ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለ2022 የዓለም የድሆች ቀን ያሰተላለፉት መልእክት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለ2022 የዓለም የድሆች ቀን ያሰተላለፉት መልእክት  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለ2022 የዓለም የድሆች ቀን ያሰተላለፉት መልእክት

“ለእናንተ ሲል ክርስቶስ ድሃ ሆነ” (2ቆሮ. 8፡9)

1. “ኢየሱስ ክርስቶስ… ለእናንተ ሲል ድሃ ሆነ” (2ቆሮ. 8፡9)። ሐዋርያው ​​ጳውሎስ በቆሮንጦስ የመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች በችግር ላይ ለነበሩ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት የምያደርጉትን ጥረት እንዲቀጥሉ ለማበረታታት በማሰብ እነዚህ ቃላት ተጠቅሞ ተናግሯቸዋል። የአለም የድሆች ቀን በዚህ አመት እንደ አንድ ጤናማ ተግዳሮት ሆኖ ይመጣል፣ ይህም በአኗኗራችን እና በዙሪያችን ስላሉት በርካታ የድህነት ዓይነቶች እንድናሰላስል ይረዳናል።

ከበርካታ ወራት በፊት ዓለም ከወረርሽኙ አውሎ ንፋስ ነፃ እየወጣች ነበር፣ በዚህም የተነሳ በኢኮኖሚ ፍሰት ረገድ የማገገሚያ ምልክቶች እየታዩ ሲሆን ይህም ሥራ በማጣታቸው የተነሳ ወደ ድህነት አዝቅት እየወረዱ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እየታደገ ይገኛል። ውድ ወገኖቻችንን በማጣታችን የተነሳ የደርሰብንን ሐዘን ሳንቀንስ ወደ ቀጥተኛ የእርስ በርስ ግንኙነት እንደሚመልሰን እና ያለ ተጨማሪ እገዳ እና ገደብ እርስ በርስ ለመቀራረብ ቃል የገባልን ሰማያዊ ሰማይ ተከፈተ። አሁን ግን በዓለማችን ላይ በጣም የተለየ ሁኔታ ለመፍጠር የታሰበ አዲስ ጥፋት ከአድማስ ላይ ታየ።

በዩክሬን ውስጥ ያለው ጦርነት ለዓመታት ከባድ ሞት እና ውድመት ከደረሰባቸው በተለያዩ አገራት ውስጥ እየተከሰቱ ከሚገኙ ጦርነቶች ጋር ተደምሯል። ነገር ግን እዚህ ላይ የሰዎችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መርህ በመጣስ የራስን ፍላጎት ለመጫን የታለመ "የልዕለ ኃያል" አገራት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ሁኔታው ​​​​ይበልጥ የተወሳሰበ እንዲሄድ አድርጎታል። አሳዛኝ ሁኔታዎች እንደገና እየተስተዋሉ ነው፣ እናም ጥቂት ኃይሎች የምያቀርቡት አጸፋዊ ቅድመ ጥያቄዎች ለሰላም የሚጮኽውን የሰው ልጅ ድምጽ እያፈኑ ይገኛሉ።

2.  በግድየለሽነት የሚፈጠር ትርጉም የለሽ ጦርነት እንዴት ያለ ታላቅ ድህነት ይፈጠራል! የትም ብንመለከት፣ መከላከያ የሌላቸውን እና ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዴት እንደሚደርስ ማየት እንችላለን። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከየተኛውም ወጣት ወንድ እና ሴት ልጆች በላይ ሥር መሰረቶቻቸውን ለመቁረጥ እና ሌላ ማንነት ለመጫን ሲባል እየተባረሩ እንደ ሆነ እናስባለን። አሁንም የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ቃላት እነዚህ ጉዳዮች ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል። የኢየሩሳሌምን ጥፋትና የዕብራውያን ወጣቶች ግዞት በማሰላሰል እንዲህ ሲል ዘምሯል:- “በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን። እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን። የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን። የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!” ( መዝ 137፡1-4 )

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች፣ ህጻናት እና አረጋውያን በጎረቤት ሀገራት ተፈናቅለው ጥገኝነት ለማግኘት ሲሉ የቦምብ አደጋን በድፍረት እንዲጋፈጡ እየተገደዱ ይገኛሉ። ምን ያህሉ በጦርነቱ ቀጠና ውስጥ ቀርተው በየቀኑ በፍርሃት እና በምግብ፣ በውሃ፣ በህክምና እና ከሁሉም በላይ የሰው ፍቅር እጦት እየኖሩ ነው? በእነዚህ ሁኔታዎች ምክንያቱ ጨልሟል እና ውጤቱ የምሰማቸው ቀድሞውንም እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ተራ ሰዎች ናቸው። ለዚህ ሁኔታ በቂ ምላሽ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? እናም እርግጠኛ ባልሆነ መንገድ እና ባለመረጋጋት ውስጥ ገብተው ለሚኖሩ ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች እፎይታ እና ሰላምን ማምጣት የምንችለው እንዴት ነው?

3. በዚህ ታላቅ ግጭት ውስጥ ስድስተኛውን የዓለም የድሆች ቀን እያከበርን ነው። “ሀብታም ቢሆንም፣ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድንሆን ስለ እኛ ድሃ ሆነ” በሚለው በኢየሱስ ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ በሐዋርያው ​​ጥሪ ላይ እንድናሰላስል ተጠየቅን (2ኛ ቆሮ 8፡9) ጳውሎስ ኢየሩሳሌምን በጐበኘበት ወቅት ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ተገናኘ፤ እርሱም ድሆችን እንዳይረሱ አሳስቧቸዋል። የኢየሩሳሌም ማህበረሰብ በሀገሪቱ በተከሰተው የምግብ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ነበር። ሐዋርያው ​​ወዲያው በድህነት የተጎዱትን ለመርዳት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ማደራጀት ጀመረ። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችም እርሱ የሚያከናውነውን ተግባር በጣም ተረድተው ይደግፉት ነበር። ጳውሎስ ባቀረበው ጥያቄ፣ በእያንዳንዱ የሳምንቱ የመጀመርያ ቀን መዳን የሚፈልጉ ሰዎችን በሙሉ ሰበሰቡ እናም ሁሉም በጣም ለጋስ ሆነዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየእሁዱ የቅዱስ ቁርባን አከባበር ላይ ህብረተሰቡ የድሆችን ፍላጐት ለሟሟላት መባዎቻችንን በማሰባሰብ ተመሳሳይ ነገር እናደርጋለን። ማንኛቸውም ወንድሞቻችን ወይም እህቶቻችን ለሕይወታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እንዳያጡ ለማድረግ ክርስቲያኖች ሁል ጊዜ በደስታና በኃላፊነት ያደርጉት የነበረ ነገር ነው። ለዚህም በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለንጉሠ ነገሥት አንጦኒኖስ ፒዮስ ጽፎ የክርስቲያኖችን የእሁድ እለት አከባበር ከገለጸው ከቅዱስ ያዕቆብ ሰማዕትነት ማረጋገጫ አግኝተናል። በእሱ አነጋገር “በእሁድ ቀን በከተማው ውስጥም ሆነ በአውራጃው ውስጥ ከሚኖሩ ከሁሉም አባሎቻችን ጋር ስብሰባ እናደርጋለን። ጊዜ እስካለ ድረስ የሐዋርያት ወይም የነቢያት ድርሳናት ይነበባሉ… ቅዱስ ቁርባን ይከፋፈላል፣ ዲያቆናቱም ላልተገኙ ሰዎች ሁሉ ወደ ቤታቸው ይወስዳሉ። ሀብታሞች ከፈለጉ መዋጮ ማድረግ ይችላሉ፣ እናም መጠኑን ይወስናሉ። መባው የሚቀመጠው በሊቀመንበር ሥር ሲሆን ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን እና መበለቶችን እና በማንኛውም ምክንያት በችግር ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለመርዳት ይጠቀምበታል፣ በህመም፣ በእስር ላይ ለሚገኙ እና ከቤት ርቀው ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ይከፋፈላል። በአንድ ቃል ለተቸገሩ ሁሉ እንክብካቤ ለመስጠት ይውላል”።

4. የቆሮንጦስ ማህበረሰብን በተመለከተ፣ ከመጀመርያው የጋለ ስሜት ፍንዳታ በኋላ፣ ቁርጠኝነታቸው እየቀነሰ ሄደ እናም በሐዋርያው ​​የቀረበው ተነሳሽነት የተወሰነ መነሳሳትን አጥቷል። በዚህ ምክንያት ጳውሎስ “አሁንም የጀመራችሁትን ተግባር በዐቅማችሁ መጠን ከፍጻሜ አድርሱት” (2ኛ ቆሮ 8፡11) መባ መሰብሰቡን እንደገና እንዲያስጀምሩ በጭንቀት በመጠየቅ ጽፎላቸዋል።

እኔ እንደማስበው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በመካከለኛው አፍሪካ እና አሁን በዩክሬን ውስጥ ካሉ ጦርነቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመቀበል መላው ህዝብ በራቸውን እንዲከፍቱ ያደረገው የልግስና ጊዜ ይታያል። የተለያዩ የቤተሰብ አባላት ለሌሎች ቤተሰቦች ቦታ ለመስጠት ቤታቸውን ከፍተዋል፣ እናም ማህበረሰቦች ከሚገባው ክብር ጋር እንዲኖሩ ለማድረግ ብዙ ሴቶችን እና ህጻናትን በልግስና ተቀብለዋል። ይህ ሆኖ ግን ግጭቶች በቆዩ ቁጥር ውጤታቸው የበለጠ ሸክም ይሆናል። አቀባበል የሚያደርጉ ህዝቦች የእርዳታ ጥረታቸውን ለማስቀጠል በጣም አዳጋች ሆኖባቸዋል። ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች አደጋ ከእለት እለት በመጠኑ እና በዓይነቱ እየጨመረ እና እየቀጠለ ሲሄድ ሸክም እየበዛባቸው እንደ መጣ ይሰማቸዋል። ተስፋችንን ሳንቆርጥ የመጀመርያ ተነሳሽነታችንን የምናድስበት ጊዜ ይህ ነው። የጀመርነውን ሥራም በተመሳሳይ የኃላፊነት ስሜት ወደ ፍጻሜው ማምጣት ያስፈልጋል።

5. ያ በእውነቱ በትክክል አብሮነት ማለት ነው፤ ያለንን ትንሽ ነገር ምንም ከሌለው ሰው ጋር መካፈል ያስፈልጋል። የማህበረሰብ እና የመተሳሰብ ስሜት እንደ የህይወት ዘይቤ መሆን ይጀምራል እናም የመተሳሰብ ስሜት ያድጋል። በአንዳንድ አገሮች፣ ባለፉት አሥርተ ዓመታት፣ ቤተሰቦች በብልጽግና እና በደኅንነት ዙሪያ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዳጋጠማቸው ማሰብ አለብን። ይህ በግል ተነሳሽነት እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በመደገፍ እንዲሁም ቤተሰቦችን እና ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመደገፍ ተጨባጭ ማበረታቻዎች አዎንታዊ ውጤት ነው። ከደህንነት እና መረጋጋት አንፃር ያለው ጥቅም አሁን ለደህንነት እና ህልውና ፍለጋ ቤታቸውን እና የትውልድ አገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ ለተገደዱ ሰዎች ሊጋራ ይችላል። እንደ ሲቪል ማህበረሰብ አባላት የነፃነት ፣የሃላፊነት ፣የወንድማማችነት እና የአብሮነት እሴቶችን አስጠብቀን እንቀጥል። እናም እንደ ክርስቲያኖች፣ ሁሌም ልግስናን፣ እምነትን እና ተስፋን የህይወታችን እና የተግባራችን መሰረት እናድርግ።

6. ሐዋርያው ​​ክርስቲያኖችን የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እንዲሠሩ ለማስገደድ እንደማይፈልግ ማወቁ ትኩረት የሚስብ ነው፡- “ይህን እንደ ትእዛዝ አልልም” (2ቆሮ. 8፡8) በማለት ይናገራል። ጳውሎስ በምትኩ “የፍቅራቸውን እውነተኛነት” ለድሆች ባላቸው ልባዊ አሳቢነት እንዲያከናውኑ ነው የሚያሳስባቸው።  በእርግጠኝነት የጳውሎስ ጥያቄ የሚነሳው በተጨባጭ የእርዳታ አስፈላጊነት ላይ ነው፣ ቢሆንም የእሱ ፍላጎት የበለጠ ጥልቅ ነው። እሱ ራሱ ኢየሱስ ያሳየው ፍቅር የፍቅር ምልክት እንዲሆን የቆሮንቶስ ሰዎች መባ እንዲሰበስቡ ጠይቋል። በአንድ ቃል ለድሆች የሚደረግ ልግስና ትልቅ ተነሳሽነት ያለው በእግዚአብሄር ልጅ ምሳሌነት፣ ድሃ ለመሆን በመረጠው ነው።

በእርግጥ ሐዋርያው ​​ግልጽ ያደረገው ይህ በክርስቶስ በኩል ያለው ምሳሌ፣ ይህ “ንብረት መውረስ”፣ ጸጋ ነው፤ “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ” (2ቆሮ 8፡9)። በመቀበል ብቻ ለእምነታችን ተጨባጭ እና ተከታታይነት ያለው መግለጫ መስጠት እንችላለን። በዚህ ረገድ የመላው አዲስ ኪዳን ትምህርት አንድ ነው። የጳውሎስ ትምህርት ሐዋርያው ​​ያዕቆብ “    ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። ቃሉን የሚሰማ፣ ነገር ግን የሚለውን የማይፈጽም ሰው ፊቱን በመስተዋት እንደሚያይ ሰው ነው፤ ራሱንም አይቶ ይሄዳል፤ ወዲያውም ምን እንደሚመስል ይረሳል፤ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ ተመልክቶ የሚጸና፣ የሰማውን የሚያደርግና የማይረሳ ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል” (ያዕ. 1፡22-25)።

7. ድሆች በሚጨነቁበት ቦታ ወሬ ማውራት ምንም ዋጋ የለውም፣ ዋናው ነገር እጆቻችንን መዘርጋት እና እምነታችንን በቀጥታ ተሳትፎ በማድረግ ተግባራዊ መልስ መስጠት ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን አንድ አይነት ችልተኝነት ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ወደ ወጥነት የለሽ ባህሪ ሊያመራ ይችላል፣ ለድሆች የምናሳየውን ግድየለሽነት ጨምሮ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ከገንዘብ ጋር ከመጠን ያለፈ ቁርኝት በመፍጠራቸው የተነሳ ንብረቶቻቸውንና ሀብቶቻቸውን በመጥፎ አጠቃቀም ውስጥ አስገብተው ማቆየትን ይመርጣሉ። እነዚህ ሁኔታዎች ደካማ እምነት፣ ደካማ እና የማይታወቅ ተስፋ ያሳያሉ።

ጉዳዩ ገንዘብ እንዳልሆነ እናውቃለን፣ ምክንያቱም ገንዘብ እንደ ግለሰብ እና በህብረተሰብ ውስጥ ያለን ግንኙነት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ነው። ከዚህ ይልቅ ልንገነዘበው የሚገባን ለገንዘብ የምንሰጠው ዋጋ ነው፣ ይህም የሕይወታችን ፍፁም እና ዋና ዓላማ ሊሆን አይችልም። ከገንዘብ ጋር መያያዝ የዕለት ተዕለት ኑሮን ከእውነታው ጋር እንዳናይ ያደርገናል፤ ዓይኖቻችንን ያጨልማል እና የሌሎችን ፍላጎት እንዳናይ ያደርገናል። በሀብት ጣዖት ከመደነቅ የባሰ በክርስቲያን እና በአንድ ማህበረሰብ ላይ ሊደርስ የሚችል አደጋ የለም፣ ይህም መጨረሻው ጊዜያዊ እና የከሰረ የህይወት ራእይ ላይ ሰንሰለት እንደ ማሰር ይቆጠራል።

እንደተለመደው "በማሕበራዊ ደኅንነት አስተሳሰብ" ወደ ድሆች መቅረብ ሳይሆን ማንም ሰው አስፈላጊውን ነገር ማጣት እንደ ሌለበት የሚያመልክት ጥያቄ ነው። ይህን የሚያድነው ማሕበራዊ አንቂ ሳይሆን ከልብ እና ለጋስ መተሳሰብ ነው ወደ ድሀ ሰው እንድንቀርብ የሚያደርገን እንደ ወንድም ወይም እህት እጁን ዘርግቶ ከገባበት መከራ እንዲወጣ የሚጠይቀንን ወዳጃችችን ማገዝ ይኖርብናል። ስለዚህ “ማንም ሰው ከድሆች ጋር መቀራረብ እንደማይችል ሊናገር አይገባውም፣ ምክንያቱም አኗኗራቸው ለሌሎች አካባቢዎች የበለጠ ትኩረትን ይፈልጋል። ይህ በእውቀት፣ በንግድ ወይም በሙያተኛ፣ አልፎ ተርፎም በቤተክርስቲያን ክበቦች ውስጥ የሚሰማ ሰበብ ነው… ማናችንም ብንሆን ለድሆች እና ለማህበራዊ ፍትህ ከመጨነቅ ነፃ ነን ብለን ማሰብ አንችልም።” (ኢቫንጀሊ ጋውዲየም፣ አንቀጽ 201)። “ለድሆች ፖሊሲ እንጂ ከድሆች እና ከድሆች ጋር ፈጽሞ፣ ህዝብን የሚያቀራርብ የፕሮጀክት አካል ነው” ተብለው ከታሰቡት ማህበራዊ ፖሊሲዎች አካሄድ ያለፈ አዳዲስ መፍትሄዎችን በአስቸኳይ መፈለግ ያስፈልጋል። ከዚህ ይልቅ የሐዋርያውን አመለካከት መኮረጅ ያስፈልገናል፤ ለቆሮንጦስ ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ይህንን የምንለው እናንተ ተቸግራችሁ ሌሎች ይድላቸው ለማለት ሳይሆን፣ ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው” (2 ቆሮ 8፡13)

8. ዛሬ እንደ ጥንቱ ሁሉ መቀበል የሚከብደን ከሰዋዊ አስተሳሰብ ጋር የሚጋጭ ነው፡- ባለጠጋ ሊያደርገን የሚችል የድህነት አይነት አለ። ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስን “ጸጋ” በመለመን የሰበከውን መልእክት ማረጋገጥ ይፈልጋል። እውነተኛ ሀብት “ብልና ዝገት የሚበሉትን ሌባም ቈፍረው የሚሰርቁትን በምድር ላይ ሀብት በማከማቸት” (ማቴ 6፡19) ሳይሆን እንድንሸከም በሚያደርገን አጸፋዊ ፍቅር ውስጥ እንዳልሆነ መልእክቱ ነው። አንዱ የሌላውን ሸክም መሸከሙ ማንም እንዳይቀር ወይም እንዳይገለል ያደርገዋል ማለት ነው። በእነዚህ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያጋጠመን የድክመት እና የአቅም ውስንነት ስሜት አሁን ደግሞ ጦርነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ያስከተለው አሳዛኝ ክስተት አንድ ወሳኝ ነገር ሊያስተምረን ይገባል፡ በዚህ አለም ውስጥ ያለነው ለመኖር ብቻ ሳይሆን በክብር እና በደስታ እንድንኖር ነው። ሕይወት የኢየሱስ መልእክት መንገዱን ያሳየናል እና የሚያዋርድ እና የሚገድል ድህነት እንዳለ እንድንገነዘብ ያደርገናል፣ እናም ሌላ ድህነት፣ የክርስቶስ ድህነት፣ ነፃ የሚያወጣን እና ሰላም የሚያመጣልን የክርስቶስን የድህነት ዓይነት መላበስ ይኖርብናል።

የሚገድለው ድህነት የግፍ ልጅ፣ የግፍ አስተሳሰብ፣ የብዝበዛ፣ የአመጽ እና ኢፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ልጅ ነው። ተስፋ የለሽ እና ማምለጫ መንገድን በማይሰጥ በተረሳው ባህል የተነሳ የተተከለው ድህነት ነው። ሰዎችን ወደ ከፍተኛ ቁሳዊ ድህነት የሚዳርግ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን ገጽታ የሚሸረሽር፣ ብዙ ጊዜ የሚታለፍ ቢሆንም፣ አሁንም እንዳለ እና አሁንም አስፈላጊ ነው። ብቸኛው ህግ በቀኑ መጨረሻ ላይ የትርፍ ማጋበስ መስመር ሲሆን ሌሎችን በቀላሉ ለመበዝበዝ እንደ እቃ ከማየት የሚከለክለን ምንም ነገር የለም፣ ሌሎች ሰዎች የፍጻሜ ዘዴዎች ናቸው። እንደ ፍትሃዊ ደመወዝ ወይም የስራ ሰዓት ያሉ ነገሮች የሉም፣ እናም አዳዲስ የባርነት ዓይነቶች ብቅ እያሉ አማራጭ የሌላቸውን ሰዎች ወጥመድ ውስጥ ያስገባ እና ኑሮን ለማሸነፍ ሲሉ ብቻ ይህን መርዛማ ግፍ ለመቀበል ይገደዳሉ።

ነፃ የሚያወጣን ድህነት ግን ሁሉንም የሞተ ክብደት መጣል እና አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ በማተኮር በኃላፊነት ውሳኔ ምክንያት የሚመጣ ነው። ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ አንድ አስፈላጊ ነገር እንደጎደለ ስለሚገነዘቡ የሚሰማቸውን እርካታ ማነስ በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን፤ በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ለመፈለግ ያለ ዓላማ ይንከራተታሉ። እነርሱን የሚያረካ ነገር ለማግኘት በሚፈልጉበት ጊዜ፣ የጎደለውን ለማየት እንዲችሉ፣ እዚህ ግባ የማይባሉ አቅመ ደካሞች እና ድሆች የሚመራቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። ድሆችን ማግኘታችን ብዙ ጭንቀቶቻችንን እና ባዶ ፍርሃቶችን እንድናስወግድ እና በህይወታችን ውስጥ በእውነት አስፈላጊ ወደሆነው ነገር ለመድረስ ማንም የማይሰርቀው ውድ ሀብት ማለትም እውነተኛ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ፍቅር እንድንይዝ ያስችለናል። ድሆች የምጽዋዕት ዕቃ ከመሆናቸው በፊት ከጭንቀት እና ከአቅም በላይ ከሆኑ ወጥመዶች ነፃ ለማውጣት የሚረዱን ሰዎች ናቸው።

የቤተክርስቲያን አባት እና ዶክተር ቅዱስ ዮሐንስ ክሪሶስተም በጽሑፎቻቸው ክርስቲያኖች በድሆች ላይ ስለሚያደርጉት ባህሪ በተሰየመ ትችት የተሞላ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ድህነት ሀብታም እንደሚያደርጋችሁ ማመን ካልቻላችሁ ጌታህን አስብና ጥርጣሬህን አቁም ። እሱ ድሃ ባይሆን ኖሮ ሀብታም አትሆንም ነበር። አንድ አስደናቂ ነገር እዚህ አለ፡ ድህነት የተትረፈረፈ ሀብት ምንጭ ሆኗል። ጳውሎስ “ሀብት” ሲል ምን ማለቱ ነው [2ኛ ቆሮ 8፡9 እግዚአብሔርን መምሰል፣ ከኃጢአት መንጻት፣ ፍትሕ፣ መቀደስ እና አሁንም እና ሁል ጊዜ የተሰጡን ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ነገሮችን ማወቅ ነው)።

9. በዚህ አመት የአለም የድሆች ቀን መሪ ሃሳብ ሆኖ የተመረጠው የሐዋርያው ​​ቃል ይህንን ታላቅ የእምነት ህይወታችን አያዎ (ፓራዶክስ) ያቀርባሉ፡ የክርስቶስ ድህነት ባለጠጎች ያደርገናል። እግዚአብሔር ራሱ በልጁ በኢየሱስ ይህንን መንገድ ለመከተል ስለመረጠ ጳውሎስ ለብዙ መቶ ዘመናት ቤተክርስቲያን የተስፋፋችውን እና የመሰከረችውን ይህንን ትምህርት ጳውሎስ ለማቅረብ ችሏል። ክርስቶስ ለእኛ ሲል ድሀ ስለ ሆነ፣ የራሳችን ህይወት በራ እና ተለውጧል እናም አለም የማያደንቀውን እና ሊሰጥ የማይችለውን ዋጋ መያዝ ያስፈልጋል። የኢየሱስ ውድ ሀብት ማንንም የማያገል እና ሁሉንም የሚፈልግ፣በተለይ የተገለሉትን እና የህይወት ፍላጎቶች የተነፈጉትን የሚያፈቅር ፍቅር ነው። ከፍቅር የተነሳ ክብራችንን እና ሰውነታችንን ተቀበለ። ከፍቅር የተነሣ፣ ሞትን፣ የመስቀልን ሞትን እስከ መቀበል ድረስ የታዘዘ አገልጋይ ሆነ (ፊልጵ. 2፡6-8)። ከፍቅር የተነሣ እርሱ “የሕይወት እንጀራ” ሆነ (ዮሐ 6፡35)፣ ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን እንዲያገኙ እና የዘላለም ሕይወት ምግብ እንዲያገኙ አደረገ። የጌታ ደቀ መዛሙርት ይህን ትምህርት መቀበል ከባድ እንደነበረው (ዮሐ. 6፡60)፣ ዛሬም ለእኛም እንዲሁ ነው። ሆኖም የኢየሱስ ቃላት ግልጽ ናቸው፡- ህይወት በሞት ላይ ድል እንዲነሳ፣ ግፍ በክብር እንዲዋጅ  ከፈለግን፣ የክርስቶስን የድህነት መንገድ መከተል፣ ህይወታችንን በፍቅር መካፈል፣ የእለት ተእለት ህይወታችንን እንጀራ ከወንድሞቻችን ጋር መቁረስ እና እህቶች፣ ከትንሽ ጀምሮ፣ ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች የሌላቸው ጋር መቋደስ እንድንችል ያደርገናል። እኩልነትን ለመፍጠር፣ ድሆችን ከችግራቸው፣ ባለጠጎችን ከከንቱነታቸው የሚያላቅቁበት እና ሁለቱንም ከተስፋ መቁረጥ የማውጣት መንገድ ይህ ነው።

“ድሆችንና ታናናሾችን ሠራተኞችን አንናቅ፤ በእግዚአብሔር ውስጥ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ብቻ ሳይሆኑ ኢየሱስን በውጫዊ ህይወቱ ፍጹም የሚመስሉትም ናቸው። የናዝሬት ሠራተኛ የሆነውን ኢየሱስን ፍጹም ይወክላሉ። ከተመረጡት መካከል የበኩር ልጆች ናቸው። ከልደቱ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ድሆች የኢየሱስ የዘወትር ማኅበር አባላት ነበሩ… እናክብራቸው። የኢየሱስንና የቅዱሳን ወላጆቹን ምስሎች እናክብራቸው… ለራሱ የወሰደውን [ሁኔታ] ለራሳችን እንውሰድ… በነገር ሁሉ ድሆችን እንምሰል፣ ለድሆች ወንድሞችና እህቶች፣ ለድሆች ባልንጀራ መሆናችንን አናቋርጥ። እኛ እንደ ኢየሱስ ከድሆች በጣም ድሆች እንሁን፣ እናም እንደ እሱ ድሆችን እንውደድ እና እነርሱን እንከብባቸው።”  ለወንድም ቻርልስ እነዚህ ቃላት ብቻ ሳይሆኑ የሕይወቱን መሥዋዕት ከኢየሱስ ጋር እንዲካፈል ያስቻለው ተጨባጭ የሕይወት መንገድ ነው።

ይህ የ2022 የአለም የድሆች ቀን የጸጋ ጊዜ ይሁንልን። ኅሊናን በግልም ሆነ በጋራ እንድንመረምር እና የኢየሱስ ክርስቶስ ድህነት በሕይወታችን ውስጥ ታማኝ አጋራችን መሆኑን እራሳችንን እንድንጠይቅ ያስችለናል።

ሮም፣ ከቅዱስ ዮሐንስ ላቴራን ባዚሊካ እ.አ.አ በሰኔ 13/2022 ዓ.ም የተላለፈ መልእክት

01 July 2022, 09:35