ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ‘እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ የሚገኙትን ቤተሰቦች ይባርክ እና ይጠብቅ’ ማለታቸው ተገለጸ!

10ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ስብሰባ በሮም ከተማ ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 19/2014 ዓ.ም ተካሂዶ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በብፁዕ ካርዲናል ኬቨን ፋሬል መሪነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተገኙበት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ በተከናወነው መስዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁ ተገልጿል። በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባደረጉት ስብከት “ፍቅርን የምንማርበት የመጀመሪያ ቦታ ቤተሰብ ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ራስ ወዳድነት፣ ግለሰባዊነት፣ በግዴለሽነት እና በብክነት ባሕል በተመረዘ ዓለም ውስጥ የቤተሰብን ውበት በማድነቅ “ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ” የቤተሰብን ሕልውና ልንጠብቅ የሚገባን ሰዓት ላይ ደርሰናል ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቫቲካን እየተካሄደ በነበረው 10ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ስብሰባ “የቤተሰብ ፍቅር፡ ጥሪ እና የቅድስና መንገድ” በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ በተካሄደው የምስጋና መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት ላይ ነበር ይህንን የተናገሩት።

የምእመናን፣ ቤተሰብ እና ሕይወት ጉዳዮችን በሚመለከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተዘጋጀው ስብሰባ ለአምስት ቀናት ያህል የቆየ ዝግጅት ሲሆን እሁድ እለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት “የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” በተሰኘው ጸሎት መጠናቀቁ ተገልጿል።

በዓለም የቤተሰብ ስብሰባ ወቅት የተከሰቱትን የተለያዩ ልምዶች፣ ዕቅዶች፣ ህልሞች፣ ስጋቶች እና እርግጠኛ ያልሆኑ ጉዳዮችን በመግለጽ የማሰላሰያ እና ልምዶችን የመለዋወጫ ጊዜዎችን የሰጠ ክስተት መሆኑን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የገለጹ ሲሆን “የአንድ ትልቅ ህብረ ከዋክብት” በማለት ስብሰባውን ገልጸውታል።  “አባቶች፣ እናቶች፣ እና ልጆች፣ አያቶች፣ አጎቶች እና አክስቶች፣ ጎልማሶች፣ ታናናሾች እና ሽማግሌዎች” እያንዳንዳቸው የተለየ የቤተሰብ ተሞክሮ ያመጣሉ፣ ነገር ግን በአንድ ተስፋ እና ጸሎት ላይ ይጸናሉ ብለዋል።

"እግዚአብሔር ቤተሰቦቻችሁን ሁሉ ይባርክ እና ይጠብቅ"

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል በዕለቱ በተደርገው ሥርዓተ አምልኮ ንባቦች ላይ ተንተርሰው ሁሉም ሰው በትዳር እና በቤተሰብ ፍቅር ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ብርሃን እንዲያበራ አንጸባርቀዋል።

ቤተሰብ ፍቅርን የምንማርበት ቦታ ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ፣ ሐዋርያው ​​እግዚአብሔር የሰጠን ነፃነት ሙሉ በሙሉ ወደ ፍቅር እንደሚመራን ይነግረናል፣ ስለዚህም “አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል” (ገላ. 5፡13) ማለታቸው ተገልጿል።

ወደ ባለትዳሮች ዘወር ሲል ቤተሰብ ለመገንባት ያደረጉትን ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ እና “ነፃነታችሁን ለራሳችሁ ሳይሆን አምላክ ከጎናችሁ ያደረገውን ሰዎችን በመውደድ ላይ ያተኮረ ይሁን ” በማለት አወድሷል።

እንደ ትናንሽ ደሴቶች ሆናችሁ ለብቻችሁ ከመኖር ይልቅ “እርስ በርሳችሁ አገልጋዮች ሆናችሁ” መኖር ይሻላል ብሏል።

በቤተሰብ ውስጥ ነፃነት የሚኖረው በዚህ መንገድ ነው ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አስረድተዋል፣ ሁሉም “ፕላኔቶች” ወይም “ሳተላይቶች” እያንዳንዳቸው በምህዋሩ ላይ ነው የሚሽከረከሩት ብለዋል። ቤተሰብ የምንገናኝበት፣ የምንጋራበት፣ ከራሳችን ወጥተን ሌሎችን ለመቀበል እና ከጎናቸው የምንቆምበት ቦታ ነው በማለት አክለው ገለጸዋል።

"ቤተሰብ ፍቅርን የምንማርበት የመጀመሪያ ቦታ ነው."

ይህንን በጥልቅ እምነት ስናረጋግጥም “ሁልጊዜም ቢሆን በሁሉም ምክንያቶችና በተለያዩ ሁኔታዎች እንደማይከሰት ጠንቅቀን እናውቃለን” ብሏል።

“እናም የቤተሰብን ውበት በማወደስ፣ እኛ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ ቤተሰብን ለመጠበቅ እንገደዳለን። ቤተሰቡ በራስ ወዳድነት፣ በግለኝነት፣ ዛሬ ባለው የግዴለሽነትና የብክነት መርዝ እንዲመረዝ አንፍቀድ፣ በዚህም ምክንያት የመቀበልና የአገልግሎት መንፈስ የሆነውን መድብለ ዘር እንድናጣ አንፍቀድ” ብለዋል።

በትውልዶች መካከል ያለው ግንኙነት

ሁለተኛው የመጽሐፈ ነግሥት ውስጥ የተጠቀሰውን በነቢዩ ኤልያስና በኤልሳዕ መካከል ስላለው ግንኙነት ይናገራል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በትውልዶች መካከል ስላለው ግንኙነት፣ ከወላጆች ወደ ልጆች "ምስክርነት መተላለፍ" እንዳለበት ያስታውሱናል።

ሁሉም ነገር የተመሰቃቀለ እና አሳሳቢ በሚመስልበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ወላጆች “በማህበረሰባችን ውስብስብ እና ግራ መጋባት ውስጥ ልጆች መንገዳቸውን ማግኘት አይችሉም” ብለው ይፈራሉ። ይህ ፍርሃት አንዳንድ ወላጆችን እንዲጨነቁ እና ሌሎች ደግሞ ከመጠን በላይ እንዲጠበቁ ያደርጋቸዋል ያሉ ሲሆን “አንዳንድ ጊዜ፣ ወደ ዓለም አዲስ ሕይወት የማምጣት ፍላጎትን እስከ ማሰናከል ያበቃል ብለዋል።

ሆኖም አምላክ በአዲሱ ትውልድ ላይ እምነት እንዳለው ያሳየን በኤልያስና በኤልሳዕ መካከል ስላለው ዝምድና በማሰላሰል “ወላጆች በአምላክ ድርጊት ላይ ማሰባቸው ምንኛ አስፈላጊ ነው!” ብለዋል።

"እግዚአብሔር ወጣቶችን ይወዳል፣ ይህ ማለት ግን ከሁሉም አደጋዎች፣ ከማንኛውም ፈተና እና መከራ ሁሉ ይጠብቃቸዋል ማለት አይደለም” በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “እግዚአብሔር በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ እኛን ከመጠን በላይ ለመጠበቅ አይመጣም፣ በተቃራኒው ወጣቶችን ያምናል እናም እያንዳንዳቸው የህይወት እና የተልዕኮ ከፍታዎችን እንዲያሳድጉ ይጠራቸዋል" ብለዋል።

እናም ወላጆች ልጆቻቸውን ከትናንሽ ችግሮች እና መከራዎች እንዳይከላከሉ አበረታቷቸዋል፣ ነገር ግን የሕይወትን ፍቅር ለእነርሱ ለማሳወቅ እንዲሞክሩ፣ ጥሪያቸውን የማወቅ ፍላጎት እንዲቀሰቀሱ እና እግዚአብሔር በአእምሮው የያዘውን ታላቅ ተልእኮ እንዲቀበሉ እነሱን” ማበረታታት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

"ውድ ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ጥሪያቸውን እንዲያውቁ እና እንዲቀበሉ ከረዳቿቸው፣ እነሱም በዚህ ተልእኮ 'እንደሚያዙ' ታያላችሁ፣ እናም ለመጋፈጥ እና ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን ጥንካሬ ያገኛሉ፣ የህይወት ችግሮች ለመጋፈጥ ይነሳሳሉ” በለዋል።

የማያልቅ ጉዞ

በመጨረሻም የሉቃስ ወንጌል “ኢየሱስን መከተል ማለት ከእሱ ጋር በሕይወታችን ክንውኖች ውስጥ ማለቂያ የሌለውን “ጉዞ” ማድረግ ማለት እንደሆነ ይነግረናል” ያሉት ቅዱስነታቸው "ይህ ለናንተ ባለትዳሮች ምንኛ እውነት ነው!" በማለት ጥያቄ አንሰተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ክርስቲያናዊ ጥሪያችን “ችግር፣ የሀዘን ጊዜያት እና የፈተና ጊዜዎች ቢኖሩትም ታማኝነትን እና ትዕግስትን በማሳየት ጋብቻን እና የቤተሰብ ህይወትን እንደ ተልእኮ እንድንለማመድ ይጋብዘናል” ያሉ ሲሆን “ከሰው ልጆች የተወለዱ ተቃውሞዎች፣ ተግዳሮቶች፣ ውድቀቶች እና አለመግባባቶች” ጊዜያት መኖራቸው የማይቀር ነው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ነገር ግን በክርስቶስ ጸጋ “እነዚህን ወደ ሌሎችን መቀበል እና ያለምክንያት ወደ ፍቅር እንድንለውጥ” ተጠርተናል ብለዋል።

የጋብቻ እና የቤተሰብ ጥሪን በመቀበል፣ ባለትዳሮች ጉዞ ጀመሩ፣ “በትክክል ወዴት እንደሚያመራ አስቀድመው ሳያውቁ፣ ምን አዲስ ሁኔታዎች፣ ያልተጠበቁ ክስተቶች እና አስገራሚ ነገሮች ውሎ አድሮ ሊመጡ እንደሚችሉ ሳያውቁ” ነበር የትዳር ጎዞዎቻቸውን የጀመሩት ያሉት ቅዱስነታቸው "ከጌታ ጋር መጓዝ ማለት ይህ ነው። ሕያው፣ ሊተነብይ የማይችል እና አስደናቂ የሆነ የግኝት ጉዞ ነው” ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን የተወለደችው በቤተሰብ ውስጥ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቤተሰቦች ወደፊት እንዲመለከቱ በመጋበዝ “ኢየሱስ ሁልጊዜ በመንገድ ላይ በፍቅር እና በአገልግሎት እንደሚቀድመን፤ ሁል ጊዜ ክፍት፣ ወደ ውጭ የሚመራ፣ ደካሞችን እና የቆሰሉትን ‘ለመንካት’ ችሎታ ያለው፣ የአካል ድካም እና የመንፈስ ድካም፣ እና በመንገድ ላይ የምታገኛቸውን ሁሉ’ መሆን ያለበትን የቤተሰብ ፍቅር ደስታ እንዲካፈሉ አበረታቷቸዋል። ቤተክርስቲያን ከእነሱ ጋር እና በእነርሱ ውስጥ እንዳለች በማረጋገጥ! "ቤተክርስቲያን የተወለደችው ከቤተሰብ፣ ከናዝሬት ቅዱስ ቤተሰብ ነው የቤተሰብ ስብስብ ናት ቤተክርስቲያን” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

25 June 2022, 13:24