ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኮንጎ የሚታዩትን ግጭቶችን እና ኢኮኖሚያዊ ቅኝ አገዛዝን አውግዘዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጥር 23-28/2015 ዓም በዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 40ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በትላንትናው እለት መጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሐዋርያዊ ጉዞ ባደረጉበት የመጀመሪያ ቀን ከሲቪል ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በአፍሪካዊቷ ሀገር ላይ እየደረሰ ያለውን ግጭት እና የኢኮኖሚ ቅኝ ግዛትን ጨምሮ አንገብጋቢ ጉዳዮችን በማንሳት የኮንጎ ህዝብ ጥቃትን እና ግጭቶችን እንዲቃወም አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማክሰኞ ጥር 23/2015 ዓ.ም ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሲደርሱ በመጀመርያው ንግግራቸው ሀገሪቷ በአሁኑ ወቅት እየቀጠሉ ያሉትን ግጭቶች እና ግዙፍ የተፈጥሮ ሀብቷን በውጭ ሃይሎች መበዝበዙን አውግዘዋል።

በኪንሻሳ በሚገኘው "ፓላስ ዴ ላ ኔሽን" የአትክልት ስፍራ ውስጥ ከመንግስት ባለስልጣናት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ እና ከዲፕሎማቲክ ልዑካን ጋር የተገናኙ ሲሆን በሥፍራው ለነበሩት ለኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኪዲ የአክብሮት ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኮንጎ ህዝብ እጣ ፈንታቸውን በእጃቸው እንዲወስዱ አሳስበዋል።

ጥቃትን እና ጥላቻን በመቃወም

ጉብኝታቸው “የመላውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መቀራረብ፣ ፍቅርና ማጽናኛ” ለማምጣት ካለው ፍላጎት የመነጨ እንደሆነና “የእርቅና የሰላም ተጓዥ በመሆን” ወደ ጎንጎ መጓዛቸውን ቅዱስነታቸው አስረድተዋል።

የኮንጎ ሰዎች ከአልማዛቸው የበለጠ ውድ ናቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሀገሪቱ በጎንጎ ካሉት በርካታ ሀብቶች መካከል አንዱ የሆነውን አልማዝ ማዕድን በተምሳሌትነት በመውሰድ የኮንጐ ህዝብ “በፍሬያማ አፈር ውስጥ ከሚገኙት ከማንኛውም ውድ ሀብት እጅግ የላቀ ነው” ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሃብቶች ባሻገር "ሰላምና ልማት ከተወለደበት" ልባቸው ውስጥ የሚገኝ "መንፈሳዊ ሀብት" እንዳላቸው ገልጸው ለዚህም እያንዳንዱ የኮንጎ ዜጋ "የራሱን ድርሻ ወይም ተግባር እንደሰራ ሊሰማው ይገባል" ብለዋል።  

“እነዚህ ኢሰብአዊ እና ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ስሜቶች በመሆናቸው ልማትን የሚይዙ እና ወደ ቀደመው ጨለማ የሚመልሱን ስለሆኑ ዓመፅና ጥላቻ በማንም ሰው ልብ ውስጥም ሆነ ከንፈር ላይ መኖር የለበትም” ብለዋል።

የደም አልማዞች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና መላው የአፍሪካ አህጉር ዛሬ በ "ኢኮኖሚያዊ ቅኝ ግዛት" መልክ እየደረሰባቸው ያለውን ብዝበዛ በቁጭት ተናግረዋል፣ ይህም "ከባርነት እኩል ሊቆጠር የሚችል ነው” ይህም የኮንጎን ህዝብ ለገዛ መሬቱ "ባዕድ" ያደርገዋል ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።

“የስግብግብነት መርዝ የአልማዝ ማዕድኗን በደም ቀባው” ሲሉ ጳጳሱ የተናገሩ ሲሆን ዓለም ከዚህ ቀደም ለተፈጸመው “አሰቃቂ” ኢፍትሃዊ ድርጊት እውቅና እንዲሰጥ እና እየተካሄደ ያለውን የተፈጥሮ ሀብቷን ዘረፋ እንዲያቆም ጠይቀዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱሱስነታቸው የሚከተለውን በቁጭት ተናግረዋል...

“እጃችሁን ከዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ላይ አንሱ! እጃችሁን ከአፍሪካ አህጉር ላይ አንሱ! አፍሪካን ማነቃችሁን አቁሙ!  የሚዘረፍ ማዕድን ወይም መሬት አይሁን! አፍሪካ የራሷ እጣ ፈንታ ዋና ተዋናይ ትሁን!"

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የሚታየውን ግጭት አለም እንዳላየው ሆኖ አልፏል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዓይኑን ዞር አድርጓል “በተግባር እራሱን ለሚያበላው ሁከት ራሱን አጋልጧል” ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በአፍሪካ ሀገር ልማት እና ሰላምን ለመደገፍ እንደገና ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል ።

"እኔ በጣም የማበረታታቸው አሁን ያሉት የሰላም ሂደቶች በተጨባጭ ተግባራት ሊቀጥሉ ይገባል፣ እናም ቃል ኪዳኖች ሊጠበቁ ይገባል" ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

በዚህ ረገድ ድህነትንና በሽታን ለመዋጋት፣ የህግ የበላይነትን ለማስፈንና የሰብአዊ መብት መከበርን በማስፈን ረገድ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ ያሉ ሀገራትና ድርጅቶች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

"ትክክለኛው ሰብዓዊ የሆነ ዲፕሎማሲ፣ ህዝቦች ለሌሎች ህዝቦች የሚቆረቆሩበት የዲፕሎማሲ ስራ፣ ዲፕሎማሲው በመሬትና በሀብቶች ላይ ቁጥጥር፣ መስፋፋት እና ትርፍ መጨመር ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን ሰዎች እንዲያድጉ እድል በመስጠት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ያስፈልጋል” በማለት ተናግረዋል።

ወደ ጎሰኝነት እና ጠላትነት ከመመለስ ተቆጠቡ

ወደ አልማዝ መዕድን ምስል ስንመለስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንዳሉት ከሆነ የኮንጐ አገር ማህበረሰብ ብልጽግና የመጣው "ጠንካራ ከሆነ ተጨባጭ ከሆነው” ባህሪው ነው፣ ስለዚህም ተጠብቆ መቀመጥ ያለበት እና "ለጎሳ እና ለጠላትነት ምንም አይነት አጸፋዊ መንገድ እንዳይኖር" ነው ብለዋል።

“ችግሩ” ሲሉ የኮንጎን ምሳሌ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የዘር እና የማህበራዊ ቡድኖች ባህሪ ሳይሆን አብረው ለመኖር የሚመርጡበት መንገድ፡ እርስ በርስ ለመገናኘት ፈቃደኞች መሆን ወይም አለመገናኘት፣ መታረቅ እና መጀመር ነው። በአዲስ ግጭት አስከፊነት እና ብሩህ የወደፊት ሰላም እና ብልጽግና መካከል ያለውን ልዩነት እንድንረዳ ያደርጋል ብለዋል።

በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላምን እና ወንድማማችነትን ለመገንባት በቁርጠኝነት የሐይማኖት ተቋማት እና የሲቪል ማህበረሰብ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል ።

በሲቪክ እና በፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ ግልጽነት ያስፈልጋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአልማዝ መዕድን ተምሳሌትነት ላይ ተንተርሰው ሲያደርጉ የነበረውን ንግግር ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት ከሆነ በዜጎች እና በፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ግልጽነት ላይ አተኩረው "በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የመልካምነት ብርሃንን የሚያደበዝዘው ብዙውን ጊዜ የፍትሕ መጓደልና የሙስና ጨለማ ነው" ብለዋል።

በዚህ ረገድ ከግል ወይም ከቡድን ጥቅም ይልቅ ግልጽና ተዓማኒ ምርጫን ማሳደግ እና በሰላማዊ ሒደቱ ውስጥ የላቀ ተሳትፎን እና የጋራ ጥቅምን እና የህዝብን ደህንነትን ማስጠበቅ ያለውን ወሳኝ ጠቀሜታ አስምሮበታል።

በተጨማሪም የግዛቱ ይዞታ በሁሉም የግዛቱ ክፍል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና በርካታ ስደተኞችና ተፈናቃዮች እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል።

የዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎን በጣም ውድ አልማዞች እንዲያንጸባርቁ ያድርጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል "በጣም ውድ የሆኑትን የአልማዝ መዕድን እንዲያበሩ" ለማድረግ በትምህርት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል። በዚህ ረገድ ሁሉም በጣም ብዙ የኮንጎ ልጆች ትምህርት አይማሩም ፣ ይልቁንም በማዕድን ማውጫው ውስጥ ለብዝበዛ እና ለጉልበት ሥራ እንደሚዳረጉ በቁጭት ተናግሯል።

"ልጆች፣ ወጣት ልጃገረዶች እና ሁሉም ወጣቶች የወደፊቱን ተስፋ ይወክላሉ፡ ያ ተስፋ እንዲደናቀፍ አንፍቀድ፣ ይልቁንም በጋለ ስሜት እናዳብረው!" በማለት ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ፣ “መልካም የተፈጥሮ ገጸበረከቶች ተባቂዎች” የመሆን፣ የተፈጥሮ አካባቢን የመጠበቅ የጋራ ኃላፊነትን በማስታወስ የአፍሪካውያንን ሕይወት ለማሻሻል የረዥም ጊዜ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ በአደጋ ጊዜ ከሚደርገው ጣልቃ ገብነት ባለፈ ዘላቂ እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ደፋር እና ሁሉን አቀፍ በሆነ ማህበራዊ እድሳት ውስጥ ይሳተፉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማጠቃለያው ንግግራቸው ላይ የኮንጎ ሕዝብ ለ“ተስፋ መቁረጥ” እና “ትዕግስታቸው እንዳይሟጠጥ” ጥሪ ያደረጉ ሲሆን አክለውም ለማንኛውም ነገር እጅ እንዳይሰጡ፣ ነገር ግን በአገራቸው “ደፋር እና ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እድሳት” እንዲሳተፉ አሳስበዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል...

“[ በክርስቶስ ስም፣ የተስፋ አምላክ፣ የሁሉም ነገር አምላክ የሆነው፣ ሁልጊዜ በአዲስ እንድንጀምር ብርታት በሚሰጠን በዚህች አስደናቂ ምድር እጅግ ውድ በሆነው የአልማዝ መዕድን ክብርና ዋጋ ስም፣ ዜጎቿ በመሆናቸው ሁሉም ሰው ደፋር እና ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እድሳት እንዲያደርግ ማበረታታት እፈልጋለሁ። ] ”

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወቅቱ ግጭቶችና ተግዳሮቶችም የአገሪቱ ፕረዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኪዲ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ተናገሩት ከሆነ ቅዱስ አባታችን ባደረጉት ንግግር ላይ ያተኮሩ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን በመላው ኮንጎ ሕዝብ ስም አመስግነዋል። እናም "በምስራቅ አውራጃዎች ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቆ መጸለይ" እና መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው ከእነዚህ ክልሎች የተፈናቀሉ ልዑካን ቡድንን ለማግኘት ፈቃደኛ ስለነበሩም ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

31 January 2023, 15:25