ፈልግ

በደቡብ ሱዳን ያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ወደ ሮም በተደርገው የአውሮፕላን በረራ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ ሱዳን ያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ወደ ሮም በተደርገው የአውሮፕላን በረራ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ‘መላው ዓለም በጦርነት እና ራስን በማጥፋት ላይ ይገኛል’ ማለታቸው ተገለጸ!

በደቡብ ሱዳን ያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ወደ ሮም በተደርገው የአውሮፕላን በረራ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ እና የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ጉባሄ መሪ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"አለም ሁሉ በጦርነት እና ራስን በማጥፋት ላይ ነው በጊዜ ጦርነቶችን ሁሉ ማቆም አለብን!" ሲሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከደቡብ ሱዳን ወደ ሮም የመልስ በረራ ላይ ከጳጳሱ ጋር አውሮፕላን ተሳፍረው ለነበሩት ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ታንግረዋል። ከካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ጀስቲን ዌልቢ እና ኢየን ግሪንሺልድስ፣ የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ጉባኤ ኃላፊ ጋር በጋራ በመሆን ነበር መግለጫውን የሰጡት።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቀረበው የመጀሪያው ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ለመጎብኘት ጓጉው ነበር... እሁን ደግሞ ደስታውን አይተዋል... በ2016 ዓ.ም በቅድስት መንበር እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በትምህርትና በጤና ጉዳዮች መካከል የተፈረመውን ስምምነት አስፈላጊነት እንዴት የመለከቱታል?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሲመልሱ

እኔ ያንን ስምምነት በደንብ አላውቀውም፥ ነገር ግን የቫቲካን ሴክሬታሪያት በእዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሊሰጥ ይችላል። በቅርብ ጊዜ የቧንቧ ዝርጋታን በተመለከተ ስምምነት መኖሩን አውቃለሁ፣ ነገር ግን ለዚያ መልስ መስጠት አልቻልኩም። በመንገድ ላይ ባለው እና በአዲሱ ስምምነት መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን አላውቅም። እነዚህ ጉዳዮች የሚስተናገዱት ቫቲካን ከውጭ አገሮች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚከታተለው ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፖል ጋላገር ነው፣ እናም ሁሉንም የሚጠቅሙ ስምምነቶችን በማድረግ ረገድ ጥሩ ናቸው። በዲሞክራቲክ ኮንጎ ወደ ፊት የመሄድ ታላቅ ፍላጎት እና ብዙ ባህል አየሁ። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት፣ ከጥቂት ወራት በፊት በጣም አስተዋይ ከሆኑ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በበይነ መረብ አማካይነት በቪዲዮ የተደረገ ስብሰባ አድርገን ነበር። የላቀ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሏቸው - ይህ ከሀብቶቻችሁ አንዱ ነው፣ በሮችን ከመዝጋት ይልቅ ለአስተዋይ ወጣቶች ቦታ ለእነሱ መሰጠት አለበት። ሰዎች ወደ ኮንጎ መጥተው እንዲበዘብዙ የሚስቡ ብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች አሏቸው - ስለ ቃሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ- ይህን የሚያስቡ ሰዎች አሉ፣  'አፍሪካ መበዝበዝ አለባት' በማለት አንዳንዶች ያስባሉ - እውነት እንደሆነ አላውቅም - የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ከመሬት በላይ ነፃነት ሰጡ ይላሉ። ከመሬት በታች ግን ነፃነት የለም፡ ስለዚህ ወደ ማዕድናት ይመጣሉ ይዘርፋሉ። ነገር ግን አፍሪካ መበዝበዝ አለባት የሚለውን ሀሳብ ከአእምሯችን ማጥፋት አለብን። እናም ስለ ብዝበዛ ማውራት እኔን በጣም ይነካኛል፡ በምስራቅ ውስጥ ያሉ ችግሮች ያሠቃዩኛል። ከጦርነቱ ሰለባዎች፣ ከቆሰሉት አልፎ ተርፎም እጆቻቸው የተቆረጡ ሰዎች ጋር መገናኘት ቻልኩ። ታላቅ ሥቃይ ነበር እናም ሁሉም የተደርገው ሀብትን ለመንጠቅ ነበር። ይህ ምንም ጥሩ አይደለም። ጥሩ አይደለም። ኮንጎ ብዙ እድሎች አሏት በማለት መልሰዋል።

ለቅዱስነታቸው የቀረበው ሁለተኛው ጥያቄ

ጥያቄ በሁለቱም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለት ተልዕኮዎች ቢኖሩትም ሁከት ተስፋፍቷል። ብዙ ተስፋ የቆረጡ የአፍሪካ ሀገራት የአለም አቀፍ ህግን የማያከብሩ ሌሎች አገሮች ለደህንነት አጋሮቻቸው የመምረጥ ፈተና እየጨመሩ በመምጣታቸው እርስዎ እንዴት አዲስ የጣልቃ ገብነት ሞዴልን ለመምከር ሊረዱ ይችላሉ? እንደ ሩሲያ የግል ኩባንያዎች ለምሳሌ በሳሄል ክልል ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ዓይነት ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ? አመሰግናለሁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ

ሁከት የዕለት ተዕለት ጭብጥ ነው። በደቡብ ሱዳን አይተነዋል። አመጽ እንዴት እንደሚቀሰቀስ ማየት በጣም ያማል። አንደኛው ጉዳይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ነው። ሊቀ ጳጳስ ዌልቢም ስለዚህ ጉዳይ አንድ ነገር ተናግሯል። የጦር መሳሪያ ሽያጭ፡ ይህ በአለም ላይ ትልቁ መቅሰፍት ይመስለኛል። ንግዱ... የጦር መሳሪያ ሽያጭ። እነዚህን ጉዳዮች የተረዳ አንድ ሰው ለአንድ አመት መሳሪያ መሸጥ ቢቆም የአለም ረሃብ ያበቃል ብሎ ነገረኝ። እውነት መሆኑን አላውቅም። ዛሬ ግን ከፍተኛው የጦር መሳሪያ እየተሸጠ ይገኛል። እናም በታላላቅ ኃይሎች መካከል ብቻ አይደለም። ለእነዚህ ምስኪኖች እንኳን... ጦርነት ይዘራሉ። ጭካኔ ነው። ‘ወደ ጦርነት ሂዱ!’ ይሏቸዋል፤ የጦር መሣሪያም ይሰጧቸዋል። ምክንያቱም ከጀርባው መሬቱን፣ ማዕድኑን፣ ሀብቱን ለመበዝበዝ ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች አሉ። እውነት ነው ጎሰኝነት በአፍሪካ አይጠቅምም። አሁን በደቡብ ሱዳን እንዴት እንደሆነ አላውቅም። እዚያም ያለ ይመስለኛል። ነገር ግን በተለያዩ ጎሳዎች መካከል ውይይት መደረግ አለበት። ሙሉ ስታዲየም ውስጥ ኬንያ በነበርኩበት ጊዜ አስታውሳለሁ። ሁሉም ተነስቶ ጎሰኝነት፣ ጎሰኝነት የለም አሉ። ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው የድሮ ጠላትነት፣ የተለያዩ ባህሎች አሉ። ነገር ግን የጦር መሳሪያ በመሸጥ በጎሳዎች መካከል ግጭት መቀስቀስ እና ከዚያም የሁለቱንም ጎሳዎች ጦርነት መጠቀማችሁ እውነት ነው። ይህ ዲያብሎሳዊ ነው። ሌላ ቃል ማሰብ አልችልም። ይህ ማጥፋት፡ ፍጥረትን ማጥፋት፣ ሰውን ማጥፋት፣ ማኅበረሰብን ማጥፋት ነው። በደቡብ ሱዳንም ቢሆን ይከሰት እንደሆነ አላውቅም ነገር ግን በአንዳንድ አገሮች ይከሰታል፡ ወጣት ወንዶች የሚሊሺያ አባል እንዲሆኑ እና ከሌሎች ወጣት ወንዶች ልጆች ጋር እንዲጣሉ ይደረጋል። ለማጠቃለል ትልቁ ችግር የዚያን ሀገር ሃብት - ኮልታን፣ ሊቲየም፣ እነዚህን መሰል ነገሮች ለመውሰድ ያለው ጉጉት እና በጦርነት መሳሪያ የሚሸጡበት፣ ህፃናትንም የሚበዘብዙ ይመስለኛል።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቀረበው ሦስተኛው ጥያቄ የሚከተለው ነበር

ጥያቄ፣ ሊቀ ጳጳስ ዌልቢ እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም በደቡብ ሱዳን መሪዎች ፊት ተንበርክከው ሰላም እንዲሰፍን መጠየቆን የሚገልጽ አስደናቂ ጊዜ አስታውሰው ስለነበር ቅዱስ አባታችን ስለዚህ ጉዳይ ልጠይቆት ፈልጌ ነበር። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ከሁለት ሳምንታት በኋላ፣ በዩክሬን ውስጥ ያለው ሌላ አስከፊ ግጭት የመጀመሪያ አመት ይሆናል፣ እናም የእኔ ጥያቄ፡- እነሱን የመገናኘት እድል ካላችሁ ለቭላድሚር ፑቲን ተመሳሳይ ምልክት ለመላክ ዝግጁ ትሆናላችሁን? እስካሁን ያቀረባችሁት የሰላም ጥሪ ጆሮ ዳባ ልብስ በመባሉ ተስፋ ቆርጣችኸልን? እናም ሁላችሁንም ልጠይቃችሁ በዩክሬን ሰላም እንዲመጣ በጋራ ይግባኝ ማለት ትፈልጋላችሁ?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ

ከሁለቱም ፕሬዚዳንቶች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ: ከዩክሬን ፕሬዚዳንት እና ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ጋር ማለት ነው- ለስብሰባ ዝግጁ ነኝ። ወደ ኪየቭ ያልሄድኩት ወደ ሞስኮ ለመሄድ በወቅቱ የማይቻል ስለሆነ ነበር፣ እኔ ግን ውይይት ላይ ነበርኩ። እንደውም ጦርነቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ወደ ሩሲያ ኤምባሲ ሄጄ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ወደ ሞስኮ መሄድ እንደምፈልግ ለመነጋገር ጥያቄ አቅርቤ ነበር። ከዚያም ሚኒስትር ላቭሮቭ ይህን እያጤኑበት ነው ብለው መለሱ፣ ነገር ግን (እንዲህ አለ)፣ ‘በኋላ ላይ ጉዳዩን እናየዋለን’ ሲሉ መለሱ። ይህ ምልክት ‘እኔ እያደረኩት ነው’ ብዬ ያሰብኩት ነገር ነበር። ነገር ግን እ.አ.አ የ 2019 የስብሰባ ምልክት እንዴት እንደተከሰተ አላውቅም፣ አልታሰበም ነበር እና ያልታሰቡትን ነገሮች መድገም አትችልም - ወደዚያ የሚወስድህ መንፈስ ነው። ለማብራራት የማይቻል ነው።  

ዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል ግን ጦርነት ብቻ አይደለም። ፍትህን ማድረግ እፈልጋለሁ [በአለም ላይ ለሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ ማለት ነው]: ከአስራ ሁለት እስከ አስራ ሶስት አመታት ያህል ሶሪያ በጦርነት ላይ ነች፣ ከአስር አመታት በላይ የመን ጦርነት ላይ ነች፤ ምያንማርን አስቡ፣ ከትውልድ አገራቸው ስለተፈናቀሉ በዓለም ዙሪያ የሚጓዙትን ምስኪን የሮሂንጊያ ተወላጆችን እናስብ። በሁሉም ቦታ፣ በላቲን አሜሪካ... ስንት የጦር አውድማዎች አሉ! አዎን በሚፈጥሩት ድምጽ ምክንያት የበለጠ የሚያስፍሩ ጦርነቶች አሉ፣ ግን አላውቅም መላው ዓለም በጦርነት ላይ ነው እና እራስን በማጥፋት ላይ ይገኛል አለማችን። በቁም ነገር ማሰብ አለብን፡ እራስን በማጥፋት ላይ ነን። በጊዜ ማቆም አለብን ምክንያቱም አንድ ትልቅ ቦንብ ስናስፈነጥር ሌላ ትልቅ ቦንብ ደግሞ ወደ እኛ ይወረወራል። እናም የተረጋጋ አእምሮ ያስፈልገናል።

05 February 2023, 20:13