻ ጋር ሳይሆን በሳይንስ ብቁ የሆነ አስተዋፅኦ እንዲያንፀባርቁ እጋብዛለሁ።

ሰፋ ያለና ድንቅ የሆነ ብዙ ገጽታ ያለው ሰብአዊነታችንን የምጋራ ከወንድሞቼና ከእህቶቼ ጋር ውይይት ለማካሄድ ጽኑ ግን የተረጋጋ ጥሪ የሚያቀርብ ነው።

የዚህ መጽሐፍ ዋና ግብአት የሳይንቲስት፣ የፅንስ ጥናት ባለሙያ እና በተደባለቀ የስነ-ሕይወት ስነ-ምግባር (ባዮኤቲክስ) ኮሚቴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያለው (ማለትም ከዶክተሮች እና ከሳይንቲስቶች ጋር በሚደረግ ውይይት) ነው። ከሌሎቹ ደራሲዎች ጋር በመሆን የፅንሱን ድምጽ "በማዳመጥ" ወደ ፅንስ ማስወረድ ጭብጥ፣ ስለ ተፈጥሮው፣ ስለ እርሱ ወይም እርሷ ልዩ መሆን እንዴት እንደሚገጣጠሙ እንድንመለከት፣ ተፈጥሮ በዝግመተ ለውጥ ሺህ ዓመታት ውስጥ በጥሩ ሁኔታ በተስተካከሉ ሂደቶች በመመራት በእሱ እና በእራሳቸው መካከል የቆመ ስጋት መሆኑን እንዲያመለክት ያቀረብኩትን  ግብዣዬን ተቀብሏል።

"ወደ መወለድ ድንቅነት እንመለስ" ደራሲዎቹ ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ያልተወለደ ህይወት የሚያጋጥማቸውን ስጋት የማያቆሙ እና ለአሳዛኝ ሆኔታዎች ግልፅ መፍትሄ የማይሰጡ ፣ እንደ ፅንስ ማስወረድ ያሉ ፣ ግን ለተወለደ ህጻን እና ለእናትየው እርዳታ ሊሰጡ እንደሚችሉ ለሚሰማቸው ሁሉ ያቀረብኩትን ይግባኝ አድሳለሁ። ከሁሉም የበለጠ ተጋላጭ ከሆኑት ጀምሮ የሁሉንም ሰው ክብር ለመጠበቅ በመጨረሻ ኃላፊነት የተሰጠ ማህበረሰቡ ነው። ባጭሩ በየአካባቢው እና በየደረጃው ያለውን “የማባከን ባህል”ን መናቅ ያለበት ማሕበረሰቡ ነው። በማህፀን ውስጥ ያለ ልጅ ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉ ተግባራትን፣ የአረጋውያን በብቸኝነት መኖርን፣ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ብዙዎችን ድህነት ውስጥ የዘፈቀውን እና ሕዝቡ ከዋና ዋናዎቹ መሰረታዊ ነገሮች እና የእድገት ተስፋዎች እጥረት ውስጥ እንዲገባ ያደረገውን፣ በጦርነት ሰለባ የሆኑት ሰዎች ስቃይ እንዲያበቃ፣ በተስፋ መቁረጥ እና በስቃይ ምክንያት ለስደት የተዳረጉ ሕዝቦች ስቃይ እንዲያበቃ፣ በሁሉም የዓለም ክፍሎች ውስጥ ያለው ሥቃይ እንዲያበቃ ማድረግ የሚችለው ማሕበረሰቡ ራሱ ነው።  በብዙ ንፁሀን ተጎጂዎች ስም በዚህ "ተአምር" ህይወት ላይ በጋራ ለመወያየት እና ለማሰላሰል ፈቃደኛ የሆኑትን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ።

22 May 2023, 11:10