ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለክርስቲያናዊ ሕብረት የሚሰራው የፊንላንድ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለክርስቲያናዊ ሕብረት የሚሰራው የፊንላንድ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አንድነትን ለማጎልበት ፈጽሞ አትታክቱ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለክርስቲያናዊ ሕብረት የሚሰራው የፊንላንድ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ለክርስቲያናዊ አንድነት እና ለዓለም እርቅ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከፊንላንድ ከመጡ የልዑካን ቡድን ጋር ሐሙስ ዕለት ጥር 11/2015 ዓም በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት በክርስቶስ የተጠመቁ ክርስቲያኖች በሙሉ የጋራ ጥሪውን ሙሉ በሙሉ በመምራት፣ ዕርቅን ለማስፈን ያለመታከት ለመሥራት እና በጦርነት ምክንያት እየተሰቃየች በምትገኘው ዓለማችን ውስጥ የእርቅ ወኪሎች የመሆን አስፈላጊነት አስመልክተው መናገራቸው ተገልጿል።

ቡድኑ ሮምን እየጎበኘ ያለው በፊንላንድ በሰማዕትነት የተገደለው የእንግሊዛዊው ተወላጅ ጳጳስ የቅዱስ ሄንሪክ በዓልን በማክበር በካቶሊኮች እና በሉተራውያን እንዲሁም በብዙ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እና የአንግሊካን ሕብረት ለማክበር በተዘጋጀው እና በእየአመቱ ለአንድ ሳምንት ያህል በሚከበረውና በክርስቲያን ሐይማኖት ተቋማት መካከል ያለው ሕብረት እንዲጠናከር በማሰብ በሚደርገው የአንድ ሳምንት ጸሎት ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ ነው።  

ከካቶሊክ እና ሉተራን አባላት ጋር፣ የልዑካን ቡድኑ የኦርቶዶክስ እና የሜቶዲስት ተወካዮችንም አካቷል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ንግግር የጀመሩት የፊንላንድ የክርስቲያን መሪዎች በቅርቡ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ሞት የተነሳ ልዑካኑ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ በማመስገን ነበር።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ ባለፈው በጥር 8/2023 ዓም የተከበረውን የኢየሱስን የጥምቀት በዓል በማስታወስ፣ የክርስቶስ የጋራ ጥምቀት በክርስቲያኖች መካከል እና በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ እርቅን እንድናበረታታ የሚጠይቅ መሆኑን ሊቀ ጳጳሱ በቦታው ለተገኙት ሁሉ አስታውሰዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል ...

“አንድ የሆነቺውን ጥምቀት ከተቀበልን በኋላ እኛ አማኞች ከሁሉ በላይ እንድናመሰግነው ተጠርተናል፣ ምክንያቱም ከጥምቀት ውሃ ጀምሮ ህልውናችን ከእግዚአብሔር፣ ከሌሎች ጋር እና ከፍጥረት ሁሉ ጋር የታረቀ ነው። የታረቁ ወንድና ሴት ልጆች በመካከላችን ለመታረቅ እና በዓለማችን ሳንታክት የእርቅ ወኪሎች እንድንሆን ተጠርተናል”።

 

የግፍ እና የጦርነት ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ትክክለኛ ቅርበት ማሳየት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለይ በዓለም ዙሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ለክርስቲያናዊ አንድነት የጸሎት ሳምንት እ.አ.አ ከጥር 18-25/2023 ዓም በሚያከብሩበት ወቅት በዚህ ዓመት “መልካምን ማድረግ ተማሩ፣ ፍትህን እሹ” (ኢሳ 1፡17) በሚል መሪ ቃል እየተዘከረ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል ...

“በእነዚህ ቃላት፣ በጸጋ ጸድቀን፣ የፍትህ ስራዎችን እንድንሰራ እና በፍትህ መጓደል፣ በመገለል እና በተለያዩ የጥቃት ሰለባዎች ላይ ተጨባጭ ምልክቶችን እንድንሰጥ የሚጠራን የጥምቀታችን ድምጽ ስያስተጋባ ሰምተናል። ጭቆና በተለይም ጦርነት ለማስቆም ተጠርተናል”።

ቅዱስነታቸው አክለውም “በክርስቶስ አማካይነት የእምነት ምስክሮች እንደመሆናችን መጠን፣ በሰውነታችን ደካማነት ውስጥ ራሱን የነከረ፣ በተቸገሩት ሁሉ ቁስሎች ውስጥ ራሳችንን የማስጠም ግዴታ አለብን። ይህንንም አንድ ላይ ለማድረግ እንነሳ” ማለታቸው ተገልጿል።

የቅዱስ ሄንሪክን ዳራ መከተል  

ቅዱስ ሄንሪክን እንደ “የእምነት ምስክር፣ የተስፋ መልእክተኛ እና የበጎ አድራጎት መሣሪያ” በማለት በማስታወስ፣ የምንጋራውን አንድነት ታላቅነት በመገንዘብ፣ በአንድነት መጸለይ እና መለያየትን ለማሸነፍ በትጋት መሥራት እና አንድ መሆን አስፈላጊ መሆኑን ጳጳሱ አበክረው አሳስበዋል። ዓለም ያምን ዘንድ" እኛ መተባበር እና አብሮ መሥራት ይኖርብናል ብሏል።

ይሁን እንጂ ይህንን እውነታ ማወቅ በቂ አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው “የክርስቶስን አካል አንድነት ከሚጎዳው በክርስቲያኖች መካከል በተፈጠረው የታሪክ መለያየት የተሰጠውን የፀረ-ምሥክርነት ቃል ለማሸነፍ ካለው ፍላጎት የሚመነጭ እውነተኛ ስሜትን ማዳበር አለብን” ያሉ ሲሆን ከምንም በላይ ዛሬ “ለወንጌል ሥራ ልባዊ ቅንዓት ያስፈልገናል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አበክረው ተናግረዋል።

ስለዚህ “ለመውደድ እና ተስፋ በማድረግ ሩቅ ያሉትን ለመፈለግ ፈጽሞ እንዳንታክት”  ያሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስን የመስበክና የሚፈለገውን አንድነት እንድንገነባ ልባዊ ፍላጎት እንድናዳብር” ጥሪያቸውን በድጋሚ አቅርበዋል። 

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ከሌሎች ጸሎት ሁሉ በላይ የጥምቀትን እውነታ ያሳያል” ያሉትን የጌታን ጸሎት አብረው እንዲጸልዩ ከጋበዙ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

19 Jan 2023, 13:53