ፈልግ

Pope Francis hospitalised for a respiratory infection, in Rome

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ የጤና ሁኔታቸው እየተሻሻለ መምጣቱ ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በጤና እክል ምክንያት ታመው ወደ ሆስፒታል መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጤና ሁኔታቸው እየተሻሻለ በመምጣቱ ከሆስፒታል ሊወጡ እንደሚችሉ ተገለጸ። በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጤና ሁኔታ ላይ የተደረገ የህክምና መረጃ እንደሚያሳየው በአንቲባዮቲክስ መድኅኒቶች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው፣ በጤናቸው ላይ አዎንታዊ ምላሽ እየታየ ነው፣ እናም ከጥቂት ቀናት በኋላ ከሆስፒታል ሊወጡ ይችላሉ ተብሏል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ ሐሙስ መጋቢት 21/2023 እለት በሰጡት መግለጫ ርዕሰ ሊቃነ  ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከሰአት በኋላ በእረፍት፣ በጸሎት እና አንዳንድ ስራዎችን በማየት አሳልፈዋል ማለታቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እሮብ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በሮም ከተማ በሚገኘው ጂሜሊ በመባል ወደ ሚታወቀው ሆስፒታል መወሰዳቸው የሚታወቅ ሲሆን ሐኪሞች በብሮንካይት በሽታ መያዛቸውን በመጥቀስ  የአንቲባዮቲክ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ተናግረው ነበር።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ በመግለጫቸው ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በሆስፒታል ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ያገኟቸውን መረጃ በመጥቀስ እንዳስታወቁት ከታቀደው የሕክምና ምርመራ ውጤት በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብሮንካይት ቫይረስ በሽታ መያዛቸው ተረጋግጧል ያሉ ሲሆን በጤናቸው ላይም ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል ብለዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጤና እየተሻሻለ ነው።

እንደ የሕክምና ባለሙያዎች ገለጻ ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደ ሚወጡ ይጠበቃል።

አሁን በደረሰን ወቅታዊ ዜና መሰረት ደግሞ የቅዱስነታቸው የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየተሻሻለ በመምጣቱ በነገው እለት ከሆስፒታል እንደ ሚወጡ እና እ.አ.አ በሚቀጥለው እሁድ የሚከበረውን የሆሳህና በዓል መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚመሩ ይጠበቃል።

31 March 2023, 14:50