ፈልግ

በቱርክ እና በሶሪያ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈተኛ ጉዳት አድርሷል በቱርክ እና በሶሪያ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈተኛ ጉዳት አድርሷል  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቱርክ እና በሶሪያ በተከሰቱት ርዕደ መሬት በተጎዱ ሰዎች ማዘናቸውን ገለጹ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቱርክ እና በሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰው ህይወት ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ማዘናቸውን የገለጹ ሲሆን እርሳቸው በጸሎታቸው ከእነርሱ ጋር እንደ ሆኑ ለእየአገራቱ በላኩት የቴሌግራም መልእክት ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መግለጻቸው ተነግሯል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በደቡብ ምስራቅ ቱርክ እና በሰሜን ምእራብ ሶሪያ በደረሰው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የሰው ህይወት መጥፋቱን በመስማታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ተናግረዋል ።

በርዕደ መሬት መለኪያ መሳሪያ በሬክተር እስኬል 7.8 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የጎረቤት ሀገራትን ሰፈሮች ሰኞ ማለዳ በመናጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎችን አውድሟል እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ አሁንም በፍርስራሹ ውስጥ ተይዘው ይገኛሉ ተብሎ የሚታመን ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች በአካባቢው በሚገኙ ከተሞች እና መንደሮች ከፍተኛ ፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት የተረፉትን ሲፈልጉ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለሞቱት ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ የምሕረት እጅ ላይ በአደራ አስቀምጣለሁ” እናም “ለሞቱት ያዘኑትን ከልብ የመነጨ ሐዘናቸውን” መግለጻቸው ተነግሯል።

በተመሳሳይም “የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና በጎ አድራጊዎች በሚፈጽሟቸው በጎ ተግባራት ምስጋና እና ጸሎት ያስፈልጋቸዋል፣ እርዳታቸውን እንዲቀጥሉ ጸሎት ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥል” ሲሉ ቅዱስነታቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ቢያንስ 2,800 ህንፃዎች ፈርሰዋል። ይባስ ብሎ፣ ሰኞ ምሳ ሰዓት ላይ በደቡብ ምስራቅ ቱርክ ሁለተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ከፍተኛ አደጋ ማስከተሉንም አክለው ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶሪያ ባለስልጣናት መንግስት በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች ቢያንስ 320 ሰዎች መገደላቸውን የገለጹ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ደግሞ ቢያንስ 100 ሰዎች በአማፅያን ቁጥጥር ስር ባሉ ወረዳዎች መሞታቸውን ተናግረዋል ።

የአውሮፓ ህብረት ከብሪታንያ፣ ከእስራኤል፣ ከስዊድን፣ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ቃል ከተገባላቸው እርዳታ ጋር የነፍስ አድን ቡድኖችን ወደ አካባቢው እየላከ ነው። ጎረቤት ግሪክም ሀብቷን በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች።

08 Feb 2023, 16:13