ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥንዶች ወደ ጋብቻ የሚያደርጉትን ጉዞ ቤተክርስቲያን በቅርበት ልትደግፍ ይገባል አሉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥንዶች ወደ ጋብቻ የሚያደርጉትን ጉዞ ቤተክርስቲያን በቅርበት ልትደግፍ ይገባል አሉ!  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥንዶች ወደ ጋብቻ የሚያደርጉትን ጉዞ ቤተክርስቲያን በቅርበት ልትደግፍ ይገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ "የጋብቻ ጉዞዎችን የሚደግፍ ለትዳር ሕይወት የሚሆን የቤተክርስቲያን አስተምህሮ” ለማሰናዳት የሚያስችል ድህረ መመሪያዎችን ማዘጋጀታቸው የተገለጸ ሲሆን ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ወይም በተፋቱ ባለትዳሮች ምክንያት የሚደርሰውን ስቃይ ለማስወገድ የወደፊት የትዳር ጓደኞችን በተሻለ ሁኔታ ለትዳር ለማዘጋጀት የሚረዳ ድህረ መመሪያ እንደ ሆነም ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የምእመናን፣ ቤተሰብ እና ሕይወት ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ ሰኔ 08/2014 ዓ.ም  ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አዲስ ሐዋርያዊ መመሪያዎችን አውጥቷል፣ ይህም “የሐይማኖት ትምህርት የድርጊት መርሃ ግብሮች ለትዳር ሕይወት” ለማዘጋጀት አዲስ መንገድ እንደ ሚቀይስ ከወዲሁ ይጠበቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስለ ሰነዱ የሰጡትን ድህረ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ የሚያመለክት በላቲን ቋንቋ “Amoris Laetitia” (የፍቅር ሐሴት” የተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክታቸው በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የቤተሰብ ዓመት “ፍሬ” እንደሚወክል በመግለጽ በሰነዱ መቅድም ላይ ጽፈዋል።

"ቤተክርስትያን በየትኛውም ዘመን፣ የምስጢረ ተክሊልን እና ከሱ የሚፈልቀውን የቤተሰብ ህይወት፣ በተለይም ለወጣቶች ያለውን ውበት እና ብዛት እንደ አዲስ ለማወጅ ተጠርታለች" በማለት መጻፋቸው ተገልጿል።

የከሰሙ ወይም ውድቅ የሆኑ ጋብቻዎችን ቁጥር መቀነስ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ሰነዱ ትዳራቸውን በእምነት ዓለት ላይ ለመገንባት እንዲረዳቸው በጥንታዊው የጥምቀት በዓል ለአዋቂዎች ሞዴል ላይ በመመስረት ወደ እውነተኛው "የሐይማኖት ተማሪነት" የሚወስደውን መንገድ ያሳያል ብለዋል ።

ብዙ ባለትዳሮች ከሠርጋቸው በፊት ላይ ላዩን ብቻ ዝግጅት እንደሚያደርጉ መገንዘባቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው በመሆኑም ትዳራቸው “በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈርስ ከመሆኑም በላይ የመጀመሪያዎቹን የማይቀር ቀውሶች እንኳን መቋቋም እንደማይችሉ” ደካማ መሠረት ላይ ሊጥል እንደሚችል ተናግሯል።

“የጋብቻ ውድቀቶች ታላቅ ስቃይ ያመጣሉ እናም በሰዎች ላይ ከባድ ቁስሎችን ይተዋል ። ተስፋ ቆርጠዋል፣ መራራ እና በጣም በሚያሰቃዩ ጉዳዮች፣ በእግዚአብሔር በራሱ በሰው ልብ ውስጥ በተፃፈው የፍቅር ጥሪ ማመን ያቆማሉ” ብለዋል።

እናት ቤተ ክርስቲያን ጥንዶችን ታጅባለች።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በምላሹ፣ ቤተክርስቲያኗ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመጋባት የሚሹ ጥንዶችን በፍትህ ፍላጎት ታጅበው እንዲሄዱ ማድረግ ይኖርባታል ብለዋል።

ማንም እናት በልጆቿ መካከል ተወዳጅ ለመሆን እንደምትጫወት ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ልጆቿን በተለየ መንገድ አትይዝም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ካህናት ለመሆን የሚፈልጉ ወይም ወደ ሃይማኖታዊ ሕይወት የሚገቡ ሴቶችን እና ወንዶች እንደምታደርግ፣ የታጩ ጥንዶችን ወደ ጋብቻ ለመሸኘት ብዙ ጊዜና ጉልበት መስጠት አለባት ብለዋል።

ባለትዳሮች ልጆችን በመውለዳቸው፣ ስለሚያሳድጓቸው እና በእድገታቸውም አብረው ስለሚሄዱ ብቻ ሳይሆን በቤተሰባቸው ውስጥ አረጋውያንን ስለሚንከባከቡ እና ሰዎችን ለማገልገል ስለሚውሉ እውነተኛ 'የሕይወት ጠባቂዎች' ናቸው ሲሉ ተናግሯል። አካል ጉዳተኞች እና ብዙ ጊዜ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ስለሚሹ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

በመንገድ ላይ አንድ ላይ መጓዝ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለወደፊት ባለትዳሮች እውነተኛ መመዘኛ እንዲያቋቁሙ ፍላጎታቸውን ደጋግመው ገልጸዋል፣ ይህም ሁሉንም የምስጢራት ጎዳና ደረጃዎችን ያካትታል፡ ለጋብቻ የመዘጋጀት ጊዜ፣ ክብረ በዓሉ እና ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ሁሉ ከቤተሰብ ጋር አብሮ መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ዓላማው ከሠርግ በኋላም ቢሆን በተለይም በችግር ጊዜ ወይም በተስፋ መቁረጥ ጊዜ ከጥንዶች ጋር በህይወት ጉዞ ውስጥ አንድ አስፈላጊ የሆነ መንገድ መሄድ ነው" ብለዋል ።

ስጦታ እና ኃላፊነት

ሰነዱ ስጦታም ሀላፊነትም ነው ብለዋል፣ ምክንያቱም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መመሪያዎችን በባህላዊ ግንዛቤ ላይ ተመስርተው በተጨባጭ መርሐ ግብሮች ውስጥ እንዲተገበሩ ይጠይቃል።

“መንፈስ ቅዱስ እንድንፈጽመው የሚጠይቀንን የቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስት እና ሐዋርያዊ አገልጋዮች ትህትና፣ ቅንዓት እና የፈጠራ ስራ እና እነርሱን የሚረዱትን የቤተሰብን ምስረታ፣ አዋጅ እና አጃቢነት አስፈላጊ እና አስፈላጊ የሆነውን ስራ ውጤታማነት እንዲያሳድጉ እጠይቃለሁ ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቤተክርስቲያን ቀሳውስት ይህንን አዲስ ሃላፊነት በመጋፈጥ ደፋር እንዲሆኑ በማሳሰብ "የጋብቻ ጉዞ ለትዳር ሕይወት" ሰነድ መቅድም አጠቃለዋል።

"አእምሯችንን እና ልባችንን ለወደፊት ቤተሰቦች አገልግሎት እናውል" ሲሉ አክለው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ጌታ እንደሚደግፈን፣ ጥበብን እና ጥንካሬን እንደሚሰጠን፣ ፍላጎታችን እንዲያድግ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የቤተሰቡን ወንጌል ለአዳዲስ ትውልዶች ስንሰብክ የሚያስደስት እና የሚያጽናና የወንጌል ደስታን እንድንለማመድ እንደሚፈቅድልን አረጋግጣለሁ ” ማለታቸው ተገልጿል።

15 June 2022, 13:46