ፈልግ

ከሱዳን ግጭት የተሰደዱ ሰዎች ወደ ደቡብ ግብፅ ደረሱ ከሱዳን ግጭት የተሰደዱ ሰዎች ወደ ደቡብ ግብፅ ደረሱ  (ANSA)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ግጭትን እና ዓመፅን መላመድ የለብንም ማለታቸው ተገለጸ!

እሁድ እለት ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እና በማስከተለም “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እንደ ተናገረው ከሙታን ተንስቷ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ በኋላ ለአለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሱዳን ውስጥ በሁኑ ወቅት እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ያበቃ ዘንድ እየተደረጉ የሚገኙትን ውይይቶችን እንዲያበረታታ እና “ከተሰቃዩት” የዩክሬን ህዝብ ጎን መቆሙን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ እለት በሱዳን ውስጥ ያሉ ተፋላሚ ወገኖች መሳሪያቸውን እንዲያስቀምጡ ልባዊ ጥሪ አቅርበዋል ፣አለም አቀፉ ማህበረሰብ “ውይይት እንዲደረገ እና የህዝቡን ስቃይ ለመቅረፍ ማነኛውንም ሰላማዊ ጥረት እንዳያደርግ” ጥሪ አቅርበዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቀደም ሲል ለተደረጉት ከፊል ስምምነቶች ማበረታቻ ሰጥተዋል፣ ነገር ግን ከአንድ ወር ብጥብጥ በኋላ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል።

“እባካችሁ ግጭትና ብጥብጥ አንልመድ። ጦርነትን አንላመድ!” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተማጽነዋል።

ከእዚያም በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዩክሬን "የተሰቃዩ" ሰዎች ጎን መቆማቸውን እንዲቀጥሉ” ለሁሉም ጥሪ በማቅረብ ተማጽነዋል።

የዓለም የኮሚንኬሽን ቀን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እና በማስከተለም “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እንደ ተናገረው ከሙታን ተንስቷ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ በኋላ ለአለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በየአመቱ ከበዓለ ሃምሳ በፊት ባለው እሁድ የሚከበረውን የዓለም የኮምንኬሽን ቀን መከበሩን አስታውቀዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የዘንድሮው የአለም የኮምንኬሽን ቀን ጭብጥ በመጥቀስ “ለሁሉም ግልጽ እና ማሕበራዊ ግንኙነት እንድንፈጥር የሚያነሳሳን ልብ ነው” ስለዚህም በልባችን እንናገር በማለት ተናግሯል።

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አጋጣሚውን ተጠቅመው በአደባባዩ የሚገኙ የኮሙዩኒኬሽን ሠራተኞችን ሰላምታ ሰጥተው ለሠሩት ሥራ አመስግነው ምንጊዜም ለእውነትና ለጋራ ጥቅም የሚውል እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ የገለጹ ሲሆን "ግንኙነትን ለመክፈት እና ለመቀበል የሚያነሳሳን ልባችን ነው" ሲሉ አክለው ተናግሯል።

ላውዳቶ ሲ (ውዳሴ ላንተ ይሁን)ሳምንት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ “ላውዳቶ ሲ” (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) ሳምንት መጀመሩን በመጥቀስ ሳምንቱን ለማክበር ዝግጅቶችን እና ተግባራትን በማዘጋጀት ኃላፊነት የተሰጣቸውን አመስግነዋል። "የጋራ ቤታችን ለመንከባከብ ሁሉም ሰው እንዲተባበር እጋብዛለሁ" በማለት አክለውም የተናገሩ ሲሆን "ባለሙያዎችን እና የፈጠራ ክህሎቶችን አንድ ላይ ማምጣት በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉ ተናግሯል።

በተመሳሳይ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን አስታውሰው፣ በቅርቡ በጣሊያ ኤሚሊያ ሮማኛ ግዛት የተከሰተውን የጎርፍ መጥለቅለቅ ጨምሮ፣ በዝናብ ለተጎዱ ሰዎች ያለቸውን ቅርበትም በድጋሚ አፅንዖት ሰጥው ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል በቫቲካን የተቀናጀ  ሰብአዊ ልማት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ከስቶክሆልም የአከባቢ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን የላውዳቶ ሲ መጽሄቶችን ለሕዝቡ እንዲከፋፈል መደረጉን ተቁመዋል። ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን አጠናቅቀው በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን እና መንፈሳዊ ነጋዲያን ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

22 May 2023, 11:19