ፈልግ

በካዛክስታን የሚገኝ መስጊድ በካዛክስታን የሚገኝ መስጊድ  

በዓለም ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት እና ባህላዊ እምነቶች 7ኛው የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራ

በካዛኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባለብዙ ወገን ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ዲዳር ቴሜኖቭ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሚሳተፉበት 7ኛው በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሐይማኖቶች እና ባህላዊ እምነቶች መሪዎች ሸንጎ ላይ ያላቸውን እይታን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን “የሃይማኖት መሪዎች በዓለም ውስጥ የሚታዩትን ግጭቶች የመፍታት ኃላፊነት አለባቸው” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 5 በካዛኪስታን ዋና ከተማ ኑር-ሱልጣን ውስጥ ለሚካሄደው 7ኛው በዓለም ውስጥ የሚገኙ የሐይማኖት ተቋማት እና የባህል እምነቶች መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመካፈል ማክሰኞ መስከረም 3 ቀን ወደ እዚያው ወደ ካዛክስታን እንደሚያቀኑ ይታወቃል። በዝግጅቱ ላይ የአልአዛር ታላቅ ኢማም አህመድ አል ታየብ እና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካዮችን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ካሉ የሃይማኖት መሪዎች ሰላምን ለማስፈን እና ተጨባጭ ቁርጠኝነትን ለማስፈን ውይይት ይደረጋል።

ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ በዚህ ዓመት የሃይማኖት መሪዎች ከወረርሽኙ በኋላ በሚኖራቸው ሚና ላይ ያተኮረበትን ዝግጅት ፍንጭ ሰጥተዋል።

የሸንጎ ተልዕኮ

"የሸንጎ ተልእኮ በዓለም ዙሪያ በተለይም በዚህ በጣም ፈታኝ ጊዜ በሐይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር እና የጎሳ መግባባትን የበለጠ ማጠናከር ነው" ብሏል።

"በአሁኑ ጊዜ አለም በታላቅ ፈተናዎች ውስጥ ትገኛለች፣ እናም በዚህ ጊዜ የሀይማኖት መሪዎች በአስቸጋሪ ጊዜያችን ውስጥ የሀይማኖት ተቋማት በሐይማኖት ተቋማት መካከል ለሚደረገው ውይይት ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከታቸው በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል።

ሃይማኖት “በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ በጣም ጠቃሚ ሚና የሚጫወተው” ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ “የፖለቲካ አለመግባባቶች ሃይማኖታዊ አካላትን ያጠቃልላል” በማለት አጉልቶ ያሳዩት የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ  ገልጿል።

"በአለም ላይ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት የሃይማኖት መሪዎች ትልቅ ተጽእኖ እና ስልጣን አላቸው ነገር ግን በጣም አስፈላጊው ነገር በተለያዩ ሀይማኖቶች መካከል እንዲሁም በአገሮች መካከል የሚደረገውን ውይይት ማስተዋወቅ ነው" በማለት አክለው የገለጹ ሲሆን "ከዚህ ጋር በተያያዘም የዚህ ሸንጎ ሚና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የሐይማኖት ተቋማት መካከል እና የጎሳ መግባባትን ለማጠናከር ያለመ ነው" ብለዋል።

የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ ሸንጎ  "ዓለም ወደ ከፍተኛ መግባባት እና ውይይት እንዲመጣ" እንደሚረዳ ያላቸውን ተስፋ ገልጿል።

የሸንጎ ታሪክ

የሸንጎ ታሪክ እ.ኤ.አ. በ 2003 የካዛኪስታን ፕሬዝዳንት የነበሩት ኑር-ሱልጣን ናዛርባይቭ የመጀመሪያውን ጉባሄ ያስተናገዱበት ወቅት ነው "በዩናይትድ ስቴትስ በ9/11 የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ ለሃይማኖታዊ ውጥረት እና ጽንፈኝነት መነሳት ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት" ታስቦ የተቋቋመ ሸንጎ ነው።

"የሃይማኖት ተቋምት መሪዎች ሃይማኖት ሰዎችን፣ ማህበረሰቦችን እና ህዝቦችን ለመከፋፈል እንዳይጠቀሙበት ለማድረግ እድል ለመፍጠር በጣም ወሳኝ ወቅት ነበር ብለን እናምናለን" በወቅቱ ማለታቸው ይታወሳል።

ስድስት የዓለም ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሃይማኖቶች ሸንጎ ተካሂደዋል እናም የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ እንደ ገለጹት ከሆነ ሀገራቸው 7ተኛውን ሸንጎ  ለማዘጋጀት በጉጉት እንደምትጠባበቅ ተናግረዋል።

"ከቀደምቶቹ ጋር ሲወዳደር ከትልቅ ሸንጎዎች መካከል አንዱ ይሆናል" በማለት የተናገሩ ሲሆን "የዛሬ 20 አመት ገደማ የቁጥር አሃዝ እንደ ሚያሳየው የመጀመሪያው ኮንግረስ ሲጀመር 17 ልዑካን ብቻ ናቸው የተሳተፉት” በማለት የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ ገልጸዋል።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሚደረግ አቀባበል

የዘንድሮው ኮንግረስ ከ50 ሀገራት የተውጣጡ 100 የሚያህሉ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሎ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን በተሳታፊዎች ብዛት ከፍተኛውን ቁጥር እና የተከበሩ ልዑካንን ጥራት ያሳያል ብለዋል ሚስተር ተሜንኖቭ።

"በእርግጥ ይህ ለማስተናገድ በጣም የምንጓጓለትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን መምጣት ይጨምራል" ሲሉ ሚንስትሩ አክለው ገልጸዋል።

በርካታ ሃይማኖቶች የሚወከሉ ሲሆኑ፣ ሌሎች ተሳታፊዎች የታላቁ አል አዝሃር ኢማም አህመድ አል ታይብ ይገኙበታል።  የሞስኮ ፓትርያርክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አንቶኒጂ ቮሎኮላማስክ፣ አሽኬናዚ ዋና መምህር የሆኑት የእስራኤሉ ዴቪድ ላው፣ እና የእስራኤል የሴፋርዲክ ዋና አለቃ የሆኑት መምህር ይስሐቅ ዮሴፍ፣ እና የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ III በሸንጎ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የሸንጎ ዋና ጸሐፊ ከበርካታ የአለም ሀይማኖቶች ቋሚ ተወካዮች ጋር በመሆን በተሳታፊዎች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

አጣዳፊ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሃይማኖት ሚና

የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ እንዳሉት ሸንጎ የሃይማኖት መሠረታዊነት እየጨመረ በመጣበት ዓለም ልዩ የሰላም መልእክት ለመላክ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዓለም “ግጭቶችን፣ ወረርሽኞችን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ጨምሮ በርካታ ቀውሶች ሲያጋጥሟት” እንደነበር ተናግሯል።

"በዚህ በጣም አስቸጋሪ ወቅት ሃይማኖት ለህብረተሰቡ የማዕዘን ድንጋይ ሊሆን እና ሊረዳን ይችላል ብለን እናምናለን። በአስቸጋሪ ጊዜያት እንድንራመድ ይረዳናል” ብሏል።

ስለዚህም "የሃይማኖት መሪዎች በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ ልማት ውስጥ ትልቅ ሚና ቢጫወቱ እና በአሁኑ ጊዜ በጣም አሳሳቢ የሆኑ ጥያቄዎችን መፍታት በጣም አስፈላጊ ነው" ሲል አጥብቆ ይናገራል።

ለጋራ መፍትሄ ቁርጠኝነት

የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ በመላው ምድራችን ላይ ላሉ ሰዎች ሰላማዊ እና ጨዋነት ያለው ህይወት ለማስተዋወቅ ተስፋ እያደርጋሉ።

"በሰላምና መረጋጋት ስም ሸንጎ ለአለም አቀፍ የሃይማኖቶች ውይይቶች እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት እናምናለን። እናም በዚህ ቁርጠኝነት ለአለም አቀፍ አለመግባባቶች የጋራ መፍትሄ ለመስጠት ሸንጎ በምስራቃዊ እና በምዕራባውያን ስልጣኔዎች መካከል የጋራ መግባባት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል” ሲሉ የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ ገልጸዋል።

ሸንጎ በተሳታፊዎች የተፈረመ የመጨረሻ ሰነድ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

"በሸንጎ ማብቅያ ላይ መግለጫ ለመስጠት አቅደናል፣ እናም መሪዎቹ ለአለም ህዝብ መላክ የሚፈልጓቸውን ጠቃሚ መልዕክቶች በሙሉ እንደሚካተቱ ተስፋ እናደርጋለን" ያሉት የካዛኪስታን የባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳይ ክፍል ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት ዲዳር ተምኖቭ በአሁኑ ጊዜ የማስታወቂያው ጽሑፍ በተወካዮቹ ግምት የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

መግለጫው የሚነበበው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኑር ሱልጣንን በሚጎበኙበት የመጨረሻ ቀን ላይ ሲሆን በዚያን ጊዜም ለሸንጎ የማጠቃለያ ንግግር ያደርጋሉ።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቁርጠኝነት ለሃይማኖቶች ውይይት እና ጓደኝነት

በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረግ ውይይት ሁል ጊዜ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ልብ ጋር በጣም የቀረበ ነው፣ በአቡ ዳቢ የተፈረመው የሰው ልጅ ወንድማማችነት ሰነድ እና ይህንን ተከትሎ በጣልያነኛ ቋንቋ “fratelli tutti” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክታቸው ላይ ይህንን መታዘብ ይቻላል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግላቸው በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በተደረጉ ውይይቶች ላይ ተሳትፈዋል እናም ሁልጊዜም ከሌሎች የእምነት መሪዎች ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ጠብቀዋል።

12 Sep 2022, 12:09