ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሆስፒታል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሆስፒታል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለሱ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከአጭር ጊዜ የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቫቲካን ተመለሱ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳንባቸው ላይ በደረሰ የጤና እክል ምክንያት ረቡዕ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው ጂሜሊ በመባል ወደ ሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መወሰዳቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዳሜ ጧት መጋቢት 23/2015 የጤና አቋማቸው ወደ ነበረበት ስለተመለሰ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ተነግሯል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቅዳሜ ጧት ከጂሜሊ ሆስፒታል የወጡ ሲሆን  ለብሮንካይትስ ሕመም የሚሆኑ የታቀዱ ምርመራዎች እና ሕክምናዎች ባደረጉት አጭር የሆስፒታል ቆይታ አድርገዋል።

 የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ቅዳሜ ማለዳ በሰጠው አጭር መግለጫ፣ ቅዱስ አባታችን ከመውጣታቸው በፊት የሆስፒታሉን አመራሮች፣ የቅድስት ልብ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ሊቀ መንበር ፍራንኮ አኔሊን ጨምሮ፣ የሆስፒታሉን አመራር ተቀብለው ሰላምታ ማድረጋቸውን አስታውቋል። የፖሊስ ክሊኒክ ዋና ዳይሬክተር ማርኮ ኤሌፋንቲ እና የሆስፒታሉ አጠቃላይ የቤተክህነት ረዳት ጳጳስ ክላውዲዮ ጁሊዮዶሪ፣ እንዲሁም የህክምና ቡድን እና የጤና አጠባበቅ ሰራተኞች በችግራቸው ወቅት የረዷቸውን ሰዎች በሙሉ አመስግነዋል።

በሮም ውስጥ ትልቁ ሆስፒታል የአጎስቲኖ ጂሜሊ ዩኒቨርሲቲ ፖሊክሊኒክ አንዱ ሲሆን ለካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት የሚያስተምር ሆስፒታል ነው። ሆስፒታሉ የተሰየመው ዶክተር እና የሥነ ልቦና ባለሙያ በነበሩት ፍራንቸስካዊ ካህን አጎስቲኖ ጂሜሊ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው መስራች እና የመጀመሪያ ዳይሬክተር እርሳቸው እንደ ነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ።

ከሆስፒታሉ ሲወጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሌሊት ሴት ልጃቸውን በሞት ያጡትን ጥንዶች ለማቀፍ እና ለመጸለይ ለአፍታ ቆም ብለው ለተሰበሰቡት ሰላምታ ለመስጠት መኪናቸውን ለአጭር ጊዜ አስቁመው የነበረ ሲሆን ከእዚያም በኋላ ወደ መንበራቸው ቫቲካን መመለሳቸው ተገልጿል።

Photogallery

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከአጭር ጊዜ የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቫቲካን ተመለሱ!
01 April 2023, 12:12