ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቤተክርስቲያን እናንተን ትፈልጋለች ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሦስተኛው ቀን ላይ በእዚያው ለሚገኙት ካህናት፣ ገዳማዊያን ገዳማዊያት፣ ዲያቆናት እና ለዘረዕ ክህነት ተማሪዎች ጭምር ባደረጉት ንግግር ክርስቶስን በሕይወታቸው ማእከል ላይ እንዲያስቀምጡ እና የቅዱስ ወንጌል ምስክሮች እንዲሆኑ አበረታተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በወቅቱ እመበኤታችን ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ዮሴፍ ኢየሱስን በሕጻንነቱ ወደ ቤተመቅደስ ወስደው ማቅረባቸው በሚታወስበት እና በተከበረበት በዓል አስምልከተው ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኮንጎ የኪኒሻሳ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል ውስጥ ለተገኙ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና እንዲሁም ከዘረዕ ክህነት ተማሪዎች ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል።

ቅዱስ አባታችን በስምዖን እና በሕፃኑ ክርስቶስ መካከል በበዓሉ ላይ ስለሚደረገው ግኑኝነት በማሰላሰል ትምህርት መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን “ኢየሱስን በሕይወታችን ማዕከል ስናስቀምጠው አመለካከታችን ይቀየራል፣ ጥረቶቻችንና ችግሮቻችን መና የሚሆኑ ቢመስልም ቅሉ በእምነት ጸንተን በምንጓዝበት ወቅት ሁሉ ሕይወታችን ሊቀየር ይቻላል ማለታቸው የገለጸ ሲሆን በብርሃኑ እንደተሸፈነን፣ በመንፈሱ እንደተጽናናን፣ በቃሉ መበረታታት እና በፍቅሩ እንደምንደገፍ ይሰማናል ብለዋል።

“ብዙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም” “በወንጌል አገልግሎት ታላቅ ደስታ” እንዳለ ሃይማኖታዊ ጥሪ ላላቸው ሰዎች አሳስቧቸዋል። ቀሳውስትና ገዳማዊያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት፣ ሕዝቡን ዛሬ “በመጽናናት እና በተስፋ ቅባት በመቀባት የእግዚአብሔር ፍቅር ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል ብለዋል።

የህዝብ አገልጋዮች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፣ ካህናት፣ ደናግላን፣ ሚስዮናውያን እና ሌሎች ለሃይማኖታዊ አገልግሎት የተጠሩ ለሌሎች ሰዎች አገልጋይ እንዲሆኑ ተጠርተዋል፣ “የክርስቶስን መገኘት፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ ፍቅሩ፣ የእሱ እርቅ እና ይቅርታ እና ርህራሄ ያለው አሳቢነት ለማሳየት ተጠርተዋል። የድሆች አባት እንደ ሆነ ለማስረዳት ተጠርተዋል ብለዋል።

ነገር ግን ይህ አገልግሎት ሁል ጊዜ ተግዳሮቶች እና ችግሮች የሚያጋጥሙት ሲሆን ይህም መንፈሳዊ ድርቀት፣ ዓለማዊ ምቾት እና ላይ ላዩን መኖርን ይጨምራል ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህን ተግዳሮቶች በይፋ በሚደረጉ ጸሎቶች ወይም በግል ጸሎት ማሸነፍ እንደሚቻል ተናግሯል። እራስን በመርሳት እና ህይወታችንን ለሌሎች በመስጠት "የተማሩ፣ በደንብ የሰለጠኑ እና ጥልቅ ስሜት ያላቸው" የወንጌል ምስክሮች በመሆን እነዚህን ተግዳሮቶች መወጣት እንደ ሚችላ አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው በመቀጠልም “ሰዎችን የአምላክ ፍቅር ምስክሮች አድርገን ማገልገል ከፈለግን እነዚህን ተግዳሮቶች መጋፈጥ አለብን” ሲሉ ተናግረዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ሲያጠናክሩ "ጥሩ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ገዳማዊያን ገዳማዊያት ለመሆን ቃላት እና አሳብ በቂ አይደሉም፡ ህይወቶቻችሁ ከቃላችሁ በላይ ይናገራልና፣ እናንተ ውድ እና አስፈላጊ ናችሁ!' ማለታቸውም ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ህዝብ ያጋጠሙትን ችግሮች በመገንዘብ የኢየሱስን ቀሳውስትና ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እንደ ደጉ ሳምራዊ ቆም ብለው የተጨቆኑ ሰዎች ቁስሎች እንዲያክሙ አሳስበዋል።

“ወንድሞችና እህቶች፣ የተጠራችሁበት አገልግሎት ይህ ነው” በማለት ሐሳባቸውን አጠናክረው የተናገሩት ቅዱስነታቸው “መቀራረብና ማጽናኛን ለመስጠት፣ በጨለማው መካከል እንደሚበራ ብርሃን ሁኑ” በማለት ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለካህናቱ፣ ለዲያቆናት፣ ለገዳማዊያን እና ገዳማዊያት እንዲሁም ለዘረዕ ክህነት ተማሪዎች ልባዊ ምስጋናቸውን ሲያቀርቡ “ስለምንፈልጋችሁ” ተስፋ እንዳይቆርጡ በማለት አሳስበዋል።

በቤተክርስቲያኗ ሁሉ ስም ሆነው ሲናገሩ፣ “አናንተ ውድ እና አስፈላጊ ናችሁ” ሲሉ ቅዱስነታቸው አጥብቀው ተናግሯል። እናም “ሁልጊዜ የጌታ የማጽናኛ መንገዶች፣ አስደሳች የወንጌል ምስክሮች፣ በዓመፅ ማዕበል መካከል የሰላም ነቢያት፣ የፍቅር ደቀ መዛሙርት፣ የድሆችንና የተስቃዩን ሰዎች ቁስል ለመንከባከብ ምንጊዜም ዝግጁ እንዲሆኑ” ከጋበዟቸው በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

02 February 2023, 14:29