ፈልግ

2023.01.31 Viaggio Apostolico nella Repubblica Democratica del Congo e in Sud Sudan

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጦርነት እንዲቀጥል የሚያደርጉ ሁሉ እግዚአብሔርን ክደዋል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጥር 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ 40ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በዲሞግራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ እና በደቡብስ ሱዳን በቅደም ተከተል ሐዋርያዊ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በሁለተኛው ምዕራፍ የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በደቡብ ሱዳን እንደሚገኙ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በደቡብ ሱዳን በጥር 27/2015 ዓ..ም ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በወቅቱ ከተለያዩ የክርስቲንያን እምነት ተከታይ ምዕመናን ጋር በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ለተሰበሰቡ ምእመና ንግግር ያደረጉ ሲሆን በሥፍራው የተገኙት ሁሉ እንዲጸልዩ፣ እንዲሠሩና እንዲጓዙ የጦር መሣሪያ የሚያንሱ ሁሉ እግዚአብሔርን ክደዋል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በደቡብ ሱዳን በሁለተኛው ቀን ቅዱስነታቸው በነበራቸው ቆይታ ማጠናቀቂው ላይ በጁባ በሚገኘው የጆን ጋራንግ መካነ መቃብር ሥፍራ አከባቢ ላይ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንስኮስ ለተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ማኅበረ ቅዱሳን ጸሎት ለተሰበሰቡ ምእመናን ንግግር አድርገዋል። ከደቡብ ሱዳን ምድር እየተከሰተ ባለው "በዓመፅ ከተመሰቃቀለ" ሕይወት ነፃ መውጣት እንችል ዘንድ "አሁን ብዙ ጸሎት ወደ ሰማይ ተደርገዋል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቦታው የተገኙት ሁሉ በሦስት ግሦች ላይ እንዲያስቡ ጠይቀዋል፡- የመጀመሪያው መጸለይ የሚለው ነበር።

መጸለይ

የመጀመሪያው መጸለይ የሚለው ነው። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጸሎት ወደ ፊት እንድንሄድ፣ ፍርሃታችንን ለማሸነፍ፣ በጨረፍታ ለመመልከት እንድናቆም፣ እግዚአብሔር አሁንም እያዘጋጀ ያለውን የመዳን ታሪክ በጨለማ ውስጥም ቢሆን ብርታት ይሰጠናል ብለዋል። አክለውም "ጸሎት የእግዚአብሔርን ማዳን በሰዎች ላይ ያወርዳል" እናም የምልጃ ጸሎት እኛ እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎች እረኞች በተለይ እንድንለማመድ የተጠራን የጸሎት አይነት ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባድረጉት ንግግር አጽኖት ሰጥተው እንደተናገሩት ከሆነ "ባለን የእምነት ልዩነት ውስጥ፣ እንደ አንድ ቤተሰብ፣ ለሁሉም ሰው የመጸለይ ኃላፊነት በመካከላችን አንድነት እንዲሰማን እናድርግ" ማለታቸው ተግለጿል።

መሥራት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ሥራ” በሚለው ግስ ላይ ተንተርሰው እንደ ተናገሩት ከሆነ የእግዚአብሔር ሰላም የሚመጣው በግጭቶች መካከል እርቅ ብቻ በመፍጠር ቢቻ ሳይሆን “ከመዋሃድ፣ ከይቅርታና ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮችን በማቻቻል፣ ከማስታረቅና ከአለመጫን የሚመጣ ወንድማዊ ኅብረት ነው” ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የኢየሱስ እና የአብ መንፈስ እንድንገነባ ለሚገፋፋን ሰላም፥ ልዩነትን የሚያቀናጅ እና በብሃነት አንድነትን የሚያጎለብት ሰላም እንዲኖረን ሳንታክት እንሥራ" ሲሉ አሳስበዋል።

“ክርስቶስን የሚመርጡ ሁል ጊዜ ሰላምን ይመርጣሉ። ጦርነትንና ዓመፅን የሚከፍቱ ጌታን ከድተዋል ወንጌሉንም ክደዋል” በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም “ኢየሱስ የሚያስተምረን ነገር ግልጽ ነው፣ ሁሉም ሰው በሰማያት ያለው የጋራ አባታችን ልጅ አድርጎ ስለሚቆጥረን ሁሉንም መውደድ አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ ጉዞ

ሦስተኛው እና የመጨረሻው ግሥ "ወደ ጉዞ" የሚለው ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ አገር ውስጥ ማለትም በደቡብ ሱዳን "የክርስቲያን ማህበረሰቦች የማስታረቅ ሂደቶችን ለማራመድ በጥልቅ ቁርጠኛ ነበሩ" በማለት ምስጋናቸውን የገለጹ ሲሆን "ከእውነታው የተወለደ አንጸባራቂ የእምነት ምስክርነት በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም ይገለጻል፣ የትኛውም የታሪክ መለያየት አንድ የማይለወጥ እውነታ አለ እርሱም እኛ ክርስቲያኖች ነን ፣ ስለዚህ እርቅ እና ሰላም መፍጠር አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስለ ደቡብ ሱዳን የክርስቲያኖች ሕብረት ሲናገሩ ይህንን እውነታ “የከበረ ሀብት” እና የኢየሱስን ስም የማወደስ ተግባር ሲሉ ገልጸውታል። ቅዱስነታቸው አክለው እንደ ተናገሩት "በአማኞች መካከል ያለው የአንድነት ምስክርነት በአጠቃላይ ለህዝቡ ይፍሰስ" ሲሉ ተናግረዋል።

ትውስታ እና ቁርጠኝነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ ደቡብ ሱዳናውያን በጉዟቸው እንዲጸኑ የሚያበረቷቷቸው ሁለት የመጨረሻ ቃላትን አስተዋውቀዋል፡ ትውስታ እና ቁርጠኝነት።

ትዝታ ማለት "የምትወስዳቸው እርምጃዎች የቀደሙትን ሰዎች ፈለግ እንዲከተሉ ማድረግ ነው። ቁርጠኝነት ማለት ፍቅር ሲጨበጥ ወደ አንድነት መሄድ ማለት ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

04 February 2023, 22:06