ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ካቀረቡት አስተምህሮ መልስ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ካቀረቡት አስተምህሮ መልስ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ “እግዚአብሔርን ለማወቅ ልባችን የሚለውን ማድመጥ ያስፈልጋል!”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ጳጉሜ 2/2014 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ከመጽ. ሲራ. 6: 18-19 ተወስዶ በተነበበው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ላይ በማስተንተን ሳምንታዊ አስተምህሮአቸውን አቅርበዋል። ከልዩ ልዩ አገራት ለመጡት ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች ባቀረቡት በዛሬው አስተምህሮአቸው፣ በሎዮላው ቅዱስ ኢግናጢዮስ ሕይወት ውስጥ በታየው ያልተጠበቀ ክስተት በማሰላሰል አስተምህሮአቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በሕይወታችን ውስጥ እግዚአብሔርን ለማወቅ ከፈለግን ከሁሉ አስቀድሞ ልባችንን ማድመጥ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ክቡራት እና ክቡራን፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በዛሬው ዕለት ያቀረቡትን ሳምንታዊ አስተምህሮ ትርጉም ሙሉ ይዘቱን ከማቅረባችን በፊት የዕለቱን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን፥

ልጄ ሆይ! በሕጻንነትህ ጥበብን ምረጣት፤ እስክታረጅም ድረስ ታገኛታለህ። እንደሚያርስ እና እንደሚዘራ ሰው ወደ እርሷ ሂድ፤ የተባረከ ፍሬዋንም ጠብቅ፤ ስለ እርሷ በመሥራት ጥቂት ትደክማለህ፤ ነገር ግን ፈጥነህ ፍሬዋን ትበላለሕ. (መጽ. ሲራ. 6: 18-19)

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

"ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በሳምንታዊው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮም ላይ የምናደርገውን አስተንትኖ በመቀጠል ማስተዋል ምስክርነትን ለመስጠት እንዴት እንደሚያግዘን በዛሬው አስተንትኖ እንመለከታለን።

እጅግ አስተማሪ ከሆኑት ምሳሌዎች መካከል አንዱ የሎዮላው ቅዱስ ኢግናጢዮስ በሕይወቱ የተከተለውን ወሳኝ መንገድ አቅርቦልናል። ቅዱስ ኢግናጢዮስ በጦርነት መካከል እግሩን ካቆሰለ በኋላ ወደ ቤት ተመልሶ ሲያገግም ነበር። እራሱ እያስታመመ እቤት ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት መሰላቸትን ለማስወገድ የሚነበብ መጽሐፍ ካለ ይፈልግ ነበር። በመካከለኛው ዘመን የሚነገሩ ከሃይማኖታዊ ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ማኅበራዊ ሥርዓቶች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተረቶች ይወድ ነበር። ነገር ግን የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ የሚናገሩ መጽሐፍትን ብቻ ነበር ማግኘት የቻለው። በመጠኑም ቢሆን ሳይወድ ቀስ በቀስ ይለማመድ ነበር። ነገር ግን እነዚህን መጽሐፍት በማንበብ በሂደት እርሱን የሚማርክ እና ከባላባቶች ጋር የሚፎካከር የሚመስለውን ሌላ ዓለም ማግኘት ጀመረ። የቅዱስ ፍራንችስኮስ እና የቅዱስ ዶሚኒክ ሕይወት ስለማረከው እነሱን ለመምሰል ፍላጎት ነበረው። ነገር ግን በሌላ ወገን የባላባቶች ዓለም ፍላጎቱን እና ምኞቱን መቀስቀስ አላቋረጠም። በእነዚህ እኩል በሚመስሉ በሚፈራረቁ ሁለት ሃሳቦች ውስጥ ተዘፈቀ።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ አስተምህሮአቸውን በማቅረብ ላይ፤
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ አስተምህሮአቸውን በማቅረብ ላይ፤

ቅዱስ ኢግናጢዮስ አንዳንድ ልዩነቶችን ማስተዋል ጀመረ። በግል የሕይወት ታሪኩ እንዲህ በማለት ጽፏል። “ስለ ዓለማዊ ነገሮች ሳስብ በጣም ደስታ ይሰማኛል። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሁሉ ይደርቅና ያሳዝነኛል፤ ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ ሳስብ፣ እጽዋዕት ብቻ ስለመኖርና ሥነ ሥርዓቶችን እየተለማመድኩ ለመኖር ሳስብ፣ እነርሱን ሳስብ ብቻ ሳይሆን ሃሳቤን ከጨረስኩ በኋላም ደስታ ይሰማኛል” በማለት ገልጿል።

በዚህ የቅዱስ ኢግናጢዮስ የሕይወት ልምድ ከሁሉም በላይ ሁለት ገጽታዎችን እናስተውላለን። የመጀመሪያው ጊዜ ነው። ዓለማዊ ሀሳቦች መጀመሪያ ላይ እጅግ ማራኪ ናቸው። ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ውበታቸውን ያጣሉ። ባዶነት እና እርካታ ቢስነት ይታይባቸዋል። የእግዚአብሔር ሀሳቦች በተቃራኒው መጀመሪያ ላይ የተወሰኑ ተቃውሞችን ያስነሳሉ። ነገር ግን ተቀባይነትን ሲያገኙ በጊዜ ሂደት የማይገመት ሰላምን ያጎናጽፋሉ።

የቅዱስ ኢግናጢዮስ የሕይወት ልምድ ሁለተኛው ገጽታ፣ የሃሳቦቹ የመጨረሻ ነጥብ ነው። መጀመሪያ ላይ ሁኔታው ግልጽ ባለመሆኑ የማስተዋል እድገት ይታይበታል። የሚጠቅመንን ነገር የምንረዳው በረቂቅነቱ ሳይሆን በሕይወታችን ጉዞ ውስጥ ነው።

ቅዱስ ኢግናጢዮስ በማስተዋል ደንቦች ውስጥ መሠረታዊ የልምድ ሂደትን ለመረዳት የሚያስችል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታን አስቀምጧል። ሞትን የሚያስከትል ኃጢአት በሠሩ ሰዎች ውስጥ፣ ጠላት ብዙውን ጊዜ ግልጽ የሆኑ የተድላ ጥያቄዎችን በመጠየቅ፣ ሥጋዊ ደስታን እና ተድላዎችን እንዲያስቡ በማድረግ እነሱን መንገዶችን ተከትለው በክፉ ምግባራቸው እና በኃጢአታቸው እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል። በእነዚህ ሰዎች ውስጥ መልካሙ መንፈስ ምክንያታዊነት በመከተል ሕሊናቸውን እየወጋውና እያቆሰለው ተቃራኒውን መንገድ እንዲራመዱ ታደርጋቸዋል። (መንፈሳዊ ልምምዶች ቁ. 314)

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ፊ ለፊት በተዘጋጀላቸ ሥፍራ ሆነው አስተምህሮአቸውን በማቅረብ ላይ
ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ፊ ለፊት በተዘጋጀላቸ ሥፍራ ሆነው አስተምህሮአቸውን በማቅረብ ላይ

ማስተዋልን የሚቀድም ሌላ አንድ ታሪክ አለ። ይህን ታሪክ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው።  ምክንያቱም ማስተዋል በሁለት ዕድሎች ላይ ዕጣ እንደመጣል ዓይነት አይደለም። ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች የሚነሱት ሰፊ የሕይወት መንገዶችን ከተጓዝናቸው በኋላ እና የምንፈልገውን ነገር ለመረዳት ስንፈልግ ነው። ቅዱስ ኢግናጢዮስ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በአባቱ ቤት እያለ ስለ እግዚአብሔር የሚያውቀው ነገር አልነበረውም፣ የራሱን ሕይወት እንዴት ማሻሻል እንዳለበት አያስብም ነበር። እግዚአብሔርን ለማወቅ ያስቻለው የመጀመሪያ ልምዱ የራሱን ልብ ማዳመጥ ነበር። ይህም አስደናቂ የሆኑ የተገላብጦሽ እይታዎችን አቀረበለት። የመጀመሪያ እይታው በሚያምሩ ነገሮች ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን ብዙም የማያስደስት ቢሆንም ዘላቂነት ያለው ሰላምን ማግኘት ቻለ።

ቅዱስ ኢግናጢዮስ የቅዱሳንን የሕይወት ታሪክ እንድናነብ የሚጠቁመን ለዚህም ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ዘይቤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ለእኛ በጣም የተለየ አለመሆኑን በትረካ እና ለመረዳት በሚያስችል መንገድ ያስረዳሉ። ድርጊታቸው ስለ እኛ ድርጊት ስለሚናገሩ ትርጉማቸውን በቀላሉ እንድንገነዘብ ይረዱናል።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮአቸው ማብቂያ ሰላምታ ሲለዋወጡ
ቅዱስነታቸው በአስተምህሮአቸው ማብቂያ ሰላምታ ሲለዋወጡ

ባለፈው ጊዜ በተመለከትነው አስተምህሮ ውስጥ ሌላ ጠቃሚ የማስተዋል ገጽታ መኖሩን ልንገነዘብ እንችላለን።ሁሉም ነገር የሚጀምረው ከሌላ ሳይሆን ከቅዱሳን ሕይወት ነው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቅዱስ ኢግናጢዮስ ግንዛቤን ማግኘት የቻለው በቅዱሳን ሕይወት ላይ ትኩረት በማድረግ ነው። እግዚአብሔር ሥራውን የሚያከናውነው በማይታቀዱ ክስተቶች እና በተሳሳቱ አካሄዶች ውስጥ ነው። ይህን በማቴዎስ ወንጌል ውስጥም አይተናል። አንድ ሰው እርሻ ሲያርስ በአጋጣሚ የተቀበረ ሀብት አገኘ። በፍጹም ያልተጠበቀ ሁኔታ ነበር። ነገር ግን አስፈላጊው የሕይወት ዕረፍት እንዳገኘ መረዳት እና በዚህ መሠረት ውሳኔውን ማስተካከሉ ነው። ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛ።

ማስተዋል ባልተጠበቁ እና ደስ በማይሉ ሁኔታዎች መካከል፣ እንደ ቅዱስ ኢግናጢዮስ የእግሩ ቁስል፣ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን እንዲያውቅ የሚረዳ ምልክት የሚገኝበት እና ሕይወትን ለዘላለም የሚለውጥ ገጠመኝ የሚፈጠርበት መንገድ ነው።"

07 September 2022, 16:53