ፈልግ

ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እንደ ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳዎሎስ ነጻ፣ ነገር ግን ትሁታን አገልጋዮች እንሁን አሉ!

የሁለቱ ታላላቅ ሐዋርያት ፣ የወንጌል ሐዋርያት እና የቤተክርስቲያኗ ሁለት ምሰሶዎች የሆኑትን የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ በዓል እናከብራለን። ዛሬ መታሰቢያቸውን እናከብራለን።፡ እስቲ እነዚህን ሁለት ምስክሮች በእምነት ዓይን በጥልቀት እንመልከት በታሪካቸው ማዕከላዊ ስፍራ ውስጥ የሚገኘው የእነሱ ችሎታ ሳይሆን  ነገር ግን ማእከሉ ላይ የሚገኘው ህይወታቸውን ከቀየረው ከክርስቶስ ጋር መገናኘታቸው ነው። እነርሱ እነሱን የሚፈውስ እና ነፃ የሚያወጣ ፍቅር አጋጥሟቸዋል እናም በዚህ ምክንያት ለሌሎች ሐዋርያ እና የነፃነት አገልጋዮች ሆኑ።

ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በቅድሚያ እነርሱ ነጻ በመውጣታቸው ነጻ የሆኑ ሰዎች ነበሩ። በዚህ ማዕከላዊ ነጥብ ላይ ትኩረታችንን እናድርግ።

የገሊላው ዓሳ አጥማጅ የሆነው ጴጥሮስ በመጀመሪያ ከሁሉም መራራ ከሆነው ውድቀት እና የተገባው አይደለሁኝም ከሚል ስሜት ነፃ ወጥቶ ነበር ፣ ይህ የሆነው የኢየሱስን ቅድመ-ሁኔታ የሌለው ፍቅር በማግኘቱ ነው። ምንም እንኳን በሙያው ዓሳ አጥማጅ ቢሆንም ብዙ ጊዜ አጋጥሞታል። ሌሊቱን ፣ ምንም ነገር ባለመያዙ የሽንፈቱ መራራ ጣዕም (ሉቃስ 5 5 ፣ ዮሐ 21 5) እና ባዶ መረቦችን በተጋፈጠ ጊዜ ፣ ​​መርከቦቹን ወደ ጀልባው ለመሳብ ተፈትኖ ነበር ፣ ጠንካራ እና ግትር ቢሆንም እንኳ ብዙውን ጊዜ በፍርሃት እንዲሸነፍ ያደርግ ነበር (ማቴ 14 30)፣ ምንም እንኳን ፍቅር ያለው የጌታ ደቀ መዝሙር ቢሆንም ፣ የክርስቶስን መስቀል ትርጉም መረዳትና መቀበል ባለመቻሉ በዓለም እይታ መሠረት ነገሮችን ማመዛዘኑን ቀጠለ (ማቴ 16 22)፣ ምንም እንኳን ነፍሱን ለእርሱ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ቢልም ፣ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመግባቱ የተነሳ ጌታውን ለመካድ ተገዶ ነበር (ማርቆስ. 14,66-72)።

ሆኖም ኢየሱስ በነፃነት ይወደውና በእሱ ላይ ይተማመን ነበር። ተስፋ እንዳይቆርጥ፣ መረቦቹን እንደገና ወደ ባሕሩ እንዲጥል ፣ በውሃው ላይ እንዲራመድ ፣ የራሱን ድክመት በድፍረት እንዲመለከት ፣ በመስቀሉ መንገድ እንዲከተለው ፣ ነፍሱን ለወንድሞቹ አሳልፎ እንዲሰጥ፣ በጎቹን እንዲንከባከብ አበረታተው። ስለሆነም ሁሉንም ነገር አደጋ ላይ የሚጥል ድፍረትን እና እንደ ሰው አሳ አጥማጅ ሆኖ የመሰማት ደስታን በመፍጠር በሰው ደህንነት ላይ ብቻ ከሚመሰረቱ ስሌቶች ፣ ከዓለማዊ ጉዳዮች ነፃ አውጥቶታል። ወንድሞቹን በእምነት እንዲጸኑ ለማድረግ እርሱን ጠራው (ሉቃስ 22፡32)። በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንዳዳመጥነው ከጌታ ጋር ለመገናኘት ወደ እዚያው የሚያደርሱትን በሮች ለመክፈት የሚያስችሉ ቁልፎችን እና የማሰር እና የመፍታት ኃይል ለእርሱ በመስጠት፣ ወንድሞችን ከክርስቶስ ጋር ለማስተሳሰር እና የህይወታቸውን ቋጠሮ እና ሰንሰለቶች ለመፈታት ( ማቴ 16 19) የሚያስችል ስልጣን ሰጠው።

ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው - የመጀመሪያው ንባብ እንደነገረን - ለመጀመሪያ ጊዜ ጴጥሮስ ነፃ በመውጣቱ ነበር። እስረኛ አድርገው የሚይዙት ሰንሰለቶች ተበጣጥሰዋል እና ልክ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነፃ በወጡበት ምሽት እንደተከሰተው በፍጥነት እንዲነሳ ፣ ቀበቶውን እንዲታጠቅ እና የጫማውን ማሰሪያ አጥብቆ እንዲወጣ ተጠየቀ። እናም ጌታ በሩን ሁሉ ከፊቱ እየሄደ ይከፍታል (ሐዋ. 12፡7-10)። እሱ ከያዘው እስራት በግልጽ የመወጣቱ፣ ነፃ የመሆኑ፣ ሰንሰለቶች የተሰበሩበት አዲስ ታሪክ ነው። ጴጥሮስ ፋሲካን አጣጥሟል ጌታ ነፃ አወጣው።

ሐዋርያው ​​ቅዱስ ጳውሎስም የክርስቶስን ነፃነት ተመልክቷል። እርሱ እጅግ በጣም ጨቋኝ ከሆነው ባርነት ፣ ከራሱ እና ከመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ስም ከሳኦል ነፃ ወጣ ፣ ትርጉሙም “ታናሽ” ማለት ሲሆን ይህ ስያሜ ደግሞ ወደ ጳውሎስነት ይቀየራል። እንዲሁም ስለ አባቶቹ ወግ እጅግ በጣም ቀናተኛ ደጋፊ በሆነበት ወቅት (ገላትያ 1፡14) እና ክርስቲያኖችን በማሳደድ ዓመፅ እንዲያደርግ ካደረገው ሃይማኖታዊ ቅንዓት ተላቋል። ከዚህ መንፈስ ነጻ ወጥቷል። የሃይማኖት ውጫዊ ገጽታን ማክበር እና የባህል ሰይፍ ለእግዚአብሄር እና ለወንድሞች ፍቅር ልቡን ከመከፍት ይልቅ ልቡ እንዲደነድን አድርጎ ነበር፣ ግትር የሆነ ሰው ነበር፣ እርሱ አክራሪ የነበረ ሰው ጭምር ነው። ከዚህ እግዚአብሔር አዳነው፣ እናም ይልቁንም የወንጌል ተልእኮውን የበለጠ ፍሬያማ ያደረጉትን እነዚህ ድክመቶች እና ችግሮች አለተላቀቀም ነበር-የሃዋርያቱ ድክመቶች፣ አካላዊ ድክመቶች (ገላ 4፡13-14)፣ ዓመፅ ፣ ስደት ፣ ከመርከብ መስመጥ፣ ረሃብ እና ጥማት እንዲሁም እሱ ራሱ እንደ ተናገረው በሥጋው ያሰቃየው እሾህ (2 ቆሮ 12፡7-10) ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ነጻ አላወጣውም ነበር፣ ነገር ግን እንዲጋፈጣቸው ብርታቱን ሰጠው።

ጳውሎስ “ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔር ብርቱዎችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ” (1 ቆሮ 1፡27) ፣ “ኃይል በሚሰጠን በእርሱ ውስጥ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደምንችል” ተገንዝቧል (ፊል 4፡13) ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማነው? (ሮሜ 8፡35-39) በማለት ይናገራል። በዚህ ምክንያት በሕይወቱ መጨረሻ ላይ - በሁለተኛው ንባብ ላይ እንደ ሰማነው - ጳውሎስ “ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ። ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል” (2 ጢሞቴዎስ 4፡17.18) ለማለት በቅቶ ነበር። ጳውሎስ የትንሳኤ ልምምድ ነበረው-ጌታ ነፃ አወጣው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፣ ቤተክርስቲያን እነዚህን ሁለት የእምነት ግዙፍ አባቶች ትመለከታለች እናም የወንጌልን ኃይል በዓለም ላይ እንዲሰራጭ ያደረጉትን ሁለት ሐዋርያትን ትመለከታለች ፣ ምክንያቱም በመጀመሪያ ከክርስቶስ ጋር በመገናኘታቸው የተነሳ ነጻ ለመውጣት በመቻላቸው ነው። እርሱ አልፈረደባቸውም ፣ አላዋረዳቸውም ፣ ነገር ግን ህይወታቸውን በፍቅር እና በቅርበት ተካፍሏል ፣ በገዛ ጸሎቱ ይደግፋቸዋል እናም አንዳንድ ጊዜ በለውጥ ጉዞ ላይ መራመዳቸውን መቀጠል ይችሉ ዘንድ ያናውጣቸዋል። ኢየሱስ ለጴጥሮስ በትህትና “እምነትህ እንዳይደክም ስለ አንተ ጸለይኩ” (ሉቃ 22፡32) ብሏል፣ ለጳውሎስ “ሳውል ፣ ሳውል ፣ ለምን ታሳድደኛለህ?” ሲል ጠየቀው (ሥራ 9: 4)። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲሁ ከእኛ ጋር ያደርጋል ፣ እርሱ ስለእኛ በመጸለይ እና ከአብ ዘንድ በማማለድ የእርሱን ቅርበት ያረጋግጥልናል ፣ ተነስተን መራመዳችንን ለመቀጠል ብርታት ለማግኘት እንድንችል እና ስህተት ስንሠራ በእርጋታ እንደ ገና ተነስተን እንድንጓዝ ይረዳናል።

በጌታ የተነካን እኛ እኛም እንደ እነርሱ ነጻ ወጥተናል። እና እኛ ሁል ጊዜ ነፃ መውጣት ያስፈልገናል ፣ ምክንያቱም እምነት የሚጣልበት ቤተክርስቲያን መሆን የምንችለው ነፃ ቤተክርስቲያን መሆን ስንችል ብቻ ነው። እንደ ጴጥሮስ እኛም አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ ባልሆንበት የዓሳ መጥመድ ሕይወታችን ፊት ከሽንፈት ስሜት ነፃ እንድንሆን ተጠርተናል፣ ከሚያሰናክለን እና ከሚያስፈራን ፍርሃት ለመላቀቅ፣ በጥርጣሬዎቻችን ውስጥ ገብተን በራሳችን ምቾቶች ውስጥ ገብተን ከመቆለፍ ይልቅ የትንቢት ድፍረቶችን ተጠቅመን ነጻ መሆን ይኖርብናል። እንደ ጳውሎስ እኛ ከውጫዊ ግብዝነት እንድንላቀቅ ተጠርተናል፣ ለእግዚአብሄር ቦታ ከማይሰጥ ድክመት ይልቅ እራሳችንን በዓለም ጥንካሬ ለመጫን ከሚያስከትለው ፈተና ነፃ ለመሆን፣ ግትር እና ለውይይት ዝግ እንድንሆን ከሚያደረገን ከሃይማኖታዊ ወጎች ነፃ እንድንሆን፣  ከስልጣን ሺሚያ ነጻ እንድንሆን እና ጥቃት ይሰነዘርብኛ ከሚለው አደገኛ ፍርሃት ነጻ እንድንሆን ተጠርተናል።

ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በእጃችን በአደራ እንድንጠብቅ የሰጡንን ቤተክርስቲያን በታማኝነት እና በርህራሄ የሚመራውን ቤተክርስቲያን ምስል ይሰጡናል - ቤተክርስቲያንን የሚመራው እሱ ነው፣ የደካማ ሰዎች መሰብሰቢያ ቤተ ክርስቲያን ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ጠንካራ የሆነች፣ እራሷን የተቀበለችውን ያንን ነፃነት ለዓለም ልታቀርብ የምትችል የነፃነት ቤተክርስቲያን ምስል-ከኃጢአት ፣ ከሞት ፣ ከመንፈሳዊ ኪሳራ፣ ከፍትሕ መጓደል ስሜት ፣ የዘመናችን የሴቶች እና የወንዶች የሕይወት ተስፋ በማለምለም ተስፋ ማምጣት እንችል ዘንድ ጥሪ ያቀርቡልናል።

እስቲ ዛሬ እራሳችንን እንጠይቅ ፣ በዚህ ክብረ በዓል እና ከዚያ በኋላ ፣ እራሳችንን እንጠይቅ-ከተሞቻችን ፣ ማህበራቶቻችን ፣ ዓለማችን ምን ያህል ነፃ መውጣት ይፈልጋሉ? ስንት ሰንሰለቶች መሰባበር አለባቸው፣ ስንት የተዘጉ በሮች መከፈት አለባቸው! እኛ በዚህ ነፃነት ተባባሪዎች ልንሆን እንችላለን ፣ ግን እኛ እራሳችንን ከኢየሱስ ጋር በአዲስ መልክ ለመቀላቀል እና በመንፈስ ቅዱስ ነፃነት ለመራመድ የመጀመሪያችን ከሆንን ብቻ ይህንን እውን ማደረግ እንችላለን።

ዛሬ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንድሞቻችን የሆኑት ሊቀ ጳጳሳት ፓሊየም (የጥንት ሮማውያን የሚጠቀሙበት ካፖርት ፣ ባለ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው የቤተክርስቲያን አልባስ ሲሆን ባለ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ልብስ የያዘ ካባ ላይ የሚለብስ የቤተክርስቲያን አልባስ ነው-ሄማሽን ከተሰኘ የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተከታዮች መሆናቸውን የሚያሳይ እና በየአመቱ የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ አመታዊ በዓለ በሚከበርበት ወቅት በመላው ዓለም ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የሚሰጥ አልባስ ነው) ይቀበላሉ። ይህ ከቅዱስ ጴጥሮ ጋር ያለው የአንድነት ምልክት ነፍሱን ለመንጋው የሰጠውን እረኛ ተልእኮ ያስታውሳል። እረኛው ከራሱ ነጻ የወጣ እና ለወንድሞች የነፃነት መሣሪያ ሆኖ ህይወቱን በመስጠት ነው። ዛሬ በዚህ አጋጣሚ በውድ ወንድሜ በርተሎሜዎስ የተላከው የሊቀ ጳጳስ መንበረ ፓትርያርክ ልዑካን ቡድን ከእኛ ጋር ይገኛሉ፣ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክቴን በማስተላለፍ በክርስቶስ ያመኑት አማኞች በሚጓዙበት መንገድ በነጻነት ጎዳና ላይ የአንድነት ውድ ምልክት ነው። በመገኘታችሁ እናመሰግናለን።

ስለ ክርስቶስ ፣ ስለ መጋቢዎች ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ፣ ስለ ሁላችን እንጸልይ ፣ ስለዚህ በክርስቶስ ነጻ ወጥተን በዓለም ዙሪያ የነፃነት ሐዋርያት እንሁን።

ምንጭ፡ የጎሮጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በሰኔ 22/2013 ዓ.ም የክርስትና እምነት አምዶች የሚባሉት የታላላቆቹ የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳዎሎስ አመታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካደረጉት ስብከት የተወሰደ።

30 June 2022, 13:20