ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ በሁለተኛው ቀን ያከናወኗቸው አበይት ተግባራት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ በማድረግ ላይ ባሉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በሁለተኛው ቀን የመስዋዕተ ቅዳሴን ጸሎት አቅርበው በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል የአመፅ ሰለባ ከሆኑት ሰዎች የቀረቡ አሰቃቂ ምስክርነቶችን ሰምተው፣ ለሕይወት አስጊ በሆነ ተልዕኮ ላይ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አባላት ብርታትን ተመኝተውላቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

"አደጋ በበዛበት ምሥራቃዊ የአገሪቱ ክፍል እንኳ ቢሆን ሰላምን ማምጣት ይቻላል!” ብለው ይህን በማመን በሌሎች ሳንሸነፍ መሥራት አለብን ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ይህን የተናገሩት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል ለመጡ በርካታ የአመፅ ሰለባዎች እንደሆነ ታውቋል። በሁለተኛው የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ቀን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ምዕመናን ባቀረቡት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አባላት ጋር ተገናኝቷል።

02 February 2023, 17:19