ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሮም በሚገኘው ጂሜሊ ሆስፒታል የሕፃናትን የካንሰር ክፍል ጎበኙ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሮም በሚገኘው ጂሜሊ ሆስፒታል የሕፃናትን የካንሰር ክፍል ጎበኙ ወቅት 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ናቸው፣ በሆስፒታል ውስጥ የሚገኙትን ሕጻናት ጎብኝተዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሳንባቸው ላይ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በሮም ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው ጂሜሊ በመባል ወደ ሚታወቀው ሆስፒታል ባልፈው ረቡዕ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም መወሰዳቸው  የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጤና ሁኔታቸው እየተሻሻለ በመምጣቱ ቅዳሜ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም  ከሆስፒታል እንደሚወጡ የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ገልጸው በነገው እለት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የሚከበረውን የሆሳህና በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚከናወነው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። አርብ ከሰአት በኋላ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ትንንሽ ሕጻናት ታካሚዎችን የጎበኙ ሲሆን በወቅቱ በሆስፒታል ውስጥ በመታከም ላይ የነበረ አንድ ሕጻን ልጅ ማጥመቃቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው አርብ የብሮንካይት ህክምና እየተከታተሉ ባሉበት የጂሜሊ ሆስፒታል በህክምና ላይ ከሚገኙ ህጻናት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ በሰጡት መግለጫ፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጂሜሊ ሆስፒታል የሕፃናት የካንሰር ሕክምና መስጫ ክፍል በሕክምና ላይ የሚገኙ ሕፃናትን ጎብኝተዋል።

መግለጫው “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መቁጠሪያዎችን፣ መጪውን የትንሳኤ በዓል የሚያመለክቱ በቸኮሌት የተሰሩ እንቁላሎችን እና ስለ ኢየሱስ ለልጆች የተዘጋጀ የጣሊያን መጽሐፍ ቅጂዎችን” መስጠታቸውን መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሆስፒታሉ ውስጥ በሕክምና ላይ የሚገኝ ሚጉዌል አንጅል የተባለ ትንሽ ልጅ በጠመቁበት ወቅት

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ በሰጡት መግለጫ በተጨማሪም ለግማሽ ሰዓት ያህል በቆየው ጉብኝታቸው ወቅት ጳጳሱ በሆስፒታሉ ውስጥ በሕክምና ላይ የሚገኝ ሚጉዌል አንጅል የተባለ ትንሽ ልጅ እንዳጠመቁ ተናግሯል።

ቅዱስነታቸው እሁድ እለት በሚካሄደው የሆሳህና ቅዳሴ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል

አርብ እለት የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ በሰጡት እንዳስታወቁት በነገው እለት ከሆስፒታል እንደሚወጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት እሑድ እለት በሚከበረው የጌታ ሕማማት በሚጀምርበት የሆሳህና በዓል መስዋእተ ቅዳሴ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

01 April 2023, 11:26